>
4:38 pm - Thursday December 3, 5209

አባቶቻችን እንዲህም ነበሩ!!! (አለማየሁ ገለላጋይ)

አባቶቻችን እንዲህም ነበሩ!!!
.አለማየሁ ገለላጋይ
” በዚህች ሐገር ………  ጦርነትም የወንድማማች የነበረበት ዘመን አልፏል ። የከፋ የመጨረሻ ንጉስ ታቶ ጋኪ ሼሬቾ ፣ አምላክ በእሳቸ  አድሮ የሚናገር መኾኑ የሚታመንላቸው ገዥ ነበሩ ። ከአፄ ምኒልክ ጋር ለመዋጋት በሚሰናዱበት ጊዜ የእንግሊዝ መልእክተኛ ወደ እርሳቸው መጣ ።
.
‘ ምንድነው ? ‘ አሉት ።
‘ ዩጋንዳ ላይ የሰፈረው የእንግሊዝ ጦር ልኮኝ ነው ። ‘
‘ ምን ብሎ ? ‘
‘ ከሚንሊክ  ጋር መዋጋትዎ ስለማይቀረር ጦር መሳሪያ እንላክላክልዎ ይላል ። ‘
ንጉስ ታቶ ጋኪ ሻሬቾ እንዲህ ሰሲሉ መለሱ ፦
‘ አሁን የሚካሄደው ጦርነት የወንድማማቾች …. ነውና የእናንተ እርዳታ አያስፈልገኝም ። እኔ ሚኒልክን ካሸነፍኩ አገሩን በሙሉ አስተዳድራለሁ ፤ እሱ ካሸነፈኝ አገሩን በሙሉ የይግዛ ። እርዳታ የምጠይቃቹ የውጭ ጠላት ሲመጣብኝ ብቻ ነው ። ‘
ይህ በጦርነት ላይ  የነበረው ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነት ዛሬ በሰላሙም ጊዜ የለም ማለት ይቻላል ። ሁሉም በየፊናው ተትከንካኝ እንዲሆን ስለተፈለገ …. እንኳን ጦርነት ፣ ስፖርትም በወንድማማቾች ፉክክር መታየቱ እጅግ ፣ እጅግ አጠራጣሪ ሆኗል ። “
.
( -ከ” መለያየት ሞት ነው ” መፅሐፍ  )
 
ታህሳስ ባታን በእንጦጦ ጋራ ስር!!!
የሽሀሳብ አበራ
«አልጫ መረቁ ወጡ ሰለቸኝ
ምኒልክ ተነስቶ ሽሮ ባበላኝ።» 
 
እምዬ በሞቱ ጊዜ በሕዝቡ የተገጠመ።
 
“ፈረስ በቅሎ ስጠኝ ብየ አልለምንህም
አምና ነበር እንጅ ዘንድሮ የለህም”
 ታህሳስ 3 ቀን 1906፡፡ 
………
የሸዋ መኳንንት ከአንኮበር ተጨንቀዋል፡፡የወሎ ሹማምንት ከደሴ ጆሯቸውን አንቅተው ወደ እንጦጦ ያደምጣሉ፡፡ እንጦጦ ዝም ብላለች፡፡ብላቴናዋ አዲስአበባ አንገቷን አቀራቅራ
በእንጦጦን ጋራ ስር ተደብቃለች፡፡ ታህሳስ 2/1906
ከአፍሪቃ ምድር የተገኘው ልዮ ክስተት ዛሬ አንደደበቱ ተዘግቷል፡፡ ከአድዋ ተራሮች ስር እብሪተኛውን ነጭ በእንፉቅቅ ያዳኸው፣ የክፍለዘመኑ ብስል መሪ አልጋ ላይ መዋል ከጀመረ አስርት ዓመታት ተቆጥረዋል ፡፡
ከአፍሪካ ምድር የጥቁር ሱናሜ አስነስቶ፣ ከአይሁዳዊው ሲግመንድ ፍሩድ የስነልቦና ትንታኔ ቀድም የጥቁርን ሰውነት በነፍጥ ያረጋገጠ መሪ ነው፡፡ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ከመሳፍንቱ መንጋጋ መንጭቆ ያሰመራትን ኢትዮጵያ ፣ተራማጁ መሪ ታህሳስ አንድ ጀምረው በጠና ታመዋል፡፡ህዝቡ ተጨንቋል፡፡ የቤተመንግሥት ሹመኞች እምየው
ቢሞቱ ለህዝብ እንዴት ማርዳት እንዳለባቸው ግራ ገብቷቸዋል፡፡ እትጌ ጣይቱ በቁርባን ካገቧቸው እምየ ሚኒሊክ አልጋ የሚወርስ ልጅ አልወለዱም ፡፡ ነገ ኢትዮጵያን ማን ይምራት የሚለው እንቆቅልሽ ሁኗል ፡፡ የእነ እንግሊዝ ፣የእነ ፈረንሳይን…. አሻጥር የሚመክት መሪ ፍለጋ ሹመኞች መዋተት ላይ ናቸው፡፡
ታህሳስ 1/1906
አፄ ሚኒሊክ ሲበዛ መንፈሳዊ ናቸው፡፡በማርያም ከማሉ ንቅንቅ አይሉም፡፡ በአድዋው ጦርነት ለሞቱ ወራሪ ነጮች አዝነዋል፡፡ ንሰሃ ገብተዋል፡፡በአድዋ ሃገራቸውን ነፃ ቢያረጉም፣ የጠፋው የሰው ህይወት ስላሳዘናቸው ድሉን ያከበሩት ከሰባት ዓመት በኃላ ነበር፡፡ ለጠላት የሚራሩት ሚኒሊክ በወቅቱ ስለህመማቸው እና ሞታቸው ለመናገር ለሹማምንቱ የከበዳቸውም ህዝቡ ስለሚወዳቸውም ነበር፡፡ እምየም ብሎ ይጠሯቸዋል፡፡
ሚኒሊክ በፀና ህመም እየታገሉ ለአስር ዓመት ሃገራቸውን መርተዋል፡፡ በጨለማ ዘመን የንጋት ኮከብ ሁነዋል፡፡ታህሳስ ሶስት ግን፣ የታህሳስ ባታ ዕለት 1906 ከዛሬ 105 ዓመት በፊት
ሳህለማርያም (አፄ ሚኒሊክ) በተወለዱ በ 70 ዓመታቸው እስከ ወዲያኛው አሸለቡ፡፡  ዳሩ እያደር የዘመን ትክሻን እየተጋፉ ይወለዳሉ፡፡
Filed in: Amharic