>

የህዝባዊ መሪዎች ደህንነት ዋስትና ይገባዋል (ቾምቤ ተሾመ)

የህዝባዊ መሪዎች ደህንነት ዋስትና ይገባዋል

ቾምቤ ተሾመ

 

በሰይፍ የኖረ በሰይፍ ይሞታል የሚባለው አባባል በተለምዶ እውነት ቢመስልም  ለብዙ ጨካኝ ገዳይ መሪዎች ግን እድሜያቸውን ጨልጠው በጠጡ ማግስት ነው ሰይፉ የሚጎበኛችው ፤ብዙ አምባገነኖች የብዙ ህዝብ ደም እንደ ዉሀ ካፈሰሱ በኋላ እድሚያቸውን  ጨርሰው ወይ ስልጣናቸው ከእጃቸው አምልጦ ህዝብ በአመጽ ያጠፋቸዋል ወይም ደግሞ አርጅተው ጃጅተው በበሽታ ይሞታሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ታሪክን ዞር ብለን ብናይ፤ ቦኒቶ ሞሶሎኒ አገዛዙን የተቃወሙ ጣሊያኖችን ካሰረና ከገደለ በኋላ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በአለም የተከለከለ የመርዝ ጭስ ተጠቅሞ  የኑጹሃን ደም ካፈሰሰ በኋላ፤ ከስላሳ ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ከስጨፈጨፈ ብኋላ የሞት ጽዋን ተዘቅዝቆ የቀመሰው ጣልያን ተሸንፋ የአሜሪካን ጦር ሲቆጣጠራት ወደ ስፔን ሊያመልጥ ሲሞክር ነው፡ ጆሴፍ ስታሊን ከሶስት ሚሌየን ሰው በላይ ከረሸነ በኋላ በ73 አመቱ በልብ የማጥቃት በሽታ አልጋው ስር በሽንቱ ርሶ ሞቶ ነው የተገኝው፤ ሂትለር ከሃምሳ ሚሊየን ፤ሰው በላይ የሰው የጥፋት ምክንያት ሆኖ ከስድስት ሚሌዬን ይሁዳዎችን በመርዝ ጭስ አጥፍቶ በመጨረሻው ሰአት ከእጮኛው ጋር ተጋብቶ 56 አመቱ ነው ምርዝ ጠጥቶ የሞተው ፡ማኦ ዜዱንግ  ኮምኒዝምን ለመመስረት የባህል አብዮት ብሎ ከብዙ ሚሊየን የሚጠጉ ቻይኖች እንዲሞቱ ካደረገ ብበኋላ የ82 አዛውንት ሆኖ በመታመም ነው የሞተው፡፡ የቼሊው አንባገነን አጎስቲኖ ፒኖቼ ቺሊን በግድያ የምድር ሴኦል ካደረገ በኋላ በ91 አመቱ ነው የሞተው ፤ ወደኛ ሀገር ስንመጣ ኮለኔል መንገስቱ ኋይለማርያም በነጭ ሽበር በጥርጣሬ በየመንገዱ ላይ ወጣት ሲያስገድል በቀይ ሽበር ደግሞ በየቀበሌው ወጣት ሲያስጨፍጨፍ ከርሞ ዛሬ ዝምባጉዊ ጸሃይ እየሞቀ ይኖራል፡ ከዚያም ዘረኛው መለስ ምርጫ መሽነፉን ሲያውቅ በአልመህ ግደል ትእዛዝ በአጋዜ ጦሩ በአዲስ አበባ ብቻ ክሁለት መቶ በላይ አስረሽኗል ከ750 በላይ የድሀ ልጆችን አካለ ስንኩል አድርጎ ካንሰር አንኳኩቶ ባይወስደው ኖሮ ለረጅም ጊዜ ይኖር እንደነበር ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ምክንያቱም ሞትን ከሺህ ኪሎ ሜትር ስለሚያሸት  የአዲስ አበባ መንገድ ያዘጋ የነበረው ሲያልፍ ሳይሆን ገና ለማለፍ ሲያስብ ነበር፡፡ ካለፈም በግራ ያልው ህዘብ ጸሀይ ወደምትወጣበት ፤በቀኝ ያለው ደግሞ ጸሃይ ወደምትጠልቅበት የግድ መዞር ነበረበት፤ ተገዶ! ከዚህ ሁሉ ታሪክ የምንማረው አምባ ገነኖች ለህይወታችው ፈሪዎች ስለሆኑ የሌላውን ለማጥፋት ችኩል እንደሆኑ ሁሉ የራሳቸው ህይወት ለመከላከል ግን ቆቆች መሆናቸውን ነው፡፡

አሁን ደግሞ ታላላቅ የሰላምና የእኩልነት አቀንቃኝ የሆኑ መሪዎችን ደግሞ እንመልከት ፤ አብርሃም ሊንከን 16ኛው የአሜሪካ መሪ  የባርነት (ሰውን እንደ እቃ የሚቸረችር) ኢኮኖሚ በአሜሪካ እዲቀጥል በፈለጉ ግዛቶች የተነሳውን የምገንጠ ጥያቂ ውድቅ አድርጎ በባርነት ቀንበር የነበሩ ጥቁር አሜሪካ ዜጎችን ነጻ አውጥቶ፤ አሜሪካንን ለመገንጠል የተነሱትን ግዛቶች አሸንፎ አሜሪካን የማትከፋፈል ሀገር መሆኖን ያስመሰከረ የአሜሪካን እንዲሁም በአለም የተመሰከረለት ታላቅ መሪ ነው ፡፡ ነገር ግን የባርነት አቀንቃኝ  የሆነ አንድ እኩይ ሰው ሊንከን ትያትር ወደ ሚያይበት ክፍል ተደብቆ ገብቶ አብርሃም ሊንከንን መግደል ችሏል፡፡ የሊንከን መሞት በባርነት ላይ የተገኘው ድል ጥሩ መሰረት እንዳይዝ፤ ጥቁር አሜሪካኖችም ሙሉ ዜግነት መብታቸውን ለብዙ አመታት እንዳይጎናጸፉ ምክንያት ሆኗል፡ ሌላው አንጋፋ አሜሪካዊ ማሪቲን ሉተር ኪንግ በሰላማዊ መንገድ ብቻ ተጠቅሞ ነጭ አሚሪካዊያንና ጥቁር አሜሪካዊያን አብረው የተሻለ አሜሪካ እንዲመሰርቱ የታገለ የሰላም ሰው ነበር ፤ ነገር ግን የጥላቻ ካንሰር አእምሯቸውን ላሰከረው ግን መወገድ ያለበት ጠላት ነበር ፡ ስለዚህም ካረፈበት ሆቴል ባልኮኒ ላይ እንዳለ አልመው ገደሉት፡፡ ሌላው የጥላቻ ኢላማ የሆነው ታላቁ የሰላማዊ ትግል መስራች ሞሃተመ ጋንዲ ነው፡፡ ሞሀተመ ጋንዲ በሂንዱዎችና በሙስሊም ሂንዱዎች መሀከል የተነሳውን ግጭት ለማበረድ ያላደረገው ነገር የለም ነበር ፡ ሁለቱም የህንድ ዜጋዎች ከስሜታዉነት ወጥተው ለችግሩ መፍትሄ እንዲያገኙለት ብዙ ጥረት አድርጓል፤ ነገር ግን የካቲት 30 1948 ጋንዲ የምሽት ጸሎቱን ሊያደርስ ወደ ዴሊህ ሲሄድ አንድ ሂንዱ አክራሪ  ወጣት ተኩሶ ገደለው፡፡ ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር ህዝብ የሚወዳችው፤ህዝብን በፍቅር የሚቀርቡ ልበ ቅኑዎች ለመሰሪዎች ቀላል ኢላማ መሆናቸውን ነው፡፡

ከዚህ ተምረን ጥንቃቄ ማደረግ የሚገባን ነገሮች አሉ በተለይ እንደ አብይ ያሉ ህዝባዊ መሪዎችን በተመለከተ፤ ኢትዮጵያዊያን 45 አምታት ሙሉ አቅጣጫችን ስተን እርስ በርሳችን ስንጠፋፋ ቆይተን ሁላችንንም ካለበት ዝቅጠት ሊያወጣ ዶ/ር አብይ መሀመድ የተሻለ ርአይና ብቃት ይዞ መጥቶ እየመራን ነው፤ ነገር ግን  በስምንት ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ህይወቱ ለማጥፋት የተቀናበረ ሙከራ ተደርጎ ከሽፋል፡ ሊያጠፉት የሞከሩት ሴረኝች አሁንም መቀሌ መሽገው ማሴራቸውን አላቆሙም በሌላ በኩል ደግሞ እንደነ ጸጋዬ አራርሳ ያሉት ጽንፈኛ ዘረኞች ያላቋረጠ ዘመቻ በዶ/ር አብይና ኦቦ ለማ መገርሳ ላይ እያካሄዱ ነው፡ እነዚህ ዘረኛ ወፈፌዎች እነሱ ጠመንጃ አንሰተው መተኮስ አይጠበቅባቸውም ፤የለባቸውም ፤ነገር ግን በጸጋዬ አራርሳ የዘረኛነት መርዝ የተለከፈ አንድ ጀብደኛ በወያኔ ገንዘብ እና መሳሪያ አቀባይነት ትልቅ ጉዳት ሀገራችን ላይ ሊያመጡ ይችላሉ ፡፡

ምንም እንኳን እነ አብይ በህዝባዊ ጸባያቸው ከህዝብ ጋር መደባለቅ ቢፈልጉም ሀገር  ሊገጥም ከሚችለው ብሄራዊ ቀውስ አንጻር ይህ ፍላጎታቸው በህዝብ ደህንነቱ ሊገደብ ይገባዋል፡፡ መቶ በመቶ የአካባቢው ስይፈተሽ ህዝብ መሀል ይዞ መግባቱ አስፈላጊ ላልሆነ አደጋ እነርሱንም ሀገሪቱንም ማጋለጥ ስለሆነ ጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባል፡፡ የጋንዲን ልጅ ራጂቪ ጋንዲን ህይወት ያጠፋችው ቦንብ ታጥቃ ቅርጫት ሙሉ አበባ ለመስጠት የቀረበች በዘረኝነትና በጥላቻ የተበከለች ወጣት ሴት ናት፡፡

Filed in: Amharic