>
8:32 am - Tuesday December 6, 2022

ስትፈልግ የትግራይ ክልል ትገነጠላለች እንጂ!  ተመልሰን በህወሓት እጅስ አንወድቅም!!! (ዳንኤል ሺበሺ)

ስትፈልግ የትግራይ ክልል ትገነጠላለች እንጂ!  ተመልሰን በህወሓት እጅስ አንወድቅም!!!
ዳንኤል ሺበሺ
 
* ግብረ ሰዶምን በሀገራችን ልጆቻቸው ሲያስፋፋብን፣ እግር ሲቆርጡ ፣ ፅንስ ሲያጨናግፋ ፣በኤሌክትሪክ ጡት ሲተለትሉ ፣ ያለ አግባብ ሲያስሩና ሲከሱ፣ አካለ ጎደሎ ሲያደርጉ ለምን አላወገዙም ?ሊቁ መምህር አግማሴ በመቀሌ ከመሬት ውስጥ ታስረው ህዝብ እየጮኸ ለምን ይፈቱልን አላሉም ? ዛሬ ግን ሌባ ታሰረብን የዘረፋ ሌቦች እንዳይታሰሩብን ሲሉ ሰልፍ መውጣት ነውር ነው!!!
የሰሞኑ ትግራይ ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ነገር 2000 ዓም’ን አስታወሰኝ ፡፡ የትግራይ ሕዝብ ከ1983 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ምድር ኢትዮጵያውያን የሚያካሂዱትን የፍትህ፣ የዴሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ/ትግል ለምን አያግዙም? ወይም ለምን አይቀላቀሉም? ደርግን የሚያህል ኃያል ታግዬ ጥያለሁ ለሚል ሕዝብ ህወሓት እንዴት ይከብደዋል? 
ያ ሁሉ ሰቀቀን ሲሰማ ለምን ሰልፍ አልወጡም ..ግብረ ሰዶምን በሀገራችን ልጆቻቸው ሲያስፋፋብን፣ እግር ሲቆርጡ ፣ ፅንስ ሲያጨናግፋ ፣ ያለ አግባብ ሲያስሩና ሲከሱ፣ አካለ ጎደሎ ሲያደርጉ ለምን አላወገዙም ?ሊቁ መምህር አግማሴ በመቀሌ ከመሬት ውስጥ ታስረው ህዝብ እየጮኸ ለእነሱም ለልጆቻቸውን እንደማይበጅ አውቀው ለምን ይፈቱልን አላሉም ? ዛሬ ግን ሌባ ታሰረብን የዘረፋ ሌቦች እንዳይታሰሩብን ሲሉ ሰልፍ መውጣት ነውር ነው ::
እነሱ ከታሰሩ ወደ ደደቢት እንሄዳለን እያሉ ነው :: እንደገባችሁ ደውሉልን እዛው እንገናኛለን :: ፍቅር እንጂ የሚያስፈራው ፀብማ መቼ ይፈራና የተሸከምነው ያሳቀፋችሁንን ትኩስ እሳት መትፊያ እናገኝ ነበር ያኔ ምርቱና ገለባው ይለያል :: በግፍ የፈሰሰው ደም መልስ ያገኛል ነበር።
ህወሀቶች  በታሪክ አጋጣሚ ዘለግ ያለ የመንግሥት ሥልጣንን የተቆጣጠሩት ይነገር ከተባለ የልጆቻቸው መንግሥት ተብሎ ይጠራል ፡፡ ክፋቱ ከአንድ መንደር መውረራቸው ሳይሆን ለሰው ልጅ የሚገባውን ፍትህ አለማስፈናቸው ነው ፡፡ በንጽጽር ይነገር ከተባለ ደሞ ከሙስና ውጭ ከደርግም የከፋ አረመኔ ነበሩ፡፡ ደርጎች ከሰማያዊዋ ካኪ ውጭ ሌላ ሀብት ብዙም የማይታይባቸው በሙስናና በሌብነት እምበዛም የማይታሙ ስለሆነ፡፡
እናም በደርግ ዘመን ከባዱን ቀንበር የተሸከመው ያ! ሕዝብ ዛሬም ተመሳሳይ ዋጋ እንዲከፍል መጋበዙ እንደ ሰውኛ ይከብደኛል የሚለውንና የሚያውቁት ጓዳ ስለሆነ አፈናው ከሌላው ክልል ትንሽ ከበድ ማለቱ አይቀርም ብዬ አለፍኩኝ ፡፡ ቀጠልኩና የትግራይ ሕዝብ #ጥፋቱ እንደ ሕዝብ ለወንበዴ ልጆቻቸው ፍጹም ዋሻ መሆኑ ነው ብዬ ነበር ሀሳቤን ያጠቃለልኩት፡፡
ሕዝቡ በህወሓት አገዛዝ ተጠቃሚ ሆኖ ሳለ እኛ ተሸውደን ነው ብዙ ብዙ ስንል የነበርነው? ላለፉት ለ27-ዓመታት ወደ ገበያ፣ ወደ ቤተስኪያን፣ ለመንግሥታዊና ለሌሎች ማኀበራዊ ጉዳዮች ካልሆነ በስተቀር ከቤቱ ወጥቶ የማያውቅ ሕዝብ (ድርጊቱንና ሥርዓቱን የምር የሚታገሉ/የሚቃወሙ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች እንዳለ ሆኖ) ምነው ዛሬ አመረሩሳ? ይሄ የጤና ነው ወይስ ዛሬም ዋሻ ለመሆን ነው ?
ነገ በምህረት ፣ በይቅርታ፣ በዋስትና መብት፣ ተከራክረው የመርታት ዕድል እያላቸው እንደ ትላንትናው ዛሬም ለተጠሪጣሪን እስከ አደባባይ ሰልፍ መውጣትና ዋሻ የመሆኑ ምስጥር እኔን ጨምሮ ለብዞዎቻችን አሁን ተገለጠልን ፡፡
በመጨረሻም ስትፈልግ የትግራይ ክልል ትገነጠላለች እንጂ! እናንተ (ሰልፈኞቹ) በደርግ ዘመን ከከፈላችሁት በበብዙ እጥፍ የሚበልጥ ዋጋ ከፍለን እናንተ የተከፋችሁበትን ለውጥ አምጥተናል፡፡ ከዚህ በኀላ ወደኋላ ተመልሰን በህወሓት እጅ አንወድቅም!!!
Filed in: Amharic