>

ደብረጽዮን  እራሱ የጌታቸዉ አሰፋ እስረኛ ነዉ!!!  (ሚኪ አምሀራ)

ደብረጽዮን  እራሱ የጌታቸዉ አሰፋ እስረኛ ነዉ!!!
 ሚኪ አምሀራ
ጌታቸዉ እና አክቲቪስቶች የሚጫወቱበት የክልል መሪ ቢኖር ይሄ ሰዉየ ነዉ፡፡ ደግሞ እኮ በግልጽ ደካማ ነህ አትመራንም እያሉ እየነገሩ ነዉ፡፡ ያዉ ያችን የቴሌ ካርድ ሳበበት ዛሬ ደግሞ ሌላ መግለጫ ይዞ መጣ፡፡ በቀደም ያሸነፋቸዉ መስሎ ነበር፡፡ በፊት የገንዘብ ነክ ሙስና የሚመረመረዉ በደህንነቱ በኩል ነበር ጌታቸዉ ደግሞ ይሄ መረጃ አለዉ፡፡ አሁን ከወረድንም አብረን ነዉ የምንወርደዉ የሚለዉም ለዛም ነዉ፡፡ አባይ ግድብ፤ መብራት ሃይል እና ቴሌ ቢመረመሩ ደብረጺዎን ከሰራዉ አንጻር ክንፈ ዳኛዉ ነጻ መዉጣት ይችላል፡፡
ህወሃት ብቻዉን መንግስት ሁኖ የቆየ ድርጅት ነዉ፡፡ አሁን ተሸንፏል፡፡የተሸነፈ ቡድን ደግሞ አሁንም እንደመንግስት ሁኖ መቀጠል የለበትም ይልቁን ሙሉ ለሙሉ ተማርኮ ለፍርድ መቅረብ ነዉ ያለበት፡፡መንግስት ሆኖ የቆየ ቡድን መንግስትነቱን በህዝብ ጉልበት ካጣ በኋላ ቀጥታ መደረግ ያለበት ያለዉ የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካ እና የጸጥታ ሃይል እና ሃብት ማድቀቅ ነዉ፡፡ አለበለዚያ ያሸነፈዉን ህዝብ ይበቀላል ለህዝብ ደህንነትም አስጊ ሆኖ ይቀጥላል፡፡በፖለቲካዉ ሙሉ ለሙሉ ተሸንፎ አሁን ሚንገዳገደዉ በዘረፈዉ ሃብት ነዉ፡፡
እራሱ ክንፈ ዳኛዉ ወንጀለኛ መሆኑን አዉቆ አገር ጥሎ ሊሸሽ ሲል በወጣቶች የተያዘ ሰዉ ነዉ፡፡ እና እጁ በካቴና መታሰር አልነበረበትም ይላል እንዴ፡፡በለንቋጣ ልጥ እጅ እና እግሩን ገንዞ ነበር እንዲያዉም ማቅረብ፡፡ ካቴና እማ ወግ ነዉ፡፡ደግሞ እኮ የወሰዱት በሄሊኮፍተር ነዉ፡፡ ሁለት ቀን በአይስዙ ከእቃ በላይ ጭኖ ነፋስ እያስመቱ አዲስ እንዲደርስ ነበር ማድረግ ።
ሰዉም ድርጅትም ዛፍም ይበሰብሳል እንደ ወያኔ ግን የበሰበሰ እና ከጥቅም ዉጭ የሆነ አይቸ አላዉቅም፡፡ እኔ እኮ አሁን ሃፍረት እየተሰማኝ ያለዉ እንዴት ይሄ ብስባሽ 27 አመት እንደገዛን ነዉ፡፡ በጣም ከማፈሬ የተነሳ 27 አመት ሚለዉን ለመጥራት እራሱ እሳቀቃለዉ፡፡ አንድም እዉቀት ያለዉ፤ ፖለቲካዉን የሚያዉቅ ሰዉ የላቸዉም፡፡ ያነጹት ትዉልድ በሙስና ብር የተጀቦነ እንጅ እዉቀት እና ክህሎት የቀሰመ አይደለም፡፡ ከአዲስ 22 እስከ ታይላንድ ድረስ መጠጥ እና ብልግና ሲማሩ የኖሩ ናቸዉ፡፡ አሁን ምኑን ከምን ያድርጉት፡፡
+++++++++++++++++++++++++++
እስራኤልን ከህወሃት ጋር ለማስተሳሰር መሞክሩ  የቀጠናዉን ጂኦ ፖለቲክስ አለማወቅ ነዉ!!!
ሚኪ አምሀራ
 ሰሞኑን እንደምንም ብለዉ የሆነ የእስራኤል ድርጅት የሚያግዘዉ የእርሻ ቦታ አለ እሱን ለማስመረቅ ብለዉ የእስራኤልን አምባሳደር ወደ ትግራይ ጠርተዉ ነበር፡፡ እናም ከዚህ ጋር አያይዘዉ እስራኤልን ከህወሃት ጋር ለማስተሳሰር ሲሞክሩ ታያላችሁ፡፡ ለምሳሌ ጌታቸዉ አሰፋ ወደ እስራል አቀና፤ ከሞሳድ ጋር ይሰራል ምናምን እያሉ ይጽፋሉ፡፡ ዶ/ር አብይ ከአረቦች ጋር እየሰራ ስለሆን እስራኤልን እኛ እንያዝ ማለታቸዉ ነገር ነዉ፡፡ ይህ የቀጠናዉን ጂኦ ፖለቲክስ አለማወቅ ነዉ፡፡ እነ እስራል እና ሳዉዲ አረቢያ የቀረበ ግንኙነት ነዉ ያላቸዉ፡፡ በገሃድ አያዉጡት እንጅ የቱረክ ኢራን-ኳታር ቡድንን ለመምታት እስራኤሎች ከግብጽ ሳዉዲ ጎን ሁነዉ ነዉ እየሰሩ ያሉት፡፡ አሁን አሁን እንዲያዉም በግልጽ የወጣ ነገር ነዉ፡፡ እስራኤል ቱርክ እና ኳታርን ከምስራቅ አፍሪካ ነቅለዉ እንዲወጡ አድርጋለች፡፡ ይህ የሚገባዉ የህወሃት ሰዉም ሆነ ትዉለድ የለም፡፡ በስብሰዋል፡፡ አልበሽር ነዉ የቀረዉ እሱንም በቅርቡ ታጡታላችሁ፡፡ ጂኦ ፖለቲክሱ ይሄዉ ነዉ፡፡ በነገራችን ላይ ስለ አካባቢያዊ ፖለቲካ ቱቶሪያል መዉሰድ ከፈለጉ መስጠት እንችላለን፡፡
እስራኤል አምባሳደር ሁኖ ሚሰራዉ አለቃ ጸጋየ ነዉ፡፡ እሱም ነገር ለማወሳወስ ሞክሯል፡፡ ችግሩ በምን ቋንቋ ይግባባል፡፡ ሃሳብስ የት አግኝቶ፡፡ ለዛ ነዉ ዝም የተባለዉ፡፡
Filed in: Amharic