>
8:56 pm - Tuesday July 5, 2022

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትክለኛው ገጽታ!  (አቻምየለህ ታምሩ)

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትክለኛው ገጽታ! 
አቻምየለህ ታምሩ
የአገሪቱ ከፍተኛው ባለሥልጣን  ጠቅላይ ሚንስትሩ የተገኘበት ይህ መድረክ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ከሚወሰንባቸው መድረክ አንዱ ነው። በዚህ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ከሚወሰንባቸው  መድረኮች አንዱ በሆነው በዚህ ጉባኤ  ከሁለቱ የኢትዮጵያን  ሕዝብ ሰባ ከመቶ በላይ ከሚሸፍኑት  አንዱ  የሆነው አማራ ግን  አልተወከለም ወይንም  ባለጊዜዎቹ እንዲወከል አልፈለጉም ። ይህ በአጋጣሚ  የተደረገ አይደለም!  ይህ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትክክለኛ ገጽታ ነው። ላለፉት ሀያ ሰባት ዓመታት ሁሉ የሆነው ይህ ነው።
«ለውጡን እናግዝ»  የሚሉን ሰዎች  እናግዝ እያሉን ያለው ይህንን  አማራ መቶ በመቶ ከጨዋታ ውጭ የተደረገበትን ሴራ ነው።  የተጀመረውን  የለውጥ ሂደት እንዳይደናቀድ አግዙ  እየተባልን ያለነው  አማራን  እንዲህ እያገለሉና እንዲገለል እያደረጉ ከአማራ የጸዳ አካባቢ ለመመስረት እንደተንቀሳቀሱ ሁሉ  የኢትዮጵያን  ፖለቲካ ከአማራ ለማጽዳት እያደረጉት ያለውን ደባ ነው።  ከአማራው መካከል የወጡ ጉዳይ ፈጻሚዎትም  በውጭም በውስጥም  ሆነው ለአማራ አንዳች  ነገር ጠብ ያለለት ይመስል «ለውጡን እናግዝ» እያሉ ከአማራ አንጻር የቆሙ  ጎሰኛ ባለጉዳዮችን እያገለገሉ አማራው ግን ተጠናክሮ እንዳይደራጅ  የሚያደነዝዙት አማራው እንዲህ የተገለለበትን እንደለውጥ ቆጥረውት ነው።
እስቲ የተጀመረው የለውጥ ሂደት እንዳይደናቀድ አግዙ ስትሉ የምትውሉ ለአማራው የትኛውን ነው ለውጡ?  ከታች የምታዩዋቸው  ስድስቱ  ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከዛሬ ሀያ ሰባት ዓመታት በፊት በሐምሌ 1983 ዓ.ም.  በወያኔ፣ በሻዕብያና ኦነግ  አጋፋሪነት  አማራን አግልለው  በኢትዮጵያ ምድር  ሰላምንም ዲሞክራሲንም ለመቅበር በአፍሪካ አዳራሽ  በተካሄደው «የሰላምና ዲሞክራሲ» ኮንፍረንስ በአንድም በሌላው መንገድ ተሳታፊዎች  ነበሩ  አልያም ወኪሎቻቸው ተሳትፈዋል።   ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊት ዋና ተዋናይ የነበረው ሻዕብያ በዚህ መድረክ ባይገኝም   በኢትዮጵያ ጉዳይ ወሳኝ ሁኖ «ጠረጴዋው» ላይ ግን ዛሬም አለ።   ዶክተር ብርሃኑም  ቢሆን ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊት የሽግግር መንግሥት ተብዮው  ኮንፍረንስ ተሳታፊና ታዛቢ  የነበረው  የጉራጌ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ  ግንባር አባል ነበር።
ዛሬ የጎደለው መለስ ዜናዊ  አለመኖርና  ከ27 ዓመታት በፊት በአምስት ድርጅቶች የተወከለው  ኦሮሞ ዛሬ በሶስት ድርጅቶች መወከሉ  ብቻ ነው። ሰዎቹ ኢትዮጵያን ቢወክሎ ጥያቄ ባልተነሳባቸው ነበር። ሆኖም  ሰዎቹ የወከሉት ኢትዮጵያን ሳይሆን  ነገዳቸውን  ብቻ  ነውና የተቀረው ነገድ  በነሱ ውስጥ ራሱን ባያይ  አይፈረድበትም።
ዛሬም፣ ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊትም  አንድ ተመሳሳይ ይታያል። ይኸውም ዛሬም ከሀያ ሰባት ዓመታትም በፊት   አማራው የለም።    ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊት በአማራ ጥላቻ የናወዙት  እነዚህ ስድስቱ ወይንም ወኪሎቻቸው  አማራ እንዳይገኝ አድርገው ከፕሮግራማቸው በማውጣጣት ሕገ መንግሥት  ያሉትን የቅሚያና የግድያ ደንብ አዘጋጅተው ነበር።  እነሆ  ዛሬም  ከ27  ዓመታት በኋላ ስድስቱም የ27 ዓመታት የሥራ ውጤታቸውን ለመመረቅ በመድረክ ተገናኝተው ሽር ብትን እያሉ ናቸው።
እነዚህ ስድስቱ  ዛሬ ከሀያ ሰባት ዓመታት በኋላ ለውጥ፣ ለውጥ እያሉ ቢሰክብኩም  እውነቱ ግን  አንዳችም  የመዋቅርና የሕግ ለውጥ ሳያካሂዱ በተመሳሳ መንገድ [በአብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ በጎሳ ፌድራሊዝም፣ ሕጋዊነት በሌለው ሕገ መንግሥት፣ ወዘተ]   በመሄድ የመንፈስ አባታቸውን  የመለስ ዜናዊን ራዕይ እያስቀጠሉ የተለየ ውጤት ማምጣት ይቻላል  ብለው ያታክቱናል።  ዛሬም ችግሩን በፈጠረው አስተሳሰብ እየተመራን፣ አገዛዙ የተዋቀረበት ርዕዮተ ዓለም ሳይቀየርና የመዋቅርና የአደረጃጀት  ለውጥ ሳያደርጉ የተለየ ውጤት  ሊያመጡና አገራዊ ተቋማትን ሊፈጥሩ ያስባሉ!
ደግነቱ ዛሬ ትናንት አይደለም! «ለውጡን እናግዝ» ብለው የተኮለኮሉት  የኛዎቹ አደንዛኞችም ሆኑ ባለጉዳዮቻቸው እነ ዐቢይ  ባይፈልጉትም አማራው በሚገርም ፍጥነት ራሱን ለመከላከል  ተንስቷል፡፡ ካሁን በኋላ እንደ ሰማንያ ሶስቱ  ለዳግም እርድ የሚዘጋጅ አማራ የለም! ያለርህራሔ ኅልውናውን ለመታደግ ተነስቷል!
Filed in: Amharic