በንጹሃን ላይ ወንጀሎችን በመፈብረክና ብሎም ዜጎቹን በማሰርና በማሰቃየት የሚረካው ወያኔን ጠንቅቆ የሚያውቀው ወጣቱ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ይሄ ሁሉ ግፍ ይፈጸምበት እንጂ፣ የወያኔን የፍትህና የህግ ሂደት ከመታሰሩ ቀደም ብሎ በማህበራዊ ድረ -ገጾች ላይ የጦመረው በዚህ መልኩ ነበር ‘‘ወደፊት የሚደርስብኝን ግፍም ሆነ እስር ኣልፈራም። በምታስርበት ጊዜ ከሚፈበረክብኝ ክስ ራሴን መከላከል ያለመቻሌን ሳስበው ግን ያስፈራኛል። ነበር ያለው።
የህብረተሰቡ ብሶት ብሶታችን ነው ”ስለሚያገባን እንጦምራለን” ያሉት ጦማሪዎች በጡንቸኞች እጅ ከወደቁ 79 ቀናቶች ኣልፎኣቸዋል። በነገው ዕለት ማኅሌት ፋንታሁን፣ አቤል ዋበላ እና በፍቃዱ ኃይሉ በአራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ስለሆነ ኣጋርነታችሁን እንድታሳዩዋቸው ዞን ዘጠኞች ኣሳስበዋል። እኛም የምንለው ኣጋርነትዎን በማሳየት የሞራል ስንቅ ይሁኗቸው ነው።