>
4:12 pm - Sunday August 7, 2022

እርቁ የሠላምና የፍቅር ወርቅ ነውና አናርፍድ።  (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ)

እርቁ የሠላምና የፍቅር ወርቅ ነውና አናርፍድ።
 ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
      ወርቅ ሆኖና ጀግና ተብሉ መውጣት እንደሚነገረው ቀላል አይደለም፤አፈርና ጭቃ በተለበለቡበት ወላፈን ነው ወርቅ ወርቅ ሆኖ ነጥሮ የሚ-ወ-ጣው።ልክ ወርቆቹ ጀግኖች በተሰዉበት ድል፣አፈርና ጭቃዎቹ እኛ ነን ወርቆቹ ብለን በቁማችን እንደምናናፋው። ለዚህም ነው ጊዜው ባለፈ ቁጥር ወርቆቹ በተሰዉበት ምክንያት፣በቁም ያሉት አፈር እና ጭቃዎቹ የሥልጣንና የገንዘብ ሾህ በውስጣቸው አድርገው አላፊ አግዳሚውን ሕዝብ በሰበብ አስባቡ እየወጉ አሳምመው እየወጉ መርዘው የሚያስገድሉት።
 
  በሕዝብ-አምፅ ግንባሩን ተቦርቅሶ በቁሙ የተዘረረን ርኩስ አካል፤እንዳላየን ሆነን ሐቁን ካልተቀበልን የዚያን ቀን ደም አስከፍሎ፤ ሕይወት ያስገብረናልና ለእርቁ አናርፍድ!እላለሁ።ይህን አባባል በቀላል እና በአጭር ላቅርበው።
    ዶክተር አቢይ አህመድ የኢሕአድግ ፓርቲ ሰብሳቢ ሊቀመንበር ናቸው፤ይህንን ሐቅ እርሳቸውም ጠንቅቀው ያውቁታል። ፓርቲያቸው ደግሞ የተቋቋመው በአራት የብሔሮች ድርጅት ጥምረት እና በአንድ የርዕዮተ-ዓለም መመሪያ ሥር እንደነበረም በሕዝብ መገናኛ ቀጥታ ሥርጭት ላይ ሰምተን አረጋግጠናል፤(አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ነው)።
   በ፲፩ኛው መጨረሻ የዓመታዊ ስብሰባቸው መዝጊያ ላይ ግን ነገሮች ተለወጡ፤ከዚህ ነው ለውጡ መንተክተክ የጀመረው፤ሌሎች የለውጥ ቅመሞች ሳይጨመሩበት በፊት።ሕውሃት የተባለው ድርጅት ብቻ፤”የአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ርዕዮተ-ዓለምን”አራምዳለሁ፤እቀጥልበታለሁም ብሎ፣ከቀሩት አጋር ሦስቱ ብሔር ድርጅቶች ተለይቷል።ይህ የውሳኔ ልዩነት ለውጡን ማጣፈጥ ጀመረ፤መሠረታዊ እና የሁሉም ማለትም የአራቱም”ብሔረ-ሰቦች”የመንግሥቱ ምሥረታ ፅንሰ-ሀሳቦች መንፈስ እና የእንቅስቃዎች መነሻ መስመር እንደነበር ይታወቃል።
ሆኖም፦”ለሃያ ሰባት ዓመታት የሠራነውን የአገር ጥፋት በፍፁም ልንደግመው አይገባንም፤”ያሉት ሶስቱ ድርጅቶች እና፣”በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሥም ለመድገም እንደገና መቶ ዓመታት እስኪሆነን እንሞክራለን” ብሎ የወሰነው ሕውሃት ብቻ መሆኑ በአደባባይ ታየ።እናም የፅንሰ-ሀሳብ ልዩነቱ እንደተፈጠረ ሕሊናቸው እያወቀ፤ዳሩግን”አንድ ላይ መጓዝ አለባቸው”የሚሉ ሁሉ የሚያደርጉት ሁሉ ጥፋት ሳይሆን ውድመት ነው።ከዚህ ዓይነት ሕሊና የክህደት ጉዞ የሚገኘው ውጤት፣መጓተት ካልሆነ በቀር ወደፊት መራመድ አይቻልም፤እንደው በሕዝብ ድጋፍ መንቀሳቀስ ብንጀምርም እንኳ፤በጉልበት ወደኋላ የሚጎትተን እንደሚኖር አሳስቤአለሁ(ሦስተኛውን እጅ በዚህ መረብ ላይ {(http://amharic.borkena.com/2018/10/27/የ፫ኛውን-እጅ-ሕውሃት}ይመልከቱ፣አፉ እሺ እያለ፣ልቡ የሚሸፍተውን የሕዝብን ጠላት ይለዩበታል፤)እናም ውሃን ከምንጩ ነገርን በእንጭጩ ነውና ቁስላችንን እንየው፤በጥንቃቄ ሳያመረቅዝ እንመርምር።
       በሚታየን ነገር ላይ ፍራቻም ሆነ ስጋት የሚመጣው ካላወቅነው ብቻ ነውና ለዚህ ደግሞ መፍትሔው ቢያንስ እግዚአብሔር በክብር የሸለመን እና በአምሳሉ አድርጎ ለመፍጠሩ መረጃችን የሆነውን የሕሊና ዳኝነታችንን (ገንዘብ የማይገዛውና ሥልጣን የማያሟሽሸው)መጠቀም እንደሆነ በተግባር ማሥመስከር ነው።አባቶቻችንም በሕሊናቸው እየተመሩና ፈሪሃ እግዚአብሔርን ኢትዮጵያን በነፃነት ያቆዩልን፤ይህ ፀጋ ከትውልድ ወርሰን እና በውስጣችን እያለን ከምሁራን ብቻ ዳኝነትን እና ማስተዋልን ልንጠብቅ አይገባንም።
           ሕዝብ በህሊና ዳኝነቱ እንዲመረምረው ዕድሉን ካገኘ፤ከአንዳንድ የምሁራን የጥፋቶች ወጥመድ አስቀድሞ ይጠበቃል፤እናም በሕዝብ-አምፅ ግንባሩን ተቦርቅሶ የተዘረረ መሰሪ ርኩስ አካልን እንዳላየን ሆነን ልንቀጥል አይገባንም።ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፖለቲካ ትውልድ ኢሐድግ ናቸው፤ሕዝባዊነታቸውን ሕሊናቸው ሳይቸነፍ ልባቸው ውስጥ ኣምቆ በአደራ ማቆየቱ ብልኅነት ነው።መዘንጋት የሌለብባቸው ያ!ኢሕአድግ ማክተሙን ነው፤እርሳቸው አይደለም ያፈረሱት፣ራሱ ዲሞክራሲ ነው አናቱን ብሎ የከሰከሰው።ሕውሃትም ይሄን አውቆና የለሁበትም ብሎ የፖለቲካ ገለልተኝነቱን እንዳይሆን አድርጎታል።
ስለዚህ ለእርቁ አናርፍድ፤ዛሬ ነገ እያልን በሰበብ አስባቡ ምክንያቶችን እየደረደርን ማጓተቱ እስከዛሬም ድረስ በሦስተኛው እጅ ተንኮሎች ደም አስከፍሎ፤ ሕይወት እንዳስገብረን የባሰው የሚመጣበት መንገድ በሦስተኛው እጆች አባላት እየተቆፈረ ነውና እንደሙሴ ጠላትን ለመከላከልና የታላቁ ጴጥሮስን መባረክ ልብ ብለው ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሆይ፣ዛሬም ወርቅ የሆነው እርቁ!!! ሠላምና ፍቅር የፀነሰው አፈርና ጭቃ ከመሆኑ በፊት አናርፍድ፤እላለሁ። 
Filed in: Amharic