>
5:22 am - Friday July 1, 2022

የአ.ብ.ን ሰዎች "እንገነጠላለን!" የሚሉት የወያኔን ኢትዮጵያን የማፍረስ አጋንንታዊ ዓላማ ለማሳካት ነው!!! (አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው) 

የአ.ብ.ን ሰዎች “እንገነጠላለን!” የሚሉት የወያኔን ኢትዮጵያን የማፍረስ አጋንንታዊ ዓላማ ለማሳካት ነው!!!
አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
 ጥብቅ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ ለመላው የአማራ ሕዝብ ንቃ ወገኔ!!!
ወያኔ በረሃ እያለ ኢትዮጵያዊነት የሚሰማቸውን፣ ጠባብ አመለካከቱን የሚጸየፉትን፣ ፀረ አማራ ሰይጣናዊ የደንቆሮ ዓላማውን የሚቃወሙትን ልቅም አድርጎ እያረደ እንደፈጃቸው የዓይን ምስክሮችና በርካታ መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡
ይህ የጥፋት ኃይል በአሁኑ ሰዓት እራሱን አሳክሎና እራሱን አስመስሎ ከአማራ ጉያ እራሱን ፈጥሯል፡፡ ምን ያህል በርትቶ ቢሠራና ምን ብሎ ማሳመን ቢችል ከአማራ ጉያ ውስጥ እራሱን ሊፈጥር እንደቻለ ባስበው ባስበው ሊገባኝ አልቻለም!!! ዘመኑ ሆዱን ብቻ አምላኪ የበዛበት ዘመን መሆኑ ሳይረዳው አልቀረም!!! ዳግማዊ ወያኔ ከአማራ ጉያ መፈጠሩን ምን ያህሎቻችን እንደተረዳነው ግን አላውቅም፡፡
* አብን ሲመሠረት በጣት ከሚቆጠሩት ጥቂቶቹ በስተቀር የተቀሩት መሥራቾቹ የብአዴን ካድሬዎችና ከወረዳ አሥተዳዳሪነት ሳይቀር ተነሥተው እንዲካተቱበት የተደረጉበት የብአዴን ካድሬዎች ጥርቅም መሆኑን፣
* ከመሰብሰቢያ አዳራሽ አንሥቶ የብዙኃን መገናኛ ሽፋንና ሌሎች በግልጽ የታዩ ድጋፎች ከብአዴን የተደረገላቸው መሆኑን፣
* እነኝህ መሥራች የተባሉት በሙሉ አብንን ለመመሥረት ከመንቀሳቀሳቸው ቅርብ ጊዜ በፊት ስለአማራ መብት ጥቅምና ህልውና በመሟገት፣ በመታገል፣ በመጮህ ጨርሶ የማይታወቁ መሆናቸውንና ይሄንን ድርጅት ለማቋቋም ሲያስቡ ብቻ ሁሉም በድንገት ተነሥተው ከአንደበታቸው ወጥቶ የማያውቀውን ቃል አማራ አማራ ማለታቸውን በመመልከት “ለጠቢብስ አንዲት ቃል ትበቃዋለች!” እንዲል መጽሐፉ ከእነዚህ ጠቋሚ ሁኔታዎች በመነሣት መመሥረታቸውን ይፋ ሲያደርጉ ይሄንን ድርጅት ብአዴን/ወያኔ ለስውር ዓላማ ያቋቋመው ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬየን ተናግሬ ነበረ፡፡
“በራስ ተነሣሽነት ከአማራ ሕዝብ ወጥተው ለአማራ ሕዝብ ሊታገሉ በቁጭትና በብሶት የተደራጁ ቢሆኑ ኖሮ እነዚህ ሰዎች በምንም ተአምር ቢሆን፣ በየትኛውም አመክንዮ ብናስበው ድርጅቱን ከብአዴን/ወያኔ የሰርጎ ገብ ሴራና ጥቃት እራሳቸውን ለመጠበቅ ሲሉ፣ ትርጉም ያለውን ሥራ ለመሥራትና ከሕዝብም አላስፈላጊ ጥርጣሬን ለማራቅ ሲሉ በድርጅቱ ውስጥ እንኳንና ካድሬ በገፍ ሊታጎርበት ይቅርና አንድ ሰው እንኳ ቢሆን ከታሪካዊ ጠላታችንና ከአራጃችን ብአዴን ጋር ንክኪ ያለውን ሰው ለማካተት ፈጽሞ አይፈቅዱም ነበር፡፡ አማራ ሰው አጥቶ ነው ወይ ከአማራ ታሪካዊ ጠላት ብአዴን መንጋ መጥተው የሚታጎሩበት???” ብየም ጥርጣሬየን አጉልቸ ነበር፡፡
ያልኩት አልቀረም አብን ለካ የወያኔ/ብአዴን የሸፍጥ ፍሬ ኖሮ መከረኛው አሳረኛው ለመከራ የፈጠረው አማራ ከጉያው ቀንደኛ ጠላት በቅሎለት ቁጭ ብሏል፡፡ ከሰሞኑ የአብን አመራሮች የወያኔ ተቀጣሪነታቸውን የሚያሳዩ ነገሮችን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ አንደኛው “ምርጫው ይራዘም አይራዘም?” በሚለው ጉዳይ ላይ በያዙት የወያኔን እንጅ የአማራን ጥቅም በማያስጠብቅ አቋም ሲሆን ሌላው ደግሞ አንድነትን ማብጠልጠል መኮነን መጀመራቸው፣ የኢትዮጵያን መፍረስ ለማየት መቋመጣቸውን የሚያሳዩ ሐሳቦችን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ መሰንዘራቸው ነው፡፡ ለካ ያለነገር አልነበረም የአብን አመራሮች አብንን “ከኢትዮጵያ እንገንጠል!” የሚሉት የወያኔ ቅጥረኛ የደናቁርቱ “የቤተ አማራ ፍሬ ነው!” ሲሉን የነበረው፡፡
የአማራ ርስት የአማራ መሬት ያልሆነ መሬት ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለ እንዳይመስልህ “እንገነጠላለን!” የሚሉት የወያኔን ኢትዮጵያን የማፍረስ አጋንንታዊ ዓላማ ለማሳካት እንጅ፡፡
አንድነትን ማብጠልጠል መኮነን ብቻ አይደለም እያደረጉ ያሉት፡፡ ልክ ወያኔ አንድነት፣ ኢትዮጵያ የሚሉትን ትግሮች ጠላቱ አድርጎ እያረደ እንደፈጃቸው ሁሉ አብንም አንድነት፣ ኢትዮጵያ የሚሉ አማሮችን ጠላት በማድረግ መዛት ማስፈራራት ጀምሯል፡፡
አቅሙ ስለሌላቸው እንጅ እንደወያኔ ሁሉ እነሱም ኢትዮጵያ፣ አንድነት የሚሉ አማሮችን እያረዱ ቢጨርሱ ደስታውን እንደማይችሉትና ይሄንን ከማድረግም እንደማይመለሱ አንድነትንና ኢትዮጵያን በሚሉ አማሮች ላይ በሚሰነዝሯቸው ኃይለቃሎች መረዳት ይቻላል፡፡
 በአንድነት ስም የሚነግዱ ፀረ አማራ የጥፋት ኃይሎችን መኮነን፣ ማውገዝና መታገል አንድ ነገር ሆኖ እያለ” አንድነትን ” መኮነንን፣ ማብጠልጠልን ከዚያም አልፎ አማራ የኢትዮጵያን አንድነትና ህልውና ለድርድር ሳያቀርብ ተደራጅቶ እራሱንም ሀገሩንም እንዲያድን እንዲታደግ የሚሠሩ የሚቀሰቅሱትን ጠላት አድርጎ መቁጠርን፣ ማሳደድን ምን አመጣው???
እነዚህ ሰዎች መሣሪያ በእጃቸው ቢኖር ወያኔ ኢትዮጵያዊነት የሚሰመቸውን ትግሮች መንጥሮ እንደፈጀ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት የሚሰማውን አማራ ሁሉ መንጥረው ከመፍጀት ይመለሳሉ ወይ???
የአማራ ሕዝብ ሆይ! ወያኔ/ብአዴን ጠላትህን ከጉያህ አብቅሎልሀል አቅም አግኝቶና ጎልብቶ ሳይዘምትብህ፣ እየጨፈጨፈ ሳይፈጅህ በፊት ከራስህ አውጥተህ ጣል አጥፋ!!!
አትጠራጠሩ ይሄ ጭንጋፍ የእርግማን ፍሬ የወያኔ ውላጅ የጥፋት ቡድን ጊዜ አግኝቶ አቅም ካገኘ በደምህ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያን “ጠራህ!” እያለ እያረደ ይፈጅሃል!!! ልብ በል ልብ አድርግ!!!
የአማራ ልኂቃን ሆይ! ጠላት ከጉያችን ሲበቅል ዝም ብለህ የምትመለከት የአማራ ልኂቅ ካለህ ነገ በእጃቸው ለመታረድ መፍቀድህን እወቀው!!!
ልብ በል ልብ አድርግ! ጥቂት የጥፋት ቡድኖችን ጉልበተኛ የሚያደርጋቸው የብዙኃኑ ቸልተኝነት፣ ዝምታና ይሄ ብዙኃኑ በጊዜው በሰዓቱ መውሰድ ያለበትን እርምጃ መውሰድ አለመቻሉ ነው ሌላ አይደለም፡፡ እመኑኝ ብን ያድርገውና አብን የአማራ ቀንደኛ ጠላት ነው!!! ልብ በሉ ልብ አድርጉ!!!
አማራ ሆይ! አብንን አጥፋ!!! አብን ጠላትህ ሆኖ ካልተገኘ ጸጉር ከምላሴ ይነቀል!!! አብን አደገኛ የእርጉሙ ወያኔ ፕሮጀክት ነው!!! ጠላትህ ነው ፈጥነህ አጥፋው!!! አማራ አማራ ቢል እውነቱን እንዳይመስልህ ማወናበጃው ነው!!!
እኔ እውነተኛ ትክክለኛ የአማራ ድርጅት እመሠርታለሁ ብየ ሞክሬ አልቻልኩም አልተሳካልኝም የአማራ ሕዝብና የዚህች ሀገር ጥፋት የሚገድህ፣ የሚያሳስብህ፣ የዜግነትና የወገንነት ግዴታህንም መወጣት የምትፈልግ አማራ ሁሉ ከወያኔ/ብአዴን ጋር ንክኪ ያለውን አንድም ሰው ሳትቀላቅሉ ፈጥናቹህ ተደራጁና ይሄንን ወያኔ ከጉያችን ያበቀለውን ፈንጅ አምክኑ??? እባካቹህ ይሄንን ከማድረግ ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ የለህም አማራ ሆይ ፈጥነህ ተደራጅና እራስህን አድን!!! እኔ ተናግሬያለሁ ኋላ ይቆጫቹሃል የደም እንባ ታነባላቹህ ይሄ ሳይሆን በፊት ፈጥናቹህ ተደራጁና ይሄንን የወያኔን ሸፍጥ አምክን እራስህንና ሀገርህንም ከጥፋት አድን!!!
ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
Filed in: Amharic