>

ክቡር ፕሬዚዳንት ጊዜው የይቅርታ ነውና ኮ/ል በዛብህን ጨምሮ ሌሎች ምርኮኞችን ይፍቱልን! (ደግፌ አስረስ)

ክቡር ፕሬዚዳንት ጊዜው የይቅርታ ነውና ኮ/ል በዛብህን ጨምሮ ሌሎች ምርኮኞችን ይፍቱልን!
ደግፌ አስረስ
እንደሚታወቀው የኢትዮጲያ ሃገር ኩራት የሆነው ጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት በኤርትራ ተማርኮ ይኽው ይሙት ይኑር ሳይታወቅ ለ20 ዓመታት በእስር ላይ እየማቀቀ ይገኛል።
ኮ/ል በዛብህ በኢትዮ-ሱማሊያ ጦርነት 196 ጊዜ ወደ ጠላት ክልል በመብረር የጠላትን ምሽግና ጦር ብትንትኑን ያወጣ የኢትዮጲያ ጀግና ነው። ይሁን እንጂ ከራሱ ውጭ የኢትዮጲያ ጀግኖች ጀግንነት የማይዋጥለት የወያኔ መንግስት በሰራው የተንኮል ሴራ እንዲማረክ አስገድዶታል።
 የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጲያዊነት ምልክታቸው ወደ ሆነች የጀግኖች ከተማን ጎንደር ለጉብኝት ስለሚመጡ “የኦሮሞዎች ደም የኛም ደም ነው” ያለው የጎንደር ህዝብ  “… እኛ ብንሞት ሌላ ሰው ይተካናል፤ መተኪያ የሌላት ሀገር  ከሞተች ግን ተተኪው ትውልድ ስለሚሞት ዋጋ አይኖረውም፡፡ የሀገርን ሉአላዊነት በአስተማማኝነት መጠበቅ ቆራጥነት እና ልበ ሙሉነት ይጠይቃል፡፡ እኛ በሕይወት ቆመን እያየን ጠላት አንዲት ስንዝር መሬት ቆርሶ መሄድ ቀርቶ በአንድ እግሩ እንኳ ሊቆምባት አይችልም፡፡ ከሀገር ወዲያ ሌላ መኖሪያ ዋሻ ስለሌለ በሃገርና በነፃነት ጉዳይ ምንም ቀልድ ሊኖር አይችልም፡፡…” ላለው ኢትዮጲያዊ ጀግና “ፍትህ ለጀግናው ኮ/ል በዘብህ ጴጥሮስ፣ ስለጀግናው በዛብህ ጴጥሮስ መረጃ ይሰጠን፣ የመደመርና ይቅር የመባባል ወቅት ስለሆነ በዛብህን ጨምሮ ሌሎች ምርኮኞችን ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ይፍቱልን” የሚል የተለያዩ ባነሮችን በመያዝ ከዚህ በፊት ለጀግኖች ተቆርቋሪ መሆናችሁን የምትታወቁበትን ገድል አሁንም በነገው ዕለት በመድገም ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጥያቄ እንድታቀርቡልን እንጠይቃለን።
ፍትህና መታወስ ለጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ!!!
Filed in: Amharic