ሳምሶን ሚሀይሎቪች
ህይወት ሁሌም ባይሆን ፍትህ በምድር poetic justice አይነት ነገር ትጫወታለች። ደጋጎችና ቅን አሳቢዎች ውጣ ውረዱን አልፈው ሲያሸንፉ ፣ እበላ ባዮች opportunists ደግሞ ቀን ሲጥላቸው የምናይበት አጋጣሚ ከስንት አንድ አይጠፋም። የፕሮፌሰር ምንዳርያለው ዘውዱ እና የሌላው መምህር ዘሪሁን ተሾመ ታሪክ ይህን አይነት እውነታ አለው።
በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር 1985 ምንዳርያለውም ዘሪሁን ተሾመም ” የድሮ ስርዐት ናፋቂ ” ተብለው ከሚያስተምሩበት ዩኒቨርሲቲ ተባረሩ። ዘሪሁን ወደ እሜሪካ መጭ አለ ፣ ምንዳርያለው ሀገሩ ላይ ፍዳውን ተቀበለ በስተመጨረሻም ወደ አያቶቹ ስራ ግብርና እንዲመለስ ተገደደ። እነ አዜብ ጎላ በአንድ ሌሊት ከ፬ኛ ክፍል ዘለው የህግ ምሩቅ ሲሆኑ “ነፍጠኛው” ምንዳርያለው መሀይም ይሆን ዘንድ ከሚሰራበት ዱካውን እየተከተሉ የስንብት ደብዳቤ የሚያጽፉበት ደህንነቶች ተመደቡበት።
![](https://www.ethioreference.com/wp-content/uploads/2019/01/16054-300x169.jpg)
ዘሪሁን ተሾመ በራሱ ምርጫ በግፍ ከስራ ያባረረውን ስርዐት ማገልገል ሲጀምር ምንዳርያለው ደግሞ በተደጋጋሚ ይቀርብለት የነበረው የይቅርታ ጠይቅ ተማጽኖ እምቢ ብሎ የግብርና ኑሮውን ይመራ ነበር።
ዛሬስ ? ዛሬ እነ ዘሪሁን ተሾመ ይፏልሉበት የነበረው የክብ ጠረጴዛ ውልቅልቁ ወጥቷል። ዘሪሁን ከደህንነት እንደ ሽልማት ያገኘው ‘ ዛሚ ሬዲዮ ‘ በኪሳራ ተዘግቶ እርሱና ሚስቱ ስደትን መርጠው self imposed exile ወደ እሜሪካ አቅንተዋል። የእነ ሚሚና ዘሪሁንን አይነት ገመና የተሸከመ ሰው አሜሪካም ብትሆን ቀላል ኑሮ አትሆነውም ። ሀበሻ ባየህ ቁጥር ‘ ምን ይለኝ ይሆን ? ” ብሎ መሳቀቅ በራሱ ከባድ ስቃይ ነው። ገበሬው ፕሮፌሰር ምንዳርያለው ዘውዱ ደግሞ ወደሚወደው የመምህርነት ስራ ተመልሷል ። ከዚህ በላይ ብድር በምድር poetic justice ይናራልን ?