>
8:06 am - Saturday December 10, 2022

ለሱዳን፣ ህወሀት እና ህወሀታውያን እልቂት የደገሳችሁለት ህዝብ መጽናናትን ይመኝላችሗል!!!   ዘመድኩን በቀለ

ለሱዳን፣ ህወሀት እና ህወሀታውያን እልቂት የደገሳችሁለት ህዝብ መጽናናትን ይመኝላችሗል!!!
ዘመድኩን በቀለ
~ በነገራችን ላይ የእኛዋ ቢጫዋ ሂሊኮፍተር ለጤናዋ እንደም ከርማለች? ሰላምም ናት አይደል? ሰሞኑን ስትጠፋብኝ ግዜ ነው መጠየቄ።
~ ኦማር አልበሽርስ እንዴት ናቸው?  እስከ አሁን ጅማ ናቸው ወይንስ ወደ ካርቱም ተመልሰዋል ?
~ ጌታቸው አሰፋ፣ አቦይ ፀሐዬ፣ በረከት ስምኦን፣ ታደሰ ጥንቅሹ በአጠቃላይ ሰሚን ኮሪያ ይቅርታ ሰሜንኢትዮጵያ የተደበቁት ሁሉ ሰላም ናቸው አይደል?  እነሱን ብቻ ክፉ አይንካብን። በህይወት መኖራቸውን ማረጋገጡም መልካም ነው። አሜን።
 ያዘኑትን ያረጋጋልን። ከዳግም ሰልፍና ሞትም ይሰውርልን። አሜን።
ዛሬ ጧት ረፋዱ ላይ የሀገረ ሱዳን ከፍተኛ የጦር አዛዦችን የጫነችና ከገዳሪፍ ወደ ጋላባት ለስብሰባ ይዛ በማቅናት ላይ የነበረች አንዲት የጦር ሄሊኮፕተር በጋላባት የጦር ካምፕ ውስጥ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀና በይፋም ባልተነገረ አደጋ ተከስክሳ መውደቋ ታውቋል።
በወደቀችውና በተከሰከሰችው ሄሊኮፐተር ውስጥም ለጊዜው በስም ያልተጠቀሱ 9 የሱዳንና 5 የህወሓት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እንደነበሩና ከእነዚህ የጦር መኮንኖችም ማለትም ” ከሱዳኖቹም ” ሆነ ከ”ህወሓት” ቶቹ የቀድሞ የጦር መኮንኖች ለወሬ ነጋሪ እንኳ የተረፈ እንደሌለ ነው የተነገረው።
ሄሊኮፕተሯ የመተማውን የአሜራ ወንዝ በመከተል በኢትዮጵያ ድንበር በኩል አድርጋ ጋላባት ጦር ካምፕ ስትደርስ ነው የመከስከስ አደጋው የገጠማትም ተብሏል። ትመታ ወይንም ትፈንዳ የታወቀ ነገር የለም።
የሞት ዜናውን ተከትሎ ግን ከሱዳን መንግሥት ሁሉ ቀድሞ  የትግራይ  ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒዩኬሽን ጽሕፈት ቤት የሐዘን መግለጫ ተሸቅዳድሞ መስጠት እኔን ጨምሮ  ብዙዎችን አስገርሟል። ህወሓት ከትናንትናው ሰልፍ በተጨማሪ በዛሬው አደጋ ለሱዳን አጋርነቷን በድጋሚ ማረጋገጧ ታውቋል። [ አልበሽር እንኳ ሳይሰሙ እነሱ ግን ከምኔው ሰሙ በዝናታችሁ] ወይ ፍቅር። የፍቅር እስከመቃብር ደራሲው ማን ነበር?
በትናንትናው የመቀለ ሰልፍ በደቡብ ሱዳን ባንዲራ የሰሜን ሱዳኑን መሪ የአልበሽርን ፎቶ ይዘው ሰልፍ የዋሉ ዜጎች ከዚህ አደጋ በኋላም ደግሞ ዛሬ ለሞቱት የሱዳን ከፍተኛ የጦር መሪዎች የሀዘን መግለጫ የድጋፍ ሰልፍ በሚል ሰበብ ሰልፍ እንዳይጠሩና መሳቂያ መሳለቂያ እንዳይሆኑ የሚሰጉም አሉ።
ለማንኛውም የሜትሮሎጂ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ በአግባቡ ካልተያዘ በቀር ሰሜን ጎንደር ከሚነሳ ሄሪከን አውሎ ነፋስ ብዙ ደንቃራና ሞተራቸው ደካማ የሆኑ በአረቄ ጉልበት የሚንቀሳቀሱ ሂሊኮፕተሮችን ይከሰክሳል፣ አውራ ጎዳናውንም ያጠራል። ኢትዮጵያንም ከቆሻሻ አስተሳሰብ ነፃ የዋጣል ተብሎም ይጠበቃል።
★ የዐማራውን አምላክ ባሰብኩት ቁጥር ግን እንደው ድንቅ ነው የሚለኝ። እንዲህ ቅርብ ነው ለካም እላለሁ። ለዚህ ህዝብ በችግሩ ጊዜ መንግሥትም፣ ፌደራልም፣ መከላከያና ፖሊስም፣ ልዩ ኃይልም አልደርስለት ቢሉ የሰማይ የምድሩ ጌታ ግን አይዘነጋውም። እሱ የምስኪኖች ጌታ በፈቃዱ እንዲህ ከተፍ እያለ ሊወጋው የሚያኮበኩበውን ሁሉ ክንፉን እየሰበረ ፦
~ ወዳጄ ጥፋ ሲልህና ፈጣሪ ሲጣላህ አንቀዥቅዦ ወስዶ ከዐማራው ጋር ያላትምሃል። ከዚያ በኋላ አለቀልህ። ዐማራን ከኢትዮጵያ ጋር አንድ አድርገው ሊያጠፉ የተነሱ ሁሉ ድራሽ አባታቸው ሲጠፋ አይቻለሁ።
~ ሊቢያ የዚህ ጽዋ ጠጪ ናት፣ ሶሪያም እንዲሁ። የመንና ሶማሊያም ቀምሰዋል። ሶማሊያማ 50 ቦታ ነው የተቆራረጠችው። ኤርትራም ዐማራን ጠላቴ ብላ ተዋግታ  የጤፍ ያለህ እስክትል ድረስ በጠኔ ተቀጥታለች። ግብፅ በጣር ላይ ናት። ዐረቦቹ በሙሉ በየተራ ይቀምሷታል። ሻእቢያንና ወያኔን አሰልጥና ኢትዮጵያን ለሁለት የከፈለችው ሱዳንም ሳትውል ሳታድር የእጇን አግኝታለች። ሰሜንና ደቡብ ሱዳንም ሆና አርፋዋለች። ለሦስተኛ ሀገርነት ደግሞ ዳርፉር ትግል ላይ ናት።  ጣሊያን ብዙ ዐማራ አርዳ ከተመለሰች በኋላ የአውሮጳ ነጭ ድኻ ሆና ቀርታለች። ዐማራና ኦርቶዶክስን እናጠፋለን የሚሉ ሁሉ ወገብ ዛላቸው ይቆረጣል። በሰቀቀንም ይኖራሉ። እውነታው ይሄው ነው። ለዚህ ምስክሩ ደግሞ ህውሓት ናት። ፖሊሲ ቀርጻ ልታጠፋው ብትጥርም ጭራሽ ራሷን አጥፍቷት አረፈው።
የሞቱትን ነፍሳቸውን ይማር ። የትግራይ ኮሚኒኬሽንም ጽናቱን ይሰጠው። አሜን።
ሻሎም !  ሰላም !
ሕዳር 30/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic