>

በደቡብ ኢትዮጵያ ግልጽ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተካሄደ ነው!!! (ዘመድኩን በቀለ)

በደቡብ ኢትዮጵያ ግልጽ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተካሄደ ነው!!!

ዘመድኩን በቀለ
* ★ ኧረ ኡኡኡ የወገን ያለህ፣ የሀገር ያለህ
የጌዲኦ ህዝብ እንደ ቅጠል እየረገፈ ነው!!
 
ክቲቪስት የላቸውም። ስለ እነሱ ሁኔታ ግድ ብሎት የሚዘግብላቸው ጋዜጠኛም የላቸውም። የሰብዓዊ መብት ቶቆርቋሪ ድርጅቶች፣ የእንባ አባሹም፣ እንባ አፍሳሹም ተቋም አያውቃቸውም። የህዝብ ተወካይም ተጠሪም የላቸውም። ቀይ መስቀልም፣ ቀይ ጨረቃም ዞር ብሎ አያያቸውም። ሀገር አቀፍ፣ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም ዘንግተዋቸዋል። አያውቋቸውም!!
•••
ባለ ተራዎቹ አንደኛ ደረጃ ዜጎች ከሶማሌ ክልል በመፈናቀል ሰበብ አዲስ አበባ መጥተው ኮንዶሚንየም በነፃ፣ የኪስ ገንዘብ በነፃ፣ የቤት መሥሪያ ቦታ በነፃ፣ ቤትም በነፃ ይሰጣቸዋል። ዝቅተኛ ደረጃ የተሰጣቸው ዜጎች ግን በጅምላ የዘር ማጥፋት ወንጀል ይፈጸምባቸዋል። ይሄ ወንጀል ነው። ይሄ ግፍ ነው። ይሄ ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው። ይሄ ዓለም አቀፍ ወንጀል ነው። ሁሉም ተጠያቂ ነው። ያፈናቀለውም፣ በረሃብ እየፈጃቸው ያለውም ተጠያቂ ነው። በህግም በእግዚአብሔር ፊትም ተጠያቂ ነው።
•••
የገዢው ፓርቲ፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ለእነሱ ደንታ አልሰጥ ብሏቸዋል። ዐቢይ አህመድ የሚያስጨንቀው የኤርትራ ሰላም ውሎ ማደር፣ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ኢትዮጵያዊ ሆነው እንደ ዜጋ መቆጠር፣ ያልተጣሉትን የሶማሊያና የኬንያ መሪዎች ለማስታረቅ በሚል ሰበብ ውሎ አዳሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ማድረግ ሆኗል። አዲስ ዘመንና ሌሎሎች ጋዜጦች፣ ኢትዮጵያ ራዲዮ፣ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን፣ ራዲዮ ፋና፣ እና ሌሎችም እንዳይዘግቡት በዓዋጅ የተከለከሉ ይመስላል። ማኅበራዊ ሚድያው በቄሮ ዱላ ተጥለቅልቋል። በወልቃይትና ራያ ጥያቄ ታጥሯል። የደቡብ ክልል መንግሥት ጭጭ ብሏል። አፈናቃዩ የኦሮሞ ክልል ጮጋ ብሏል። ሁሉም ጮጋ ብሏል።
•••
ህጻናት በእናታቸው ዘእቅፍ እንዳሉ እየሟሙ ነው። ረሃብ እንደቅጠል እያረገፋቸው ነው። አዛውንቶች ከመሬት እየተጣበቁ፣ ጎልማሶች ክንዳቸው እየዛለም ነው። መሬታቸውን ኦነግ ቀምቷቸዋል። ንብረታቸውንም ግማሹን ኦነግ፣ ግማሹን እሳት በልቶታል። ከመንግሥት የሥራ ገበታ ተፈናቅለዋል። ትምህርት ካቋረጡ አንድ ዓመት አልፏቸዋል።  ጤና ጣቢያ፣ ንጹህ የመጠጥ ውኃ የማይታሰብ ነው። እንዲህ ሆኖ ሳለ ግን ዐቢይ አህመድ የአዲስ አበባን የወንዝ ዳር ለማልማት ለአንድ ምሽት ራት መግብያ 5 ሚልየን ብር ትኬት ይሸጣል። ዜጋ ከዳር ሀገር በረሃብ እየጠረገ፣ እያስወገደ መሃል ሀገሩን ላስውብ ብሎ ይቀልዳል። የዘንድሮውስ የጉድ ነው።
•••
ጌዲኦዎች መንግሥት ባለበት ሀገር ራሳቸው ሀገር አልባ ሆነዋል። የታማሚው ብዛት ለጉድ ነው። ሰዎች እንደ እንስሳ ሳርና ቅጠል መብላት ጀምረዋል። አቅም ያላቸው ለመለመን ወደ ከተማ ደርሰው የሚቀመስ ይዘው ወደ ጫካ ሲመለሱ ቤተሰብ ሞቶ፣ ጓደኛ ረግፎ እያገኙ ነው። አሁን ላይ ሁላቸው ተስፋ ቆርጠዋል። የበጋ ፀሐይ የክረምት ዝናብ በላያቸው ላይ ያልቃል። እመኑኝ በዚሁ ከቀጠልን ሁላችንም የጌዲኦዎች ዕጣ ፈንታ በእጃችን ነው።
•••
በኢትዮጵያ ታሪክ እንዲህ እንዲህ አንድ ነገድ በተጠና መልኩ እንዲወገድ ሲደረግ ታይቶም ተሰምቶም የሚያውቅ አይመስልም። የመጀመሪያውም ሳይሆን አይቀርም። በተፈጥሮ አደጋ ረሃብ የፈጃቸው እንዳሉ ቢታወቅም መንግሥት አፈናቅሎ የፈጃቸው ግን ከጌዲኦ በቀር ሌላ ያለም አይመስለኝም። ወዳጄ ነግ በእኔ ነው። ዛሬ የእነዚህ የጌድኦ ወገኖቻችን በጅምላ በተጠና መልኩ ዘራቸው በረሃብ፣ በበሽታ እንዲጠፋ ሲደረግ ዝም ያልን ነገ በእያንዳንዳችን ስላለመድረሱ ምንም ዋስትና የለንም። የጌዲኦ ብቻ ሳይሆን በደቡብ ብዙ ብሔሮች በጅምላ ሞት እንደተፈረደባቸው ነው ተብሏል። ሌሎችም እንዲሁ ሰማይ የተደፋባቸው ሞልተዋል ነው የሚባለው።
•••
አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ዜጋ የሚታዩትና ጥያቄ ሳይጠይቁ መልስ የሚሰጣቸው፣ ጥያቄውን ራሳቸው አውጥተው፣ መልሱንም ራሳቸው የሚመልሱ፣ ጥያቄ ጠይቀው መልሱን በጉልበትና በትእግስት የሚጠብቁ የትግሬ፣ የኦሮሞና የዓማራ ነገድ አባላት ብቻ ናቸው እንደ ባለ መብት የሚምነሸነሹባት። ሌላው ብሔር ከነ መኖሩም አይታወቅ።
•••
ያለ መርፌ፣ ያለ ኪኒን፣ ያለ ጥይት፣ ያለ ቦንብ፣ ያለ መድፍ፣ ያለ ሚሳኤል፣ የጌዲኦ ህዝብ ዓይናችን እያየ የአቢቹና የለማ መንግሥት ከምድረ ገጽ እያጠፋቸው ነው። ተናግሪያለሁ። እንድረስላቸው። ቢያንስ የሚበላ ሰጥተናቸው እየበሉ ይሙቱ። ግፉ ለሁላችንም ነው የሚተርፈው። የእያንዳንዳችንን ቤትም ነው የሚያንኳኳው።
•••
የአብቹ መንግሥት ምላስ እንጂ ጆሮ እንደሌለው እወቁ። 3ሺ ዓማራና ጉራጌ፣ ደቡብም በለገጣፎ አፈናቅሎ አዲስ አበባ አይንህ ስር በረሃብ ልክ እንደ ጌዶዎች እየፈጀልህ ያለ መንግሥት ነው። መንግሥት የህዝብ ቁጥር ቅነሳ ላይ ያለ ይመስላል። ግድም አይሰጠውም። የአቢቹ መንግሥት አሁን የሚያስጨንቀው ኦሮሞ እንዴት ሞያሌን እንደሚጠቀልል፣ ደቡብን እንደሚሰለቅጥ፣ ጎጃምና ወሎን ኦሮሞ እንዴት እንደሚያደርግ እንጂ የሚጨነቀው ስለሌላው የሚያገባው አይመስልም።
•••
ዐማራና ትግሬን አባልቶ፣ ሌላውን አራቁቶ። ሀገሪቷን ስሟን ቀይሮ ኦሮማይዝድ ማድረግ የፈለገ ይመስላል። እናም ጎበዝ ለጌድኦ ህዝብ ድምጽ እንሁነው። በፈጠራችሁ ድምጻችንን እናሰማላቸው። ከ900 ሺህ ህዝብ በላይ በረሃብ ሊረሸን ነው። እንደ ቅጠል ሊረግፍ ነው። የሚበሉት ቅጠልና ስር እንኳ ጠፍቷል እየተባለ ነው። ወገን በየጥሻው ወድቋል። 3 ተኛ ደረጃ ዜጎች እየረገፉ ነው።
•••
እነ ታማኝ በየነ የሚሰበስቡት ገንዘብ ለእነዚህ ምስኪን ተፈናቃይ ዜጎች ቢውል ፈቃዴ ነው።  ይሄን ግፍ እያያችሁ ዝም ያላችሁ ባለሥልጣናት በሙሉ እግዚአብሔር ይይላችሁ። የእጃችሁን አግኙ። እናንት ፖለቲከኞች ፍርድ ሩቅ አይደለም። ቅርብ ነው።
★ እኔማ አሁንስ ራሱ ዐቢይ አህመድ መልኩን ቅዱስ ሚካኤልን አስመስሎ ሰይጣን እያስተዳደረን፣ እየገዛንም እየመሰለኝ መጥቷል። የቅድስት አፎሚያን ታሪክ ልብ ይሏል።
•••
በጌዲኦ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ይቁም !!
እኔም ጌዲኦ ህዝብ ነኝ።
የጌዲኦዎች ስቃይ ስቃዬ ነው። ሞታቸው ሞቴ ነው። 
ፍትህ ለጌዴኦ ተፈናቃዮች!!
ሻሎም!  ሰላም !
Filed in: Amharic