>
4:42 pm - Tuesday May 17, 2022

ምናልባት በዛው ካሸለብኩ በሚል የተፃፈ ፅሁፍ ( ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ )

ምናልባት በዛው ካሸለብኩ በሚል የተፃፈ ፅሁፍ

 

 ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ
.
እኔ ደራሲ ለመሆን እሞክራለሁ እንጂ ሉሲ አይደለሁም፡፡ ሉሲ መሳሳት አትችልም፡፡ ሉሲ ፈፅሞ ሰው ከሆነች ቆይታለች፡፡ ሰው ሳለች እንጂ አሁን ስህተት ፈፅሞ አይነካትም፡፡ ታድላ! ሉሲ ናት እንዳረጋችሁዋት የምትሆነው፡፡ አሜሪካንም ኢትዮጵያንም አታውቅም ሉሲ፡፡ እንደምትፈልጉት ሳይሆን እንደምፈልገው ተራምጄ ለሞት ጭንቅላት መስጠቴ ቢያሳዝንም፣ አያሳዝንም፡፡

እናንተም ፀጉር ያብቅል እንጂ መጀመሪያ ጭንቅላታችሁ ነው የሚሞተው፡፡ እንዲያውም አሁንስ አለን? ሳትሉ አልቀራችሁም፡፡ እኔ በግማሽ ጭንቅላቴ የምበልጠው ሚኒስትር እንደሞላ ሁላ፡፡ እኔ ወደ ህክምና ልሄድ ስለሆነ፣ ያጠፋሁ የመሰላችሁ ይቅርታችሁን አትከልክሉኝ፡፡ በዛው ካሸለብኩ ማለቴ ነው፡፡ ግን ከዳንኩ እናንተን አያድርገኝ፡፡ በከንቱ የሰደባችሁኝ ሁላ ቀናችሁን ጠብቁ፡፡ እኔ ልዳን ብቻ፡፡ ጠላቶቼ ሆይ፣ የእናንተ መኖር ነው እንድድን የሚያደርገኝ፡፡ እንጂ ይህን ሁሉ ብር በሆስፒታሉ አካውንት አላስገባም ነበር፡፡

ክቡራንና ክቡራት፣ (ሁሉንም ማለቴ ሳይሆን) ራሱ ሐኪም፣ ራሱ ታማሚ፣ ከሆነው ሐበሻ ውስጥ እኔን አይቶኝ የማያውቀው ሁሉ ብዙ ነገር ተብላችሁዋል፡፡ እኔን መታመሙ ሳይሆን የጎዳኝ፣ ባላየው ባልሰማው ነገር አሳፋሪው የሐበሻ ሐሜት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እኔን ጨምሮ ለሐሜት እንፈጥናለን፡፡ እኔን ጨምሮ፡፡ የምን አዙሪት እንደሞላን አላውቅም፡፡ …ባጭሩ፣ ሳታጣሩ አትዋጡ፡፡
እንዳትፅፍ ተብዬ ነበር በወዳጆቼ፤ “ዝም በል፣ አይመጥንህም”… ልክ ናቸው፡፡ ግን…መፃፍ አማረኝ- በአንድ ነገር ብቻ፡፡ ያዘጋጀሁት ሆስፒታሉ ፈቃድ እንደሰጠኝ ነው፡፡

አሁን አይደለም፡፡ ጭንቅላቴ ስለሚከፈት፣ በዛው ካሸለብኩ ብዬ ነው ይህንም የምፅፈው፡፡ ባሸልብም ችግር የለም፡፡ እውነቱን ጫፉን አስያዝኳችሁ፡፡ እናንተው ትሞሉታላችሁ፡፡ በሐሜታችሁ ማለቴ ነው፡፡ እስከ አሁን ከ13 መፃህፍት በላይ ሰርቻለሁ፡፡


በዛም ላይ ማንም የማይክደው ፅኑ ተማሪ ነበርኩ፡፡ ማስተርሴን ጨርሼ፣ Phd ተመዝግቤአለሁ፡፡ የወጣትነት
ጊዜዬን ፈጣሪን አጥብቆ በማዎቅና በፈጠራ አሳልፌአለሁ፡፡ አይበቃም ግን ይበቃል፡፡ ዴርቶጋዳ 6 ጊዜ በአሳታሚ (ስለፈሩ) እንደተመለሰ ከእኔ በላይ ማንም አያውቅም፡፡ በነፃ እንኳን እንዲያትሙትና ለህዝቡ አምስት ኮፒ እንኳ ያንብብ ብልም አስቤዛ የለኝም፡፡ ግን አንዴ ከታተመ በሁዋላ ያያችሁት ነው፡፡ በዛ አስፈሪ ወቅት ኢትዮጵያን አንድ ሁና ማየት የማይፈልጉ ሰዎች ነበሩ፡፡

አሁንም የዘር ጥላቻ ሳያንገፈግፋቸው አንገፍግፏቸው ብሶባቸዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች 100 አይሞሉም፡፡ ዴርቶጋዳ የታተመበትን ወቅት ታስታውሳላችሁ ከ10 አመታት በፊት፡፡ በድርሰት ገንዘብ ተበልቶበት አይታወቅም፡፡ የእኔ ሳይሆን፣ ዴርቶጋዳም የአሳታሚ ሲሳይ ሆኖ ቀርቷል፡፡ ክሱ ነው የተረፈኝ፡፡ ለአንተ የተወረወረብህን ድንጋይ እንዲሉ… ከክሱም ተምሬአለሁ፡፡ ሆኖም እኔም ሌሎችን ሥራዬን እንድሰራ በሩን አጥብቆ ከፍቶልኛል፡፡ ዴርቶጋዳ ከታተመ በሁዋላ ለሀገሬ መሥራቱን ቀጥየበታለሁ፡፡ መኪና እስኪድጠኝ ድረስ፡፡ አሁንም ተነስ ተነስ ፃፍ ፃፍ የሚለኝ መልአክ ይመጣል፡፡ ይህችም ወቀሳ እና ምስጋና ከተጀመረች በወሯ ነው የደረሰችው፡፡


በዛምበዛም ላይ ሳላዛንፍ በቀን ሶስት ጊዜ (ለሁለት አመታት) የምወስደው መድኃኒት አለ፡፡ እንደበሽተኛ ራሴን መድኃኒት በዋጥኩ ቁጥር እቆጥራለሁ፡፡ በአሳለኝ ቁጥር እናቴ በርራ ትመጣለች- የጣለኝ እየመሰላት፡፡ የሆነው ሆኖ ሰዎችን ማሳመን አለብኝ ብየ (በአንደበቴ) ተስፋም አደርጋለሁ፡፡ አንደበት ዋጋ እንዳለው አሁን ነው የተረዳሁት፡፡ ብስጭትን መግለፅ በቃላት ከፍ ዝቅ አድርጎ እንዴት ይናፍቃል? … የምልክት ቋንቋም ለመማር ራሴን እያዘጋጀሁ ነው፡፡ ማየት ለተሳናቸውም የብሬል ፅሁፍ፡፡

ህክምና እንዳገኝ የእኔን ሁኔታ የሚከታተሉ ዶክተሮች ብዙ ጥረዋል፡፡ በፌስ ቡክ አትፃፍ ይሉኛል፡፡ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የሚሰጡትን የሐበሻን ሐሜት እነሱም እየገረማቸው ያነቡታል፡፡ አንድም መረጃ የሌለውና ከጠላቶቼ የሚሰነዘር ጥቃት መሆኑን ስለሚያውቁ፣ እና እኔን ከአለም ለማጥፋት ሆነው በገፍ በጀት የተበጀተላቸው ሰዎች የቅርብም የሩቅም ሰወች ስለሆኑ ችግር የለም፡፡ እኔ ልዳን እንጂ ወይም ያሳሳቱትን ህዝብ ፊት ይቅርታ እንዲጠይቁ አደርጋለሁ፡፡

አሁንም ጥቅም የገዛቸው ሰዎች እኔ (በህክምናዬ ወቅት ከሞትኩ) ሞቼም ቢሆን ህዝብን ይቅርታ መጠየቅ
አለባቸው፡፡ አለበለዚያ ህሊናቸው አያስተኛቸውም፡፡ ሲቆጠቁጣቸው ይኖራል፡፡ ወይም አንድ ቀን እውነቱ
ይወጣል፡፡ አንዷ ይቅርታ ልትጠይቀኝ መጣች፡፡ እኔ ግን ህዝቡን በተመሳሳይ ሚዲያ ይቅርታ ጠይቂ እኔ እውነቱን አውቀዋለሁ፡፡ እስካሁን አልጠየቀችም ብየ አስባለሁ፡፡

እኔም በህግ ጠይቄ ፖሊስ አጣርቶ ለአቃቤ ህግ አቅርቧል፡፡ የእኔ ህክምና የሚደረገው ጀርመን ሀገር ውስጥ ነው፡፡ ሁሉም አልቋል፡፡ በህይዎት ከተመለስኩ ብዙ ገመናቸውን አወጣለሁ፡፡ ለምን? ማስተማሪያ ይሆናል፡፡ ሀገር ትከዳለህ የሚል ጣጣ መጥቷል አሁን ደግሞ፡፡ እነሱ ሀገራቸውን ሀገራቸው ውስጥ ሆነው መረጃ አሳልፈው እየሰጡ፡፡ ለምሳሌ ለአንድ የኬንያ ሰው የምትናገሩትን ታውቃላችሁ?

ለምሳሌ ለሶማሊያስ? ለሱዳንስ? ለግብፅስ? ይህን እኔ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ እንዲያውም ስለ ሀገራዊ ምስጢሮች
የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ቢያወያዩ ጥሩ ነበር፡፡ ብትከፋም ብትበጅም አንዲት እናት ሀገር አለችን፡፡ እኔ ለመቀበሪያ ነው የምፈልጋት፡፡ እንኳን አሁን ሀገሬን ልከዳ ስፈታ ስታሰር ዱሮም አላረኩትም፡፡ ስፈታ ስታሰርም እንደ አንዳንዶቹ ማንም የእኔን መታሰር መፈታት፣ አጠገቤ ካሉ ሰዎች እንጂ ብዙዎቹ አያውቁም (በመለስ አባባል ለማስታወቂያ አላዋልኩትም)፡፡ ፎቶዬ ይወጣል ብዬ በመፍራት፡፡ እኔ እንደደራሲ ስለሚቃጣኝ ወደ ህዝቡ መመልከት እንጂ እኔን ህዝቡ ከተመለከተኝ ምኑን ደራሲ ሆንኩት? ደራሲ እንጂ ሉሲ አይደለሁም፡፡እስከ ቅርብ ጊዜው ሰይፉ ሾው ላይ አስከምታይ ማንም በእኔ ላይ ትኩረት አልነበረውም፡፡ የሚያውቁኝ ሰዎችም ለሌላ ሰው ሲያስተዋውቁኝ ደስ አይለኝም ነበር፡፡

ወደ ህመሜ ልመለስ፡፡ ይሁንና እድሜ ለጥቁር አንበሳው ለዶክተር ዘላለም ጥላሁን እና ጀርመን ውስጥ ከሚገኙ
ኢትዮጵያውያን ዶክተሮች ጋር በመመካከር፣ እስካሁን የእኔን ጤና ሁኔታ ጥቁር አንበሳ ከሚገኝ ዶክመንቴ ላይ
በማስረዳት፣ ህመሜን እስካሁን ድረስ የታከምኩበትን ማስረጃ ተልኮ፣ MRI፣ በተለያዩ ሆስፒታሎች
የተነሳሁዋቸው 4 CT Scan፣ ሁሉም ተመርምሮ ጠርተውኛል፡፡ ለእኔም አስር ዶክተሮች ተመድበዋል፡፡ ሀገሬ
እንደዚህ ብትሆን ስል መንፈሳዊ ቅናት ቀናሁባቸው፡፡ በቀንስ አልቀንስም ለዚህ ዶ/ር ዘላለም ጥላሁን እንደኔ
ታሞ ከጥቁር አንበሳ እኔን ለማሳከም የለፋውን ልፋት በእንባም አይገለፅም፡፡ አንዳንዶችን ለመግለፅ ያክል
ሀገራቱን በዝርዝር… አሜሪካ፣ .ቱርክ.ጀርመን: ሁለት ቦታዎች ነው የተገኙት .እስራኤል፣ እስራኤል ውስጥ ያለው አርያን ሻሮን የታከሙበት በጤና ጥበቃ ውስጥ ያለ ነው፣ እስካሁን (እድሜውን ያሳጥረውና በገንዘብ እጥረት እስካሁን የዘገየውን የእኔን ህክምና) መረጃ በጥቂቱ አያይዣለሁ፡፡የባህርዳር ልጆች፣ ጎንደሬዎች ያዋጡት
ገንዘብ ሳይሆን እኔን እስከመፈዎስ ተቃርበዋል፡፡ እኔም እነሱን በጣም አመሰግናቸዋሁ፡፡ እነሱ አለሁ  በማለታቸው ሳይሻለኝ ተሽሎኛል፡፡ ጀርመን በሯን ከፈተችልኝ፡፡ ቀንሰዋል፡፡ የጭንቅላት ጉዳይ ጭንቅ ያስይዛል፡፡ እኔም ድሮ (እኔም ዱሮ አለኝ) የጤና ባለሙያ በመሆኔ የሚያደርጉልኝን አኒሜሽን በጥቂቱ ላሳያችሁ፡፡

 

Filed in: Amharic