>
6:17 am - Wednesday December 7, 2022

ለመሆኑ ይህ ሁሉ ሰልፈኛ ሚልዮኖች ሲፈናቀሉ፣ ሲገደሉ አገር ስትዘረፍ የት ነበር!!! (ሉሉ ከበደ)

ለመሆኑ ይህ ሁሉ ሰልፈኛ ሚልዮኖች ሲፈናቀሉ፣ ሲገደሉ አገር ስትዘረፍ የት ነበር!!!
ሉሉ ከበደ
 
የትግራይ ህዝብ ሌቦችን ይደግፋል ብየ አላምንም። እርግጥ ህዝብን ማሳሳት ይቻላል። ሂትለት የጀርመንን ህዝብ አሳስቶ “ከሰው ልጅ ዘር ምርጥ እኛ ነን ” ብሎ እንዲያስብና በሰባዊ ፍጡር ላይ ላደረሰው የግፍ ግፍ ተግባር  ተባባሪ እንዲሆን አድርጎታል። ለስድስት ሚሊዮን አይሁዳውያን እልቂት ምክንያት አድርጎታል!!
የትግራይ ሰልፍ። በህውሀት የሸፍጥ ፖለቲካ ባህልና ልምድ መሰረት፤ ድርጅታዊ አሰራር ፤ እያንዳንዱ የቀበሌ ካድሬ አታሎም ይሁን አስፈራርቶ ወይም አስገድዶ፤   ያስፈልጋል በተባለ ወቅት ላይ ህዝብን አደባባይ ማውጣት የተለመደ ተግባር ነው።በዚያ መልኩ ይመስለኛል ህዝቡ ተነቅሎ የወጣው። የትግራይ ህዝብ ሌቦችን ይደግፋል ብየ አላምንም። እርግጥ ህዝብን ማሳሳት ይቻላል። ሂትለት የጀርመንን ህዝብ አሳስቶ “ከሰው ልጅ ዘር ምርጥ እኛ ነን ” ብሎ እንዲያስብና በሰባዊ ፍጡር ላይ ላደረሰው የግፍ ግፍ ተግባር  ተባባሪ እንዲሆን አድርጎታል።ለስድስት ሚሊዮን አይሁዳውያን እልቂት ምክንያት አድርጎታል ።
በሌላ በኩል ደግሞ በአንድ አገር ውስጥ አንድ የተወሰነ ክፍለ ህዝብ እንዳለ ፤ ራሱን እንደገዢ መደብ አድርጎ ከቆጠረ፤ አውቆም ይሁን ሳያውቀው ይህን አይነት ስነልቡና ካዳበረ፤  በልጅም ባዋቂም አእምሮ ውስጥ ያ ነገር ካለ አደገኛ ነው። ለምሳኔ እንደሩዋንዳ ቱትሲዎች አይነት። የትግራይ ህዝብ ግን እዚያ ደረጃ የደረሰ አይመስለኝም ህውሀት ቢመኝም ቢጥርም።
አሁን ለጊዜው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሌቦች መካከል የሌላው ብሄረሰብ አባላትም አሉ። ማን እነሱን ሊደግፍ ሰልፍ ወጣ? ህውሀት በሌሎችም ክልሎች ተመሳስይ ሰልፍ በሀብቱ በብልሀቱ  ያደራጅ ይሆን? መቸም አያልቅበት። ገና ምን ተነክቶ? የኢትዮጵያ ህዝብ ህይወቱንም ንብረቱንም ሀብቱንም የመንግስትነት ቅርጽ ባለው ግዙፍ አደረጃጀት በህውሀት ሲዘረፍ ኖሯል።
የተዘረፈው ፤ ወደትግራይ የተጋዘው የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት ነው። ከምናውቃቸው  ጥቂት ጉዳቶቻችን :-
. አስር ሺህ ቶን ቡና ተሰረቀ
. አስርሺህ ቶን አሸዋ ስኳር ተብሎ ከህንድ ሀገር መጣ
. የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት የሆኑ መርከቦች አውሮፕላኖች ስምና ባንዲራ ተለውጦላቸው የህውሀት  መነገጃ ሆኑ
. በአመት ሶስት ቢሊዮን ዶላር ከሀገር ኢትዮያ ይወጣል፤
. ይህን ያህል መሬት ተቆርጦ ለሱዳን ተሰጠ ወዘተ… ተዘርዝሮ የማያልቅ የተደራጀ ሌብነት ። የትግሬው ነጻ አውጪ የሚፈጽማቸው የፈጸማቸው።
ምናልባትም በአለም ላይ መንግስት በዜጎቹ ላይ የፈጸመው ወንጀል ግዝፈት ማሳያ ሊሆን ይችላል ፤ በኦጋዴን በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሶማሌዎች ወገኖቻችን ተገድለው የተቀበሩባቸው የጅምላ መቃብሮች መኖራቸው ተረጋግጧል።
የዚያ ወንጀል ፈጻሚና አስፈጻሚ የህውሀት ጀነራሎችና አብዲ ኢሌ መሆናቸው ማንንም አያጠራጥርም። በወልቃይት ጠገዴና ወያኔ ወደትግራይ ካጠቃለላቸው የክፍለሀገር መሬቶች በተለይም በአማራ ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል ተፈጽሟል።
የትግራይ ወንበዴዎች ከፍትህ የሚያመልጡበት አንዳችም ብልሀት  አንዳችም አቅጣጫ ሊኖር አይገባም። ህዝብን አነሳሥቶ ሰላማዊ ሰልፍ በማስወጣት የሚፋቅ ወንጀል የለም።
ህውሀት ህዝቡን ብሄር ተኮር ጥቃት በተደራጀ መልኩ ደረሰብን የሚል መፈክርም አሸክሞ ነበር። ማነው የዚህ አይነት ድርጊት ባለሙያና ኤክስፐርት ? ተደራጅቶ ተቀናጅቶ ብሄርን ማጥቃትና ነጣጥሎ መምታት የህውሀት የእድሜልክ ስራ አይደለምን? ማንን ነው ለማደናገር የሚሞክሩት? አማራውን እየገደለ  የዘር ማጽዳት ያካሄደበት ማነው? ኦሮሞን በሚሊዮን እንዲፈናቀል በአስርሺ እንዲሞት ያደረገው ማነው? ሶማሌን ባስርሺ ጅምላ መቃብር የከተተው አቀናባሪ ሰሪ  ማነው? አራት መቶ በላይ አኟኮችችን ባንድቀን ጀምበር የረሸነው ማነው? ይህን ሁሉ እድፍ የተሸከመ ህውሀት የትግራይን ህዝብ አፍኖ ይዞ በግድም በሸፍጥም ሰልፍ እያስወጣ ሀያሰባት አመት ከፈጸመው ወንጀል ሊያመልጥ አይችልም።
ብቻውን አይደለም የሚጠየቀው በየክልሉ ያሰማራቸው ተላላኪዎቹ ሁሉ የትም አያመልጡም። ይለቀማሉ ከየወንዙ ከየቤቱ ገና ተጀመረ እንጂ መች አለቀ?
ትዝብት፤ ሀያሰባት አመታት ያሁሉ ደም በህውሀት ታጣቂዎች ሲፈስና አናት በልጇ ሬሳ ላይ ተቀምጣ አፏን እንድትዘጋ ሲደረግ፤  ታዳጊ ወጣቶች ዲሞክራሲ ያስፈልገናል ፤ የስር አት ለውጥ ያስፈልገናል በማለታቸው ብቻ ወያኔ በሚያዘው ሰራዊት ሲጨፈጨፉ ፤ በሀገሪቱ ሁሉም ማዘን ህዝብ ተነቃንቆ ሲቃወም ትግራይ ሰላም ነበር።  ሌባ መታደን ሲጀመር ሰልፉ ለምን?
Filed in: Amharic