>

የዜጎቻችን ደምና ስቃይ አሁንም ትጮሀላች ፍትህ ፍትህ!!! (ሀብታሙ አያሌው)

የዜጎቻችን ደምና ስቃይ አሁንም ትጮሀላች ፍትህ ፍትህ!!!
 ሀብታሙ አያሌው
በደቡብ ክልል የተፈፀሙ ወንጀሎችና ኢሰብአዊ ድርጊቶች፡-  በዜጎች ላይ ከፍተኛ ሰባዊ መብት ጥሰት ከፈጸሙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ የቀድሞ የደቡብ ክልል ፕሬዝደንት እና ተባባሪዎች ዋነኛዉ ሲሆን በዝርዝር የተወሰኑትን እነሆ፡-
1. በ1994ዓ.ም የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄን መነሻ አድርገዉ ራሳቸዉን በራሳቸዉ ለማስተዳደር በተነሳዉ የህዝብ ህገ መንግሥታዊ ንቅናቄ በተለምዶ የሎቄ ጅምላ ጭፍጨፋ በርካቶች በጠራራ ጸሀይ ደማቸዉ እንዲፈስ ሆኗል፡፡(https://kichuu.com/shiferaw-shigutes-crimes-sidama/) ፡፡
2. በጉራፈርዳ ወረዳ ይኖሩ የነበሩ ሺዎችን ህጻናት፣ እናቶችንና አርሶ አደሮችን ዜጎቻችን አማራ ስለሆኑ ብቻ ከገዛ ሀገራቸዉ እንዲፈናቀሉ በማድረግ ለስቃይ ለሞትና እንግልት የዳረገ ፕሬዝደንት ሆኖ ቀጥታ አመራር የሰጠ ይህንንም በሚድያ መግለጫ የሰጠ ማፊያ ነበር (https://ecadforum.com/blog/ethiopia-gura-ferda-and-crimes-against-humanity/) ፡፡
3. በ2010 ዓ.ም በሰኔ ወር ከሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ በአል ጋር አያይዘዉ ሁከትና ግጭት በማስነሳት በሀዋሳና ሲዳማ ዞን ዉስጥ ባሉ ወረዳዎችና ከተሞች በርካታ የወላይታ ብሄር ተወላጅ በሆኑት ላይ በኢትዮጵያ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አሰቃቂ ግድያ፣ሬሳ ማቃጠል፣ቀጥቅጦ በዱላ መግደል፣እናቶችንና ህጻናትን እንድደፈሩ፣ሀብት ንብረታቸዉ እንዲዘረፍ ቤታቸዉ እንዲቃጠል ያስደረገ ሲሆን በዚህ ግዜ የፓርቲዉ ሊቀ መንበር ሆኖ በክልል በነበሩ አባሪዎች በዋናነት፡- አቶ ደሴ ዳልኬ (የክልል ፕሬዝድንት)፣ቴዎድሮስ ገቢባ (ሀዋሳ ከተማ ከንቲባ)፣ አቶ አክልሉ አዱላ (የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ)፣ አቶ አያኖ በሪሶ (ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት) ሲሆኑ ለ27 አመት የወያኔ ተላላኪ የነበሩ አሁን በክልል እንሁን ጥያቄ ሽፋን ከባድ የሰባዊ መብት ጥሰት እንዲፈጸም ያቀናበሩ ናቸዉ፡፡ በቅርቡ የክስ መዝገብ በተወሰኑት ላይ ተጀምሮ የተዳፈነ መሆኑን እናስታዉሳለን፡፡ ፍትህ የዜጎቻችን ደምና ስቃይ አሁንም ትጮሀላች ፍትህ ፍትህ! የዘገየ ፍትህ እንደተነፈገ ይቆጠራልና!    (https://www.thereporterethiopia.com/article/ag-indicts-former-hawassa-mayor-over-conflict/)
በርካታ ሌሎች ህዝቦች ላይም የዝርፊያና የዛቻ ወንጀሎች ተፈጽመዋል በለኩ ከተማ በርካታ ጉራጌዎች፣ሥልጤዎች፣ንብረታቸዉ ወድሟል ተዘርፏል፡፡ ፍትህ በጋራ ትግላችን አንድ ቀን በቅርቡ ትፈርዳለች! አሁን በሜቴክና በደህንነት ሀላፊዎች የተጀመረዉ ወረበሎቹንና ወንጀለኞቹን የመያዝና ህግንና ፍትህን የማስከበር ሥራ ወደ ደቡብ መምጫዉ ጊዜ ነዉ፡፡ እንደ ጎርፍ የፈሰሰዉ ደም ይጮሀል በላይ በሰማይ!!!!!!
በተለይም በሀዋሳ ወይን ቤት (እስር ቤት) የተፈጸመዉ አሰቃቂ ግዲያ መቼም የማይረሳ ኢሰባዊ ወንጀል ነዉ ፍትህ ይዳኘን! በተጨማሪም በ2011ዓ.ም መስከረም ወር መጨረሻ በሀዋሳ አሮጌ ገበያ ቃጠሎ ሰብብ በአሁኑ ጊዜ ያለ ፍትህ በእስር ቤት እየተሰቃዩ ያሉ የወላይታ ተወላጆች ፍትህን ይሻሉ! ቢጫዋ ሂሊኮፕተር ወደ ደቡብ መምጫዋ በጉጉት ይጠበቃል የክሩ መተርተር ፍትህን በሀገራችን ለማስፈን ወሳኝ ነዉና በአክብሮት እንጠይቃለን!!!!!”
Filed in: Amharic