>

የአድዋ ዘመቻ ጦርነት እና የክብረ-በዓላችን ዋዜማ፤በዐይነ-ደረቅ፣የሌብነት ቃጭል፤ቀልድ።

የአድዋ ዘመቻ ጦርነት እና የክብረ-በዓላችን ዋዜማ፤

በዐይነ-ደረቅ፣የሌብነት ቃጭልቀልድ።

ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ 
 
 “አድዋ” ሲባል በዓለም ላይ፦ከከተማነቷ ይልቅ የኢትዮጵያ ጦርነት እና ዓለም-አቀፍ  የድል ይዞታነቷ ጎልቶ ይታወቃል።ይህም የአድዋ ድል በኢትዮጵያዊያን ባለቤትነት   በታሪክ ሲመዘገብ ውስጠ-ታሪኩ የሚያመላክተው የኢትዮጵያ ሕዝቦችን መስዋዕትነት መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፤አብዛኛው ለመንግሥት ሥርዓት የማይቀርበው እንደማያውቀው ብናውቅም የእኛን ታሪክ እንደማያውቁ ባዕዶች  ግን  አንሸወድም
         የአድዋ ዘመቻ ዋዜማን ስናስታውስ በጦርነትነቱም ሆነ በክቡረ-በዓልነቱ፣ማለትም ሁለቱም ክስተቶች የሚያተኩሩበትን “ክህደቶች”ልንዘነጋቸው አይገባንም።   የ”ክህደቶቹ”ልዩነት  አንድም የዘመናት መለዋወጥ ሲሆን፣በሌላ በኩል ደግሞ የአድራጊዎቹ ወይም የፈፃሚዎቹ የመለያየት አጋጣሚ እንጂ፣የእባብ ጭራነቱን ግን ልብ ልንል ይገባል።
የእባብ ጭራ ያስባለው ክህደት:-አጋጣሚውም ታሪክ እምዬ ምንሊክ(አባ ዳኘው)ከአድዋው ጦርነት በፊት ከነበራቸው ኢትዮጵያን የማዘመን ጥረታቸው አንፃር ነው።   ሁሉንም እንግዳዎች እንደ ኢትዮጵያዊነት የአቀባበላችን ባሕል አንፃር ለሕዝብ ሠላምና ፍቅር ባዕድን አምነው ደፋ ቀና በሚሉበት ወቅት ነበር የተከሰተው።ፋሺሽት ጣሊያን የእባብ(የተንኮል)ልቡን በሰውነቱ እቅፍ አድርጎ ጠቅልሎት ግንኙነቱን በሠላም ሥም ሊመሰርትያኔ የተንኮል ውል ተፈራረመ።በ”አንድም ሆነ በሌላ መንገድ የሚናገረው “እግዚአብሔር አምላክ፣በካቶሊክ ሐይማኖት ሽፋን የክርስትናን ካባ የለበሰውን የጣሊያን ፋሺሽት(የመጥረቢያ አርማ ድሮም ስለነበረው) መንግሥት፣ በስምምነታቸው ውስጥ መርዝ እንደጨመረበትና የእጌ ጣይቱ ብጡል(የአጤ ምንሊክ ባለቤት)ውሉ ቀፏቸው አንገታቸውን ድንገት ዞር ሲያደርጉ 0ይኖቻቸው የእባቡን ጭንቅላት ድንገት በአንቀጾቹ ውስጥ ከነእቅፉ ተቀብሮ በማየታቸው ነው የሚጀምረው።
  እናም ሳይውሉ ሳያድሩ ከንጉሰነገሥቱ እምዬ ምንሊክ ጋር አስተርጓሚያቸው  ባለበት እንደገና ውሉን በሚገባ ገፅ በገፅ መረመሩት፣ራሳቸው ጣሊያኖችንም እንዲታረም ጠየቁ፣ከኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጋር ተማከሩ፣ሐቁን በማወቅ ችግሩ እንዲፈታ ጥረት አደረጉ።ለዘመናት ዘረኛ የነበረውና ዓለምን ተቆጣጥሮ የነበረው የሮማው ፋሺሽት መንግሥት ግን ባንዳዎቹን ተማምኖ እንኳን ስህተቱን ሊያርም፣በእምዬ ምንሊክ ጥቁርነታቸውም ሳይቀር ዘብቷል፤በአፍሪቃዊነቱ”ያልሰለጠነ ብለው ሕዝቡን” አንኳስሰውታልይህ ነው የጦርነቱ መነሻ እና የሽንፈታቸው መጀመሪያ
    ጣሊያኖች የትግሬውን ንጉስ አምስት ጊዜ በድብቅ እንዳሸነፉት እየተኩራሩ ንጉሰነገሥት የተባሉትን”አጼ ምንሊክን” እጁን ጎትተው ሊያመጡ እንደሚችሉ በጣሊያንኛ እየተሳለቁ በጦር ሊወጉን ወሰኑ።ቅን ልቦና የነበራቸው እምዬ ምንሊክም ይህ ክህደት ብቻ መኖሩን እንዳረጋገጡ የአንበሳ ክንዳቸውን(የሕዝብ እና የእግዚአብሔርን)በቕዽስት ማርያም የአዋጅ መቀነት ጠፍረው፣ ውስጥ ውስጡን በባሕር ጠረፋችን በባንዳዎች ተደራጅቶ የነበረውን የፋሺሽት ጦር ለመግጠም ሸዋ ተቀምጦ ሳይሆን ጎሬአቸው ድረስ ተጉዘው የተከማቸበት አድዋ በመዝመት ድባቅ ሊመቱት ቆረጡ።ነጋሪት ተመታ ሕዝ በ-ኢትዮጵያ ሰማ፣”በስራህ ደሀ አትበድል ነጋሪት ባይኖረው እንባ አለውውሀ ሆኖ ቢኮል ያለ ሞረድ የተሳለ ነው ።”ስለዚህ በደል ሐይማኖት የለውም፣ቋንቋም አያስፈልግም ባርነት ሊያሳድረን የሚሻ ፈረንጅ ሊወረን እየተጓዘ ነውና ለነጻነትህ ለእናት አገርህ ስትል ተከተለኝ፤የ”ወሰለት ቢገኝ ማርያምን አልምርህም!”አላሉም ቃል-በቃል።ያሉት ከዚህ አባባል የተለየ አይደለም፤ ጠላት ሊወረን ነው አብረን እንቋቋመውና እናሳፍረውም ቢሉም ያው ነው፤ንጉሠ ነገሥቱ እራሳቸው ናቸው፤ለዚህም ድል አድርገዋል።
   በአድዋ ጦርነት:- “ድል!!!” በቀላሉ አልመጣም፤ዘመቻ ከመደረጉና ከመጀመሩ በፊት የእምዬ ምንሊክ ቤተመንግሥት፣ከርኩሰት መንፃት ነበረበትና አሥራ ሁለት የሰላይ ፈረንጆች ወዲያውኑ እንዲባረሩ ሲደረጉ በወቅቱ መንፈሳዊ አባት ናቸው ተብለው ቤተመንግሥት የነበሩት አባ ማትያስ የተባሉትም በተንኮል ሸራቢነታቸው በሊቃውንቶች ስለተደረሰባቸው ወዲያው እንዲባረሩ ተደርገዋል፤ዘመቻው የተጀመረው ከቤተ-መንግሥት “ፅዳት”ነው።እነሆ ዛሬም ለለውጥ ተደመርን የምንል ሁሉ ያንን የአድዋ ድል መቶኛ ዓመታት መቶ ሃያ ሁለተኛ ዓመታት በዓልን ለማክበር ለዝግጅቱ በምንጣደፍበት ጊዜ የቤተመንግሥቱን ንፅህና እርግጠኞች መሆን አለብን።አንዱም የትግራይን ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያውያን ለመለየት፣ከባንዳ የልጅልጆች ቡድን ሴራ ጋራ በማያያዝ ያለይሉኝታ በውዝኝብር የሚያምሱት ቆሻሻ የአድዋ ባንዳዎች የሽንፈታቸው እድፍ ነው።
    የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ሕዝብ ድል እንጂ የተግሬዎች ወይም የአማራዎች ብቻ እንዳልሆነ፣እንደውም ሰበቡ ለጣሊያን መረጃ ሲያቀብሉ የነበሩት የተግራይ ባንዳዎቹ መሆናቸው ይታወቃል።እናም ይህ ሁሉ ጥፋት እየተደረገ ያለው የአድዋን ድል በዓል ከማድረጋችን በፊት እና በዋዜማው ደግሞ በወያኔ-ባንዳዎች ቡድን የኢትዮጵያን ሕዝብ ደም በማፋሰስ  በሚክዱበት ወቅት ነው።የተጨማለቀ እጃቸው እንዳይታይባቸው ወደኋላ ደብቀው፣ለ”ሠላም ምንጊዜም ዝግጁ ነኝ”በሚሉት እነደብረ-ፂዮን እና የ”ሰላም መልዕክተኛ ነኝ”በሚሉን እነ ኣባ ማትያስ ከነክህደታቸው በአደባባይ መታየት መጀመራቸው ነው፤በመረጃ ላስደግፈው።
  ለምንድን ነውሳ በአክሱም ማርያም ፅዮን አመታዊ በአል ላይ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ኣቡነ ማትያስ ለደብረ-ፂዮን የተክሊል ዘውድ የጫኑለት?ያውም ዕምነቱ እና  ሐይማኖቱ ላልሆነ ሰው፣የተቀደሰ እና ውድ የተክሊል ማዕረግን መግለጫ ማርከስ መንፈሳዊ ዕምነታችንን የሚሸረሽር እና አመኔታ የሚያሳጣ ድርጊት መፈፀማቸው በሐይማኖት አባቶች ይቅርታ ሊባሉ አይገባቸውም።ሕዝቡን ይቅርታ እስከሚሉት ድረስ በፍፁም ምህረት የማይደረግላቸውም፤ቤተክርስቲያኗን ስላረከሷት ነውና ተፀፅተው ንስሐ ሊገቡ ይገባል።በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያውም የቤተክርስቲያኗ ዓመታዊ በዓል ሥነስርዓት ላይ፣ሲኖዶሱ ይፍቀድ አይፍቀድ በማን-አለብኝነት ውርደት ብቻ ሳይሆን ርኩስነት ተፈፅሟል፤በተለይም ዛሬም ድርጊቱ እያንዳንዱን ሰው በየግሉ ግራ-እያጋባው ተሸፋፍኖ ይገኛልና እንደቀድሞው ሥርዓት ሁለቱም አጥፊ ባለሥልጣኖች ከነሙሉ ጥፋታቸው ዝም ተብለዋል።ይህ ሁሉ እየተደረገ ያለው የአድዋን ድል መቶ ሃያ ሁለተኛ ዓመታት ልናከብር በምንዘጋጅበት ወቅት ነው።
  ስለዚህ ማነውሳ በትግራይ ያለውን ችግር የሚፈታውና እንደ ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ከቤተ-መንግሥት ጀምሮ ያለውን የአድዋ ድል ለማግኘት በአባ ማትያስን ማባረር የዳግማዊ ምኒልክ ቤተ-መንግሥን የሚያፀዳው?የቆሻሻው ብዛት እንዲህ ቀላል አይደለም፤በደም የተጨማለቀው ያስፈራል፤የወርቅነህ ገበየሁ ጉድስ?የደብረ-ፂዮን ሴራስ?የእነ ስብሃት ነጋና የእነ አባይ ፀሃዬ ብቅ-ጥልቅ የእነ አርከበ ዕቁባይ ሹክክ፣የካድሬ ጀሌዎች ጅልጅል(ጀሌነት)ስንቱ ተነገሮ ያልቃል?ሁሉም ግን የአድዋ ድል በዓል ሊቆጠር ቀናት በቀሩት ዋዜማ ላይ ከአድዋ ጦርነት ያላነሰ ችግሮች በኢትዮጵያ ላይ እየወታተቡባት ይገኛሉ፤ዐይናችንን ገለጥ አድርገን እንመልከት፤ወሳኝ ወቅት ላይ ነን፣ኢትዮጵያዊ መሆን ወይም አለመሆን። “ጸሎት ከፍቅር ሀይማኖት ከምግባር ይበጃል አለበለዚያ ለግብዝነት እንጋለጣለን”ዐይነ-ደረቆቹ፣የሌብነት ቃጭላቸውን እንደቀልድ ይዘው ወደ አፄ ምኒሊክ ቤተ መንግሥት   ይገባሉና ከአድዋ የድል ታሪክ እንማር።

መልካም የአድዋ ድል ፻፳፪ ኛው በዓል ይሁንልን።

Filed in: Amharic