>

መጭው ግዜ የሚወሰነው ለመብታችን በምናደርገው ተጋድሎ ብቻ ነው!!! (ሀይለ ገብርኤል አያሌው)

መጭው ግዜ የሚወሰነው ለመብታችን በምናደርገው ተጋድሎ ብቻ ነው!!!
ሀይለ ገብርኤል አያሌው
 
 *  ‹‹ሁሉም ኢትዮጵያ ለአዲስ አበባ›› 
የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ 
 
እስክንድር የመርሕ ሰው ነው ላመነበት ለሕዝብና ለሃገር አንድ ሰው እንኳ ቢቀር ከአቋሙ የማያፈገፍግ ጽኑ ጀግና ነው!!!
የሕዝብ አደራ ከሚገባው በላይ እየተጫነበት መጥቷል:: ይህ ሰው ከምቾት ሕይወት አለያም ከስደት ተመላሽ አይደለም :: ያለውን ሁሉ ትቶ ስለ ሃገር ሲል በአስከፊ እስር ቤት ነው ያሳለፈው:: ሌሎች እሳቱ ሲብርድ ሰላም ሲሰፍን የገቡ የአጥቢይ አርበኞች በመንግስት ሃብት በአረቦች ድጋፍ አብጠው የተዳራጀ ሃገር አፍራሽ ዘመቻ ጀምረዋል:: እኛስ ሃገር ልናጣ እንገታችን ሊቀላ ሽብር የተክፍተብን ዜጎች ቃላትና ኡኡታ ብቻ ነው ተሳትፏችን??? ወይስ በምንችለውና ባለን አቅም ትግሉን ልንረዳ ተዘጋጅተናል::
መጭው ግዜ የሚወሰነው በምናደርገው እንቅስቃሴ ብቻ ነው:: እንደ እስክንድር አይነቱን ትላንት ከእስር የወጣ ትንሽ እንኳ ልረፍ ሳይል ትግሉ ግንባር ላይ የቆመን ጀግና በወሬ ብቻ ከተውንው ድጋፍና እገዛ ካላደረግንለት ተጠያቂው እኛና እኛ ብቻ ነን::
 
ጋዜጠኛና የዲሞክራሲ አክቲቪስት እስክንድር ነጋ እሁድ ከህዝብ ጋር ሊወያይ ቀጠሮ ይዟል!
የፊታችን እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የሚመክር ህዝባዊ ውይይት ሊደረግ እንደሆነ በረራ ጋዜጣ በዛሬ እትሙ ዘግቧል፡፡ በእለቱ ‹‹ሁሉም ለአንድ አዲስ አበባ›› በሚል መሪ ቃል ላይ ተመርኩዞ ‹‹ለአዲስ አበባ ምን ይደረግ?›› የሚለው ጥያቄ ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል፡፡ የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ለበረራ ጋዜጣ እንደገለፁት በውይይቱ ላይ ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ የአሁንና የወደፊት የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ጥናታዊ ፅሁፍና አቅጣጫ ጠቋሚ ሀሳብ ያቀርባል፡፡ እንዲሁም በውይይት መድረኩ ላይ ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ የስፖርት ቤተሰቦች እንዲሁም የህግ ባለሙያዎችና አክቲቪስቶች እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡
Filed in: Amharic