>
8:35 pm - Sunday January 23, 2022

አገዛዙ ያረከሳቸው የኢትዮጲያውያንን ዕሴቶች በጨረፍታ (ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ)

አገዛዙ ያረከሳቸው የኢትዮጲያውያንን ዕሴቶች በጨረፍታ

 

ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ

 ኮተቤ ሜትሮፖሊን ዩኒቨርስቲ

 

ህወሓት የተከበሩ ነገሮችን የማርከስ ክፉ ልክፍት ተጣብቶታል፡፡ ህወሓት በስልጣን ላይ በቆየባቸው ሀያ ሰባት አመታት በርካታ የተከበሩ ዕሴቶችን አቃል፤ ክብራቸውን ቀንል፤ አይነኬ የሆኑ ጉዳችን ደፍል፡፡ ከእነዚህ ጉዳዩች ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉት ናቸው፡፡

ኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያዊነት ለህወሓት ትላቁ በሽታው ነበር፡፡ የነፃነት ተምሳሌት፣ አኩሪ ባህል፤ ቅርስ፤ ስነ-ፅሁፍ፤ እምነት እና ታሪክ ያላትን አገር እና ዜጎቿን ማዋረድ የህወሓት ተቀዳሚ ተግባሩ ነበር፡፡ አገሪቱን በጎሳ ፖለቲካ ከፋፍሎ ለመበተን ያደረገው ሴራ በፈጣሪ ጣልቃ-ገብነት እና በጥቂት ብርቅየ ዜጎቻችን ጥረት ከመበተን ተርፈናል፤ በአገር ውስጥ በዜጎች ላይ ሲደርስ የነበረው ውርደት አላበቃ ብሎ ዜጎች በተሰደዱበት አገር ጠያቂ መንግስት አጥተው ዜጎቻችን በሳውዲ፣ በሊቢያ፣ በግብፅ፣ በታንዛኒያ የደረሰባቸው ግፍ እና በደል የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡

ቋንቋን ፖለቲካዊ ቃና እንዲኖረው ስርዓቱ አበክሮ ሲሰብክ ስለነበር ሁሉም ዜጎች በየ ክልላቸው ተወስነው አንዱ ካንዱ እንዳይግባባ የህወሓት ስርዓት አጥር ነበር፡፡የአማርኛን ቋንቋን መናገር እንደ ነውር፤ በርካታ አገር-በቀል ቋንቋ­‹” SMSÉ እንደ ላቀር አስተሳሰብ እንዲቆጠር ስርዓቱ ተግቶ ሰርቷል፡፡

ኢትዮጲያን እንደ አገር ፀንታ እንድትቆም ካደረጓት ነገርች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ቤተ-እምነቶች ናቸው፡፡ ለዘመናት ተከብረው የኖሩትን ቤተ-እምነቶች የህወሓት ካድሬዎች መነኩሴ፣ መጋቢ፣ ፓስተር እና ኢማም እየመሰሉ የማይደፈሩትን ቦታዎች የደፈሩ የህወሓት ጭፍሮች ናቸው፡፡ አባ ገብረየሱስ ኪዳነ ማርያም ከደረጀ ሃ/ወልድ ጋር በኢሳት ቴሌቪዥን  ጥቅምት 04/2011 ባደረጉት ቃለ-ምልልስ እንደገለፁትኢትዮጲያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን  እየሰለሉ ምንም ስልጣነ-ክህነት ሳይኖራቸው እስከ ጵጵስና ደረጃ የደረሱ ካድሬዎች እንዳሉ  ገልፀዋል፡፡ ይህ ሁኔታ በሌሎችም ቤተ-እምነቶች ውስጥም እንደሚኖር ለመገመት አያዳግትም፡፡

የኢትዮጵያ የከፍተኛ ት/ት ተቋማት ላቅ ያለ ክብር ነበራቸው፡፡ የትምህርት ተቋማቱ አካዳሚክ አቅም ያነገቡ ወጣቶች እና መምህራን የሚገኙበት የምርምር ማዕከላት ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን ከጥራት ይልቅ የቁጥር አባዜ የተጠናወተው ስርዓት ሁሉንም እያግበሰበሰ ዜጎች ሁሉ ድግሪ መያዝ አለባችሁ ተብሎ በአዋጅ የተነገረ እስኪመስል ድረስ ዩኒቨርስቲዎች የገበያ ማዕከል መስለዋል፡፡ በሂደቱም ጥራት የሚባል ነገር ጠፍቶ መምህሩን ከተማሪው ለመለየት አልተቻለም፡፡

በዘመነ አሀ/ስላሴ  እና በደርግ ስርአት የአገር መከላከያ ሰራዊት ጄነራሎች እና የጦር መኮንኖች የትምህርት ዝግጁነታቸው እና ማዕረጋቸው እጅጉን የተከበረ ነበር (ብ/ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ፣ 2000)፣ የጦር መኮንኖች እና ወታደሮች የነበራቸው የውጊያ ብቃት ድንቅ ነበር(ብ/ጄኔራል ተስፋዬ ሀ/ማርያም፣ 1997)፡፡ በዘመነ ህወሓት ግን የጄነራሎች እና የጦር መኮንኖች የትምህርት ዝግጁነታቸው ምን እንደሚመስል የኤርሚያስ ለገሰን መፅሀፍት በማንበብ መረዳት ይቻላል፡፡ በአራተኛ ክፍል የትምህርት ዝግጅት የጄነራልነት ማዕረግ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርል፡፡

መገናኛ ብዙኃን እውነተኛ መረጃን በማቅረብ፣ የወጣቶችን ስብዕና በመቅረፅ፣ ትምህርታዊ እና አዝናኝ ዘገባዎችን በማዘጋጀት ስራ ላይ ሊጠመዱ ይገባ ነበር፤ ዳሩ ግን በዘመነ ህወሓት መገናኛ ብዙኃን የገዥው ፓርቲ ልሳን መሆናቸው ሳያንስ የስርዓቱ የውሸት መፈልፈያ sት እና ዲስኩር የሚነዛበቸው  የፕሮፓጋንዳ ምንጭች ነበሩ፡፡

የኢትዪጲያ አየር መንገድ በአፍሪካም ብሎም በአለም ደረጃ ስመ-ጥር የሆነ እና ሁሉም ኢትዪጲያዊያን ተቀጥረው የሚሰሩበት አገራዊ ክብር ያለው ተsም ነበር፤ ዛሬ ግን ዜጎች በማንነታቸው የሚጠቁበት፤ የአንድ ብሄር የበላይነት የገነነበት ድርጅት ሆኗል (የካፒቴን ሀ/መድህን አበራን፤ የካፒቴን ዮሀንስ ተስፋዩን፤ የታሪኩ አባስ እቴነሽን፣ የወረታው ዋሴን ታሪክ እንዳስረጅነት ማነሳት  በቂ ይመስለኛል)፡፡

አብዛኛዎቹ የህወሓት መሪዎች ወይም የበፊቶች የኢህአዲግ ባለስልጣናት በሚያራምዱት የሌብነት ተምሳሌት፣ የሀሰት ፖሮፓጋንዳ፣  እና በተላበሱት የማጭበርበር ሰብዕና ዜጎች ምን ሊማሩ እንደሚችሉ መገመት አያደግትም፡፡ ‘’ሌብነት ሌባው እስካልተያዘ ድረስ ሙያ ነው’’ የሚል ጠቅላይ ምኒስተር በነበረበት አገር ዜጎች ምን ይማራሉ? ከሞራል እና ከግብረ ገብነት ባህሪያት አንፃር መሪው ከሚመራው ህዝብ ተሽሎ ባልነበረበት አገር፤ ተምሳሌት የሆነ አመራር ጠፍቶበት በነበረበት ምድር፣ ግብረገብነት የተላበሱ ዜጎችን ማፍራት ዳገት ነው የሚሆነው፡፡ ኩሩነት፣ ታታሪነት፣ ታማኝነት፣ ሰውን በሰውነቱ ማክበር፣ የኢትዮጲያን መገለጫ ባህሪያት ነበሩ(ኤፍሬም 1971)፡፡ እነዚህን ባህሪያት በዘመናዊ የትምህርት ስርዓት ማጠናከር ሲገባ የነበረው የህወሓት ስርዓት በየቢሮው ሰራተኛውን አጎብዳጅ፣ ክብሩን በጥቅም የሚለውጥ፣ ሰውን በማንነቱ ሳይሆን በዘውግ የሚፈርጅ፣ ታማኝነት እንደ ጅል እንዲቆጠር በማድረግ የነበረውን የማንነት ዕሴቶች እንዲጠፉ ስርዓቱ አስተዋፅኦ አድርል፡፡ ዜጎች የመንፈስና የሞራል ልዕልናቸው እንዲያሽቆለቁል እና ሕይወታቸው በቅፅታዊ ደስታና ዳንኪራ  እንዲፈዝ ስርዓቱ ጉልህ አስተወፅኦ ነበረው፡፡

እንዚህ ሁሉ ጥላሸት የተቀቡ ክብራችን በዶ/ር አብይ አስተዳደር ለዉጥ እንደሚያሳዩ  ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያዊነት፣ ቤተ-እምነቶች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የኢትዪጲያ አየር መንገድ፣ የአገር መከላከያ ሰራዊት ጄነራሎች እና የጦር መኮንኖች ብቃት፣ መገናኛ ብዙኃን፣ የግብረገብነት ት/ት ወዘተ ወደ ነበሩበት ክብራቸው ይመለሳሉ ብየ አምናለሁ፡፡ ለዚህም የዶ/ር አብይ አስተዳደር ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል፡፡

References

Ephraim Isaac (1971). Social Structure of the Ethiopian Church.   Ethiopian Observer:14(1). Addis Ababa.

ካሳዪ ጨመዳ፣ ብ/ጄኔራል(2000). የጦር ሜዳ ውሎዎች (ግለ-ታሪክ)፡አዲስ አበባ

ተስፋየ ሀ/ማርያም፣ ብ/ጄኔራል (1997). የጦር ሜዳ ውሎ፡ ላብ ደምን ያድናል. አዲስ አበባ

Filed in: Amharic