>

በነጻነት ካልዘረፍን ጫካ እንገባለን!!! (ሉሉ ከበደ)

በነጻነት ካልዘረፍን ጫካ እንገባለን!!!
ሉሉ ከበደ
የጎልያድ እብሪት ለዳዊት ወንጭፍ ዳረጎት  ነው ። ሰው በላው የትግሬ ነጻ አውጭ ፤ የሌቦች ቡድን መሪ ደብረጽዮን የሚባለው ትንሽ ሰው ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን ህዝብ ሊያስፍውራራ ሞክሮ ነበር።  የትግራይን ህዝብ ማንበርከክ አይቻልም ብሏል። ይህንንም ያለው በካቴና  እየታሰሩ ወደእስር በመጋዝ ላይ ያሉ ብሄራዊ ሌቦች ፤ የሚበዙት ትግሬዎች በመሆናቸው ነው ። ይዋል ይደር እንጂ ካቴናው ለሱም የሚመጣለት መሆኑ ስለገባው ይሆናል።  የትግራይን ህዝብ ማነሳሳቱ ይመስላል  የህውሀትን ሌቦችና ነፍሰ ገዳዮች እንዲታደግ።
በመሰረቱ ህውሀት የኢትዮጵያን ህዝብ ከማንበርኩኩ በፊት ያንበረከከውና  እንደፈለገ የጋለበው የትግራይን ህዝብ ነው።  የትግራይን አርሶ አደር ልጆች ተጠቅሞ የኢትዮጵያን ህዝብ አንበረከከ። አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ በቆራጥ ልጆቹ መስዋእትነት ከህውሀት ነጻ ሲወጣ፤ እስካሁን እንደተንበረከከ ያለው የትግራይ ህዝብ ግን ማናኛውንም አይነት የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ እየሆነ ነው። ይህን ወገናችንን ነጻ ማውጣት የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ሀላፊነት ነው።
 በሌቦች ላይ ተከፍቶ  ያለውን ዘመቻ ህዝብ መረጃ በመስጠት ማፋፋም አለበት። ባለፉት ሀያሰባት አመታት ንብረታችሁን የተቀማችሁ፤ ስራችሁን የተቀማችሁ፤ የንግድ ድርጅታችሁን የተቀማችሁ ፤  በውጭ ሀገር እድሜልካችሁን ደክማችሁ ያጠራቀማችሁትን ሀብት ሀገር እናለማለን ብላችሁ  ከገባችሁ በኋ ላ በወያኔ ተዘርፋችሁ  የተባረራችሁ ፤ ለምሳሌ የአዲግራት መዳኒት ፋብሪካ መስራች አቶ ሙሉጌታ ጓዴ ሀያ አምስት ሚሊዮን ብር ተዘርፍርው ካገር ወተዋል።የመዳኒት ፋብሪካውንም ኢፈርት ቀምቷቸዋል።ለንደን ላይ ወያኔን ከሰው ነበር በንግሊዝ አገር ፍርድ ቤት። እዚያ መክሰስ የቻሉት ወያኔ ለንደን ውስጥ ድርጅት፤ ንብረት ስለነበረው ነው። ሀብታችንን ያልወሰዱበት ቦታ የላቸውም። ሌሎቻችሁም በውስጥም በውጭም ተመሳሳይ ዝርፊያ የተፈጸመባችሁ ኢትዮጵያውያን ቢቻል በመደራጀት ሀብትና ንብረታችሁን የማስመለስ ህጋዊ ትግል መጀመሪያው ጊዜ አሁን ነው።
ሰሞኑን የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት በየዞኑ እየተዘዋወሩ በክልሉ ሲፈጸም የኖረውን ወንጀል በማጥናት ላይ ናቸው።በሰበዊው ሰው ላይ የደረሰው ዘግናኝ እልቂት እንዳለ ሆኖ ያንኑ ያህል በሚዘገንን መልኩ አብዲ ኢሌን ያንቀሳቅሱት የነበሩ የትግሬ ጀነራሎች የክልልሉን ግዙፍ ሀብት ሰርቀዋል። በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወስደዋል። ከፌደራል መንግስት በጀት ለክልልሉ ሲለቀቅ ወቅቱን ጠብቀው የህወሀት ሰዎች ወደዚያ ይንቀሳቀሳሉ ። ኮንራት ይፈራረማሉ በልማት በፕሮጄክት ስም። ክልሉ ለህውሀት ሰዎች እንጂ ለሀገር አቀፍም ሆነ ለአለም አቀፍ ህብረተሰብ ዝግ ሆኖ የቆየ ነው። የትግራይ ጀነራሎች የሚደልቡበት ትልቅ በረት ነበር። የተዋዋሉበት ስራ ሳይጀመር ሚሊዮን ብሮች ወደ አካውንታቸው ይገባል። የሚፈለገው የገንዘብ መጠን ተጠናቆ ከገባ በኋላ ውሉ የተፈረመ ስራ ይቀራል። ወይም ተጀምሮ ያለምክንያት ይቋረጣል። ጠያቂ የለም ። ተጠያቂ የለም። ይህ መደበኛ የወያኔ አመታዊ ስራ በክልሉ ላለፉት የስቃይ አመታት ሲካሄድ የኖረ ነው። ሌላው የጀነራሎቹ ስራ መሬት በልማት ስም ማጠርና በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከባንኮች በብድር  ማውጣት ነው። በዚህ መንገድም በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ተዘርፏል። በመቶ ሺ ሄክታሮች የሚለካ መሬት ታጥሮ ህብረተሰቡ ለከብቶቹ ግጦሽ እንኳ ሊጠቀምባቸው አልቻለም ። እጅግ ሰፊ አካባቢ አጥረው ህብረተሰቡ አንዱ ወዳንዱ እንዳይሄድ ሁሉ አድርገዋል። የዚህ ሁሉ ዝርፊያ ባለቤቶች ከትግራይ የዘመቱ የመከላከያ ጀነራሎችና ባለስልጣናት ናቸው። በድሬዳዋም እንደዚሁ የፕሮጀችት ኮንትራት ተፈራመው በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ከተረከቡ በኋላ ስራውን ሳይሰሩ ቀርተዋል። የህዝብ ገንዘብ ወስደናል ። በልተናል ። ብለው  አይሸሹም ።አይደበቁም ።እንደገና መተው ሌላ ኮንትራት ይፈራረማሉ። ልባርጉ በክልሉ በየአመቱ በሚከሰተው ድርቅ ምክንያት በመቶሺዎች ዜጎች በረሀብ ይሰቃያሉ ። ህጻናት ይሞታሉ። እንስሣት ይረግፋሉ። በየአመቱ። በየአመቱ።በየአመቱ። ከዚህ ህብረተሰብ ላይ ነው እንግዲህ የወያኔ ነፍሰ በላዎች የሚቀሙና ወደቤታቸው የሚያሸሹት።
አፋር ውስጥ የእንፋሎት ሀይል ማመንጫ እንሰራላችኋለን ብለው በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ተቀብለው ገንዘቡ ተበልቷል ። ሀይል ማመንጫው ህልም ሆኖ ቀርቷል። የአፋር ጨው ሀብትና ሌሎችንም ማእድናት እያወጡ በመሸጥ ላይ ያሉት በበላይነት ያካባቢውን ሀብት የሚዘርፉት የትግራይ ወንበዴዎች ናቸው።ይህ የጠቃቀስኩት ዝርፊያ በጣም ጥቂት ምሳሌ ነው።
በጋምቤላ ሰባ በመቶ በባለሀብትነት መሬቱን የተቀራመቱት የትግራይ ሚሊሺያ አዛዦች ናቸው። ያን በማሳየት ከልማት ባንክ፤ከንግድ ባንክ፤ የወሰዱትን ገንዘብ ለእርሻ ልማት ሳይሆን በየዘመዶቻቸው ስም ፎቅ ገንብተውበት ሚሊዮን ብሮች በየወሩ የሚያከራዩ አሉ። አንዳንዶችም አሜሪካና ካናዳ በጣም ውድ ቤቶችን ገዝተው እየኖሩበት ነው
እነዚህ ሰዎች ናቸው ታዲያ የፌዴራሉ መንግስት የትግራይን ህዝብ ሊያንበረክክ ዘመቻ ከፍቷል የሚሉት። የትግራይ ህዝብ አይደለም እኮ እየሰረቀ ያለው። ስድ አደጉ ፤ ሌባው ፤ ቀማኛው፤  ማጅራት መቺው ህውሀት ነው።
Filed in: Amharic