>

ከአራቱም አቅጣጫ የመጣው አዲስ አበባ ላይ እኩል ነዋሪ ነው! እኛ መጤና ነዋሪ ብለን አንለይም!" (ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ)


ከአራቱም አቅጣጫ የመጣው አዲስ አበባ ላይ እኩል ነዋሪ ነው! እኛ መጤና ነዋሪ ብለን አንለይም!”
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከአዲስ አበባ ህዝብ ጋር የመከረው!
* የአዲስ አበባ አስተዳደር በአዲስ አበባ ስም ለመደራደር የሕግም፣ የፖለቲካም፣ የሞራልም ውክልና የለውም።” 
 
 አቶ ታከለ አዲስ አበባን ወክለው ይደራደሩ ማለት አቶ መለስ በሕይወት ቢኖሩ አዲስ አበባን ወክለው ከትግራይ ጋር ይደራደሩ ማለት ነው”
. . . . .
“ዋናው ድክመታችን ድርጅት የሌለን መሆኑ ነው። ዛሬ የእናንተን ውክልና የምንጠይቀው ድርጅት ስለሌለን ነው። ምርጫው መቼም ተካሄደም መቼ እዚህ ከተማ ላይ ልዩ ጥቅም የሚል አንድ ቀበሌ፣ አንድ ወንበር አያሸንፍም። ይህን ለማድረግ እንደራጃለን! አዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም አላት የሚልን ለመታገል ክልሎች ሄደን እንቀሰቅሳለን። የማይደግፉን ክልሎች እንዳሉ ሁሉ የሚደግፉን ክልሎች እንዳሉ ማወቅ አለብን”
~~~
“የወሰን ድርድር አይደረግ ማለት ኮንዶሚኒዬም የደረሳቸው ሰዎች ቤታቸው አይሰጣቸው ማለት አይደለም። ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊሰጣቸው ይገባል። የፌደራል መንግስቱ ቤቱን እንዲያገኙ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት። በየት ሀገር ነው በትውልድ ቦታ ልዩ ጥቅም የሚጠየቀው? የኮንዶሚኒየሙን እጣ ተቃውሞ በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ ተደርጓል። ከመግለጫው እንደተረዳነው በሰልፎቹ የኦሮሞ አስተዳደር እጅ አለበት። በእነዚህ ሰልፎች ገጀራ፣ ዱላ ተይዞ ተወጥቷል። ሚስማር የተመታበት ዱላ አሳፋሪ ነው። መንግስት ይህን በይፋ ማውገዝ ነበረበት።
~~~
“የአዲስ አበባ መስተዳደር የእለት ተዕለት የአስተዳደር ስራ ከመስራት ውጭ፣አስር ቀንም ሌላም ጊዜ ይቆይ እስኪለቅ ድረስ በአዲስ አበባ ስም ለመደራደር የሕግም፣ የፖለቲካም፣ የሞራልም ውክልና የለውም። ይህ ይመዝገብልን። በሕዝብ የተመረጠ መስተዳደር እስኪመጣ ድረስ የሕዝብ ሰፈራም የድንበር ድርድርም መደረግ የለበትም። እኛ ችግራችን ከአቶ ታከለ ኡማ ጋር አይደለም፣ እኛ ራሳችን ኦሮሞ ነን፣ የሚያጣላን አስተሳሰባቸው ነው። አቶ ታከለ የመጡት ለአዲስ አበባ ሊሰሩባት እንጅ ሊሰሩላት ነው። አቶ ታከለ አዲስ አበባን ወክለው ይደራደሩ ማለት አቶ መለስ በሕይወት ቢኖሩ አዲስ አበባን ወክለው ከትግራይ ጋር ይደራደሩ ነበር ማለት ነው”
~~~
የአዲስ አበበና ኦሮሚያ ሊደራደሩ መንግስት ኮሚቴ አቋቁማል። የኦሮሚያውን የሚመሩት የኦዴፓ ከፍተኛ አመራር ናቸው። አዲስ አበባን የወከሉት የኦደፓ ከፍተኛ አመራር ታከለ ኡማ ናቸው። ኦሮሚያንም አዲስ አበባንም የወከሉት የኦዴፓ ከፍተኛ አመራሮች ናቸው። ይህ ድርድር አይደለም። ይህ ድራማ ነው።
~~~
ይህ አዲስ ድራማ አይደለም። ይህን ድራማ 1987 አይተነዋል። በ1987 ሕገ መንግስት ወጣ ተባለ። ያወጣው ሕዝብ አይደለም። ሕወሓት ነው። ምርጫ ተደረገ ተባለ። ኢህአዴግ ስልጣን በሕዝብ ለተመረጠ መንግስት አስረከብባለሁ ብሎ ነበር። ምርጫ ተደረገ ከተባለ በኋላ ኢህአዴግን ወክለው ዶክተር ነጋሶ መጡ። አዲሱን በሕዝብ የተመረጠ መንግስት የተባለውን ወክለው አቶ መለስ መጡ። ኢህአዴግ በነጋሶ በኩል አዲስ የተመረጠ መንግስት ወኪል ናቸው ለተባሉት መለስ መዶሻ አስረከቡ። አሁንም ሊሰራ የተፈለገው ይህ ድራማ ነው። ይህ ደራማ አዲስ አበባን አይወክልም።
~~~
አዲስ አበባን የምንመኛት ለአፍሪካ መዲናነት እንጅ ለአንድ ብሔር አይደለም። ይህን የሚሉትም የኦሮሞን ሕዝብ ይወክላሉ ብለን አናስብም። ከአራቱም አቅጣጫ የመጣው አዲስ አበባ ላይ እኩል ነዋሪ ነው። እኛ መጤና ነዋሪ ብለን አንለይም!”
~~~
በመጨረሻም ለተሰብሳቢው በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አማካኝነት ተነብቦ በድጋፍ የፀደቀ የአቋም መግለጫ
1) አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ እና የኢትዮጵያ እንጅ ማንኛውም ክልል ልዩ ጥቅም ሊጭንበት የማይችል ከተማ ነች
2) የአዲስ አበባ ወሰን፣ በከተሞች የሚደረጉ ሰፈራዎች ላይ በምርጫ የተመረጠ አስተዳደር እስኪኖር ድረስ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳይደረግ
3) የአዲስ አበባ ሕዝብ በሚቀጥለው ምርጫ ልዩ ጥቅም ለሚል አካል አንድ ድምፅ እንዳይሰጥ፣ ይህን ለማድረግ ስብሰባውን የጠራው አካል በሕዝብ የተሰየመ መሆኑ
4) እንቅስቃሴያችን ሰላማዊ መሆኑን የወሰንን መሆኑን በሙሉ ድምፅ ተስማምቶ ገልፆል።”
~~~
ማሰር እና ማፈን ለውጥ እንደማያመጣ ከትናንት ተግባራችሁ ተማሩ!!
በህልውናው ላይ የተጋረጠበትን አደጋ በሰላማዊ መንገድ ተናጋግሮ መፍትሔ ለማስቀመጥ የተሰበሰበውን የሸገር ወጣት ፌደራሎች አስለቃሽ ጭስ እየተኮሱ ትርምስ በመፍጠር በርካታ ወጣቶችን ለእስር ዳርገዋል – በአስቸኳይ ፍቱ!!
~~
በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ET 302 በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ያጡ 157 ሰዎች አምላክ ነብስ ይማር! ወዳጅ ዘመድ መፅናናቱን ይስጣችሁ!
Filed in: Amharic