>

በየትኛውም አለም  በአንድ ሀገር ያለው አንድ የታጠቀ መንግስት ብቻ ነው!!! (ሰይድ የሱፍ አሊ)

በየትኛውም አለም  በአንድ ሀገር ያለው አንድ የታጠቀ መንግስት ብቻ ነው!!!
ሰይድ የሱፍ አሊ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ያወሩትን ነገር ቶሎ የመርሳት ችግር አለባቸው?
መጀመሪያ ኦነግ ትጥቁን በሰላም  አይፈታም  አሉ ። መንግስት ትጥቅ ሊያስፈታቸው ያሉበት ድረስ ሲሄድ “ምክንያቱ ምን እንደሆነ  ባልታወቀ ምክንያት  የታጠቀ የመንግስት ሰራዊት መጥቶ እየተዋጋኘ ነው” ይላሉ።
የምር የመንግስት ወታደር  ኦነግ ወዳለበት አካባቢ  ለምን እንደመጣ ከረሱት ወይ ነገሮችን ቶሎ የመርሳት ካልሆነም ትኩረት ( ሀሳባቸውን) ለረጅም ጊዜ አሰባስበው የማቆየት ( short attention span) ችግር  አለባቸው ማለት ነው።
በመንግስት እና በኦነግ መካከል የነበረውን እሰጣገባ  አቶ ዳውድ ቢረሱትም እኛ አናስታውሰዋለን።
(October 7)
አቶ ዳውድ ኢብሳ 
ኦነግ ትጥቅ አይፈታም ፣ ትጥቅ ፈቱ መባል አንፈልግም  ከዚህ ጋር ተያይዞ ያለው ምንድነው አንዱ ትጥቅ የሚፈታ ሌላው የሚያስፈታ ይመስላል ብለው በሚዲያ ተናገሩ።
(October 10)
የመንግስት ኮሚንኬሽን ፅ/ቤት ሚንስትር ዴታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ።መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ህገመንግስታዊ ስርአቱን ለማስጠበቅ ሲል ኦነግን ትጥቅ እንደሚያስፈታ ተናገረ ።
ጥቅምት 30, 2018 የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ይህን መግለጫ አወጣ ።ምክንያቱን በትክክል ለመረዳት አዳጋችና ኣስቸጋሪ በሆነብን ሁኔታ። ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት በቄሌም ወለጋና በጉጂ ዞን ኣከባቢዎች እርምጃ መውሰድ ጀምሮአል።
አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ መንግስት የኦነግን ትጥቅ ለማስፈታት በወሰደው እርምጃ ተደስተዋል።
ጥቂት የኦነግ ደጋፊወች ደግሞ ይህን እርምጃ ተቃውመውታል። የኦነግ ደጋፊወች ያልተረዱት ነገር በየትኛውም አለም  በአንድ ሀገር ያለው አንድ የታጠቀ መንግስት ብቻ ነው ።የኢትዮጵያ ህዝብ ማእከላዊ መንግስቱ በየትኛውም የሀገሪቱዋ ክፍል ህግ እና ስርአት ለማስከበር የሚወስደውን እርምጃ ይደግፋል ።
መንግስት  ሰላም፣ መረጋጋት እና የህግ የበላይነት በዘላቂነት የማስከበር ግዴታ አለበት ይህን ህጋዊ እና ታሪካዊ ሀላፊነቱን ለማከናወን በሚወሰደው እርምጃ ህዝቡ ለተወሰነ ጊዜ ቢሆንም ሊቸገር እና ነፃነቱ ሊታቀብ እንደሚችል ይታወቃል ።በአሁኑ ሰአት የዶ/ር አብይ መንግስት ኦነግን ትጥቅ ለማስፈታት የጀመረው ዘመቻ በሀገራችን ጠንካራ ማእከላዊ መንግስት መኖሩን ለሁሉም ወገን መልእክት የሚያስተላልፍበት ጥሩ አጋጣሚ ነው ።
Filed in: Amharic