>

‹‹ መጀመሪያ አይጧን ከጉድጓድ አዉጣት፣ ከዚያም ግደላት ›› ዓይነት ጨዋታ ዛሬ ላይ አይሰራም!!! (በፍቃዱ ሞረዳ)

‹‹ መጀመሪያ አይጧን ከጉድጓድ አዉጣት፣ ከዚያም ግደላት ›› ዓይነት ጨዋታ ዛሬ ላይ አይሰራም!!!
በፍቃዱ ሞረዳ
የአቶ ለማ መገርሳ ኦዴፓና አቶ የዳዉድ ኢብሳ ኦነግ ስለተፈራረሙት ሰነድ ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርጉ ሲጠየቅ ከርሟል፡፡ በሁለቱም በኩል እስከአሁን  ዝርዝር ስምምነቱን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ መኖሩን ቢያንስ እኔ አላዉቅም፡፡
  የምናዉቀዉ ነገር ቢኖር በሁለቱም ወገኖች በኩል ግልፅነት ባለመኖሩ ሕዝብ ለኅሊና ፍርድ መቸገሩን ነዉ፡፡የምናዉቀዉ ነገር ቢኖር በሁለቱ ወገኖች ዳፋ የድሃ ሕዝብ ልጆች የጥይት ቀለብ እየሆኑ መሆኑን ነዉ፡፡  አሁን በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል ያለዉ ሁኔታ ጥሩ አይደለም፡፡ የመቶና የሺህ ታጣቂዎችም ጉዳይ አይመስልም፡፡
  የኢሕአዴግ መንግሥት ‹‹ መጀመሪያ አይጧን ከጉድጓድ አዉጣት፣ ከዚያም ግደላት ›› ዓይነት የእነእንትናን ጨዋታ እየተጫወተ ከሆነ ችግሩ ከታሪክ አለመማርም፣ መሬት ላይ ያለዉንም ሀቅ አለማወቅም ነዉ፡፡
  ዛሬ ጥይት ከቶዉንም የሚፈታዉ ችግር የለም፡፡በዚያ መንገድ ‹‹አሸናፊ እሆናለሁ›› ብሎ የሚያስብም ካለ በእርግጥ ግብዝ ነዉ፡፡
ዋናዉ መፍትሔ በጨዋነት ቁጭ ብሎ በሕዝብ ፊት መነጋገር ነዉ፡፡ምንም እንኳን ሁለቱም ተፋጣጭ ኃይሎች ሕጋዊ የሆነ የሕዝብ ዉክልና ባይኖራቸዉም ለሕዝብ የኅሊና ፍርድ ራስን ማቅረብ ተገቢ ነዉ፡፡ ከቅርብም ሆነ ከሩቅ፣ ከግራና ከቀኝ የሚያጨበጭበዉና የሚያሸረግደዉም እዉነት ለሕዝብና ለሀገር ሠላም አስቦ አለመሆኑን እንደሚታወቅ መዘንጋት የለበትም፡፡ ሕልማቸዉ ሥልጣን ወይም ከጉልበተኛዉ የተረፈ ፍሪፋሪ ከመሆን እንደማያልፍ ይታወቃል፡፡
 በአጠቃላይ  ደም ማፍሰስና ሕይወትን ማጥፋት ይቁም፡፡ ሁሉም መሳሪያዉን አስቀምጦ ወደንግግር ይመለስ፡፡ አሽቀባጮችና ደላሎችም አደብ ግዙ፡፡
   Warrii gamaa gamasii- qalanii gogaa dhisuu
   Fooniin foon wawwaadanii- foon walii nunyaachisuu.
 Jennee ture. Ammas inumajenna.
Filed in: Amharic