>

ይድረስ ለዶክተር አብይ > መረጃ (ሀብታሙ አያሌው)

ይድረስ ለዶክተር አብይ  > መረጃ
ሀብታሙ አያሌው
ዛሬ ማክሰኞ ምሽት በዓቃቤ ህግ መስሪያ ቤት በኩል የተላለፈው ዶክመንተሪ ያሳለፍነውን ሰቆቃ በከፊል አሳይቷል።  የወንድሞቼን ሰቆቃ እንደ  አዲስ እየሰማሁ እንባዬን በመዳፌ መስፈሬንም አልደብቅዎትም።  ይህ ጊዜ እንዲመጣ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦም በግሌ ከልብ አመሰግናለሁ።
ምስጋናዬን የሚከተል ጥቆማ ግን አለኝና እሱን ላድርስዎ… 
1ኛ. ይህ ሁሉ ስቃይ የተፈፀመበትን ማዕከላዊን ሲመረ የነበሩት የማዕከላዊ ዋና አዛዥ ኮማንደር እረታ እና የፀረ-ሽብር ዲቪዚዮን ኃላፊው ኮማንደር ተክላይ መብርሃቶም በቁጥጥር ስር አልዋሉም ተሰውረዋል።
 በጣም  አሳዛኙ ነገር ግፈኛው ኮማንደር እረታ የእስር ዘመቻው ከመጀመሩ ከሁለት ቀናት ቀደም ብሎ እስከ ቤተሰቡ ጀርመን እንዲገባ ተመቻችቶለት በክብር መሸኘቱን ያላወቁ እንደው ልንገርዎ ብዬ ነው።
ኮማንደር ተክላይን ዱካውን እየተከታተልን ነው ኮማንደር እረታ የኦዴፓ (የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) ኮማንደር ተክላይ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ  ሰዎች እንደነበሩ ይታወቃል።
2ኛ. የእርስዎ ፓርቲ አመራር የሆኑት የአሁኑ የአቃቤ ህግ  መስሪያቤቱ ሚኒስትር  አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ያን ጊዜ ሚኒስቴር ዴታ ሆነው ለዚህ ሁሉ ወንጀል የህግ ከለላ ሲሰጡ የነበሩ እና የአዴፓ (የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ) አመራር የነበሩት የቀድሞው የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር የአሁኑ የእርስዎ አማካሪ አቶ ጌታቸው አምባዬ ዋነኛ አካል ነበሩ። ሁለቱም ሰዎች ቢያንስ   ከፊት ለፊት ዘወር ሊሉ ሲገባ ከሳሽ ሆነው መቅረባቸው ተቀባይነት የለውምና እባክዎ ዘወር ያድርጉልን።
3ኛ. በጌታቸው ምባዬ ትዕዛዝ ክስ እያደራጀ የስንቱን ሂይውፕት  ያመሰቃቅል የነበረው  አቶ ዓለምአንተ አግደው ወንድሜነህ የተባለ የጌታቸው አሰፋ እና የጌታቸው  አምባዬ ተልዕኮ ፈፃሚ የነበረ፤ ባሁኑ ( ወቅት  በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህግ ጉዳዮች ምርመራ እና  ቁጥጥር ዳይሬክተር ) በተጨማሪም የሜቴክ የወንጀል   ጉዳይ አጣሪ ኮሚቴ ሆኖ እየሰራ ያለ።  የአማራን ህዝብ እወክላለሁ ብሎ በያዘው ስልጣን አማራ እያደነ እንደ ጠላት ለሰቃይ ሲዳርግ የነበረ ሰው ዛሬም በተመሳሳይ ኃላፊነት ቀጥሏል።  እናም እባክዎ ነዚህን ሰዎች ቢያንስ ከስልጣን  ገለል ያርጉልን።  ኮማንደር እረታስ እንዴት የእስር  ዘመቻው ከመጀመሩ ከሁለት ቀን ቀድሞ ካአገር  ወጣ ?  ቢጣራ መልካም ነው።
Filed in: Amharic