>

ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ምን ላይ ነዉ?   (ሚኪ አምሀራ)

ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ምን ላይ ነዉ? (non-partisan analysis) 
ሚኪ አምሀራ
ኢህአዴግ እንደ ድርጅት cohesive ሁኖ እየተንቀሳቀሰ ነዉ ማለት ይከብዳል፡፡ ስብሰባቸዉ እንኳን ስለ ድርጅቱ እና የሀገሪቱ እጣ ፋንታ ሳይሆን እርስ በርስ መወነጃጀል ላይ ብቻ ያተኮረ ነዉ፡፡ ከሳምንታት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያደረጉት ስብሰባ እንኳን አንት ነህ ጥፋተኛ፤ እናንተ ናችሁ ጥፋተኞች፤ ተጠያቂ ከሆንን ሁላችንም ነዉ እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ምናምን በሚል ንትርክ ነበር ያበቃዉ፡፡ 
አንድም ቁም ነገር ሳይወራበት ስብሰባዉ እንዳለቀ ሰምተናል፡፡አለ የተባለዉ ኢህአዴግ ካለም ዶ/ር የአብይ እጅ ላይ ነዉ ያለዉ፡፡ከበረከት እስር ጋር ተያይዞም የኢህአዴግ አለመተማመን ሰፍቶ ድርጅቱ ምናልባትም የህልዉናዉ ጉዳይ አጠያያቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ሁለት ነገረሮቸች ይታዩኛል፡፡ ወይ አጠቃላይ የሚጠየቀዉ ተጠይቆ ሌላዉ ተባሮ ኢህአዴግ በአዲስ ሁኔታ ይዋቀራል፡፡ ወይ ቀስ በቀስ እራሱን በራሱ እየበላ ይከስማል፡፡ 
ህ.ወ.ሃ.ት
——-
ህወሃት አሁን ብቸኛዉ ተቃዋሚ ፓርቲ ነዉ ማለት ይቻላል፡፡ ባለፈዉ አመት ኦህዴድ የኢህአዴግ ተቃዋሚ ሁኖ ከርሞ ነበር ዘንድሮ ህወሃት ያን ቦታ ተክታ ክፉ ተቃዋሚ ሁናለች፡፡ ህወሃት ህዝቡን ሙሉ ለሙሉ ከጎኑ አሰልፏል፡፡ ዘላቂነቱ ግን አጠራጣሪ ነዉ፡፡ በተለይ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍል ህዝብ ነጻ ሁኖ ሲታይ የህወሃት ደጋፊዎችም ማጉረምረማቸዉ አይቀርም፡፡ ህወሃት አዲስ አበባ ላይ እያለ ባንድም ሆነ በሌላ መልኩ ወደ ትግራይ የሚሂዱ ጥቅማጥቅሞች እየቀነሱ ብሎም እየከሰሙ ሲመጡ ከህዝቡ በኩል የሚመጣዉ የኑሮ ጫና የህወሃትን ፕሮፖጋንዳ እስከመጨረሻዉ አሁን በተቀበለበት ሁኔታ ይዞ መዝለቅ ሊከብደዉ ይችላል፡፡ ነገር ግን ህወሃት ባንዱ ባይሳካ እንኳን በሌላኛዉ መንገድ ህዝቡን አሳምነዋለዉ በሚል ሁለት እና ሶስት ጠላት የሚል ነገር አዘጋጅቷል፡፡አንደኛዉ ዶ/ር አብይ የትግራይ ጠላት እንደሆነ በደንብ ፕሮፖጋንዳ ሰርቶበታል፡፡ ሁለተኛ የአማራ ህዝብ ጠላቱ እንደሆነ ጦርነት ሁሉ እንደሚኖር ሰብኳል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ እንደ ጠላት የያዘዉ ኢሳያስን/ኤርትራን ነዉ፡፡ የኤርትራን ጉዳይ በጥንቃቄ ነዉ የያዙት፡፡ ቢያንስ የአማራ ህዝብ እና ዶ/ር አብይ ጠላቶቻችን ናቸዉ በሚሉት መንገድ በገሃድ በየቀበሌዉ ፕሮፖጋንዳ አይሰሩበትም፡፡ የኤርትራን ጉዳይ አለዝበዉ ነዉ የያዙት፡፡ ሁለቱ ጠላት ያሏቸዉ ካልሰራላቸዉ ኢሳያስን እንደ ሶስተኛ አማራጭ ይጠቀማሉ፡፡ ይሄን ሶስት አማራጭ አሟጠዉ ስለሚጠቀሙ ህወሃትን ከህዝቡ መለየት ከባድ ያደርገዋል ወይም ጊዜ ይፈጃል፡፡
አረና ይህ ነዉ የሚባል ስጋት በህወሃት ላይ የሚጥል አይመስልም፡፡ አረና ልክ እንደሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሚዲያ ላይ እንጅ መሬት ላይ ይህ ነዉ የሚባል የተዋቀረ ሲስተም የለዉም፡፡ ነገር ግን እነ አብርሃ ደስታ ከእነ ዶ/ር አብይ ጋር አዲስ አበባ ከተገናኙ በኋላ ደፍረዉ ህወሃትን የመቃወም እና ወደ ሴንተር ፖለቲክስ የመምጣት ሁኔታ ይታያል፡፡ ምናልባትም ጠቅላይ ሚኒስቴሩ እኒህን ሽማግሌወች አስወግዳችሁ የህዝባችሁን እጣ ፈንታ ወስኑ፡፡ በሌቦች እና በሽማግሌወች ሳይሆን የትግራይ ህዝብ ፍላጎት የሚረጋገጠዉ በናንተ በወጣቶች ነዉ ብሎ ያበረታታቸዉ ይመስላል፡፡ ነገር ግን አረናም ለረዥም ጊዜ ህወሃትን ከመቃወም ይልቅ ሲደግፍ ስላሳለፈ አሁን ይህ ነዉ የሚባል ተጽእኖ የለዉም፡፡ ምናልባት በቀጣይ ወራቶች ለዉጥ ካለ የምናየዉ ይሆናል፡፡
ኦ.ዴ.ፓ/ኦ.ህ.ዴ.ድ
——-
ኦዴፓ መንግሰት ነዉ፡፡ ኢዲስ አበባ ላይ በብቸኝነት ነዉ ያለ ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን የኦነግ አንዱ ክፍል ከመጣ በኋላ ጊዜዉን እና ጉልበቱን በምእራብ ወለጋ አካባቢ በማድረጉ እሱም ቢሆን የመሃል ሀገሩ ፖለቲካ ላይ ሰከን ባለ ሁኔታ ሚናዉን እየተወጣ አይደለም፡፡ ኦሮሚያ ሰፍቶበታል፡፡ በየአቅጣጫዉ የተለያየ ፍላጎት አለ፡፡ ብዙ ፓርቲዎች በክልሉ አሉ፡፡ እራሳቸዉን እንደ ፓርቲ የሚቆጥሩ ግለሰቦችም አሉበት፡፡ ከእነሱ ጋር deal ማድረጉ በራሱ አንዱ ትልቁ ፈተና ነዉ፡፡ ኦህዴድ በፕሮፖጋንዳ በኩል ጥሩ ነዉ፡፡ በፊትም ወደ ስልጣን ሲመጣ በፕሮፖጋንዳ ሌሎችን በልጦ ነዉ የመጣዉ፡፡ ህወሃት ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሮፖጋንዳ የተበላዉ ባለፈዉ አመት በኦህዴድ ነበር፡፡ የዳዉድ ኢብሳዉን ቡድን በፕሮፖጋንዳ ማለት ይቻላል ከህዝቡ የነጠሉት፡፡ ይህ ቡድን ከህወሃት ጋር ግንኙነት እንዳለዉ፤ ትግሬወች አብረዉ ሲዋጉ እንደተያዙ በመግለጽ፤ ባንክ ዘረፋ አና መሰል ሁኔታወችን አጉልቶ በማዉጣት ባንዴ በህዝቡ ዘንድ ጥርጣሬ እዲገባ በማድረግ እጁን አስገድዶ ዉንብድናዉን እንዲያስቆም ያረገ ይመስላል፡፡ከዛም በላይ አሁን ኦዴፓ ሌሎች ሃላፊነቶች አሉበት፡፡ ከመሃል ሀገር ፖለቲካ ራቅ ያሉ እንደ ሶማሌ እና ጋምቤላ አይነት ክልሎችን የበላይ ጠባቂ ነዉ፡፡ ስለዚህም በእነዚህ አካባቢወች የሚነሱ እሳቶችንም ማጥፋት ይጠበቅበታል፡፡ ኦዴፓ አንድ ትልቅ አድቫንቴጅ ያለዉ በኦሮሚያ ክልል ዉስጥ ከዚህ በፊትም ተቃዋሚ ፓርቲወች ስለነበሩ ከእነሱ ጋር እንዴት መስራት እንዳለበት ያዉቃል፡፡ ስለዚህም ኦዴፓ ሲያዩት ደካማ ቢመስልም ልምድ ስላለዉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንዴት ማሸነፍ እንዳለበት የሚቸግረዉ አይመስለኝም፡፡ነገር ግን ኦዴፓም በተደጋጋሚ ኮምፓሱ ሲጠፋበት አይተናል፡፡ ነገር ሲበላሽበት ወደ ፕሮፓጋንዳዉ ይመለሳል፡፡ ለምሳሌ ጌታቸዉ አስፋ የሚል ጩኸት ይዞ ሊመጣ ይችላል ወይም ሌላ አንድ ነገር፡፡
አ.ዴ.ፓ/ብ.አ.ዴ.ን
——-
አዴፓ ስሙን፤ አርማዉን እና አንዳንድ ነገሮችን ከቀየረ በኋላ የፖለቲካ እንቅስቃሴዉንም አብሮ ለመቀየር ፍላጎት ቢያሳይም ከፍተኛ የሆነ የአቅም እጥረት ይታይበታል፡፡ ነግሮችን ቀድሞ ያለመገንዘብ፤ ለዘብተኛ የመሆን (አልፎ አልፎ የዝብርት ፓርቲ ይመስላል) እና ፓርቲዉን በርዮተ አለም ደረጃም ሆነ በፕሮገራም ወደ ፊት አስፈንጥሮ ይመራል የሚባል ተስፋ የሚጣለበት ሰዉ አለመዉጣቱ ችግሮቹ ናቸዉ፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሰዉ እጥረት አለበት፡፡ ከታችኛዉ የአመራር ከፍል ጋር የግንኙነት መስመር የተበጠሰ ይመስላል፡፡ ምክንያቱም በአንዳንድ አካባቢ የሚነሱ ችግሮች የላይኛዉ ክፍል ልክ እንደኛ በሚዲያ ነዉ የሚሰማዉ፡፡ ከቁጥጥሩ ዉጭ የሆኑ ቀበሌወች፤ ወረዳወች መኖሩ ምናልባትም ብዙዉ የአደፓ አመራር ብዥታ ዉስጥ መሆኑን ያሳያል፡፡ በተለይም ታችኛዉ ክፍል የምናገባኝ ስሜት አዳብሯል፡፡ አዴፓ ከፍተኛ የሆነ የ Public relation ችግር ከበፊትም ጀምሮ አለበት፡፡ ፕሮፖጋንዳ እንዴት እንደሚሰራ እንኳን አያዉቅም፡፡ አሁን ላይ ክልሉ አካባቢ የሚፈጠሩ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ይመስላል፡፡ በተለይም የክልሉን ጸጥታ እንደገና ለመቆጣጠር በሚመስል መልኩ የድሮ አባሎቹን (ወታደራዊ መኮነኖቹን) ወደ ስልጣን መልሷል፡፡ ይህ ጥሩ ነገር ቢሆንም አዴፓ ጥሩ ጥሩ የፖለሲ እና የፖለቲካ ንቃተ ህሊና ያላቸዉን ሰወች በተለይ ወጣቶች መሳብ ካልቻለ የድርጅቱ የአመራር ድርቀት አሁንም ይቀጥላል፡፡ በእርግጥ እንደ እነ መልካሙ ተሾመን አይነት ብሄርተኞችንም አስገብቷል፡፡ ነገር ግን ገና የተለማመዱት አይመስሉም ድርጅታችን ብለዉ በድፍረት ሲከላከሉ አላየነም፡፡ ምናልባት የነበሩበት ቦታ ባንዴ እንደዛ እንዳይሆኑ አድርጓቸዉ ይሆናል፡፡ ወይም የድርጅቱን organizational culture and climate እስኪለማመዱት ሊሆን ይችላል ድምጻቸዉ የጠፋዉ፡፡ሰሞኑን ያወጣዉ መግለጫ ምናልባት እራሱን እንደገና ለማነቃቃት እየሞከረ ይመስላል፡፡
አብን ዋና የአዴፓ ተግደርዳሪ ነዉ፡፡ አብን በብዙ ወጣቶች ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ ድርጅት ነዉ፡፡ አዴፓ እንደ ኦህዴድ ተቀናቃኝ ፓርቲ handle የማድረግ ልምድ የለዉም፡፡ ስለዚህም አዴፓ ከዚህ ፓርቲ ጋር ያለዉ ግንኙነት እና እንዴት react እንደሚያደርግ መተንበይ ያስቸግራል፡፡ አብንም እንደ አረና ወይም የኦሮሞ ፓርቲዎች ልምድ የለዉም፡፡ አብን በራሱ እንዴት ከገዥዉ ፓርቲ ጋር መስተጋብራዊ ግንኙነት እንደሚፈጥር ለመተንበይ ያስቸግራል፡፡ ባጠቃላይ የአማራ ህዝብ በዚህ ዙሪያ ልምድ የለዉም፡፡ እናም በቀጣይ ምን እንደሚሆን ማወቅ ትቂት አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ ለጊዜዉ ገግነን ጥሩ ላይ ናቸዉ፡፡
ደ.ህ.ዴ.ን
——
ደህዴን ፈርሷል ማለት ይቻላል፡፡ እንደ ፓርቲ ክልሉን መቆጣጠር አልቻለም፡፡ በተለይም የሲዳማን የክልል እንሁን ጥያቄ በአወንታ ከመለሰ በኋላ ደህዴን በሌሎች ብሄሮች አይን legitimacy የለዉም፡፡ የደህዴን ሊቀመንበርም ከደህዴን ይልቅ ለኦህዴድ የምትቀርብ ትመስለኛለች፡፡ እሱ ብቻ አይደለም፡፡ የደቡብ ክልል ፕሬዝደንት የሆነዉ አቶ ሚሊየን እልም ያለ የሲዳማ ብሄርተኛ መሆኑ እና ምናልባትም ሲዳማ ክልል ሲሆን እሱ እራሱ የክልሉ አስተዳዳሪ የመሆን ፍላጎት ስላለዉ ወይም የወደፊት የፖለቲካ ህይወቱ ከሲዳማ ጋር ስለሚሆን የደቡብ ክልልን አሁን ባግባቡ እየመራ አይደለም፡፡ ሲዳማንም ላለማስቀየም እና የፖለቲካ ነጥብ ላለመጣል ደቡብንም አሁን ላይ አስቀይሞ ከስልጣኑ እንዳይባረር አድርጎ አዝረክርኮ እየመራዉ ነዉ፡፡ ሰዉየዉ በሌሎች ብሄሮች ዘንድም ተቀባይነት የለዉም፡፡ እንዲያዉም ክልሉን ለማፈረስ የተላከ እየተባለ ይወራበታል፡፡ክልሉ ፈርሷል አሁን ጥያቄዉ አዲሱ አወቃቀር እንዴት ይሆናል የሚለዉ ብቻ ነዉ፡፡ ደቡብ ክልልም በብሄሮች ስለተሸነሸነ ይህ ነዉ የሚባል ተቃዋሚ ፓርቲ የለም ተቀባይነትም የማግኘት እድሉ ጠባብ ነዉ፡፡
Filed in: Amharic