>
5:26 am - Friday July 1, 2022

የ"ሕውሃት ፓርቲ ፤"ከፋሺዝም ባሕርይ አንፃር (አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ፤)


የ”ሕውሃት ፓርቲ ፤”ከፋሺዝም ባሕርይ አንፃር።
                   የአዲሱን ሥርዓተ-ለውጥ ለማምጣት፣የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግሉን ከተያያዘ አሁን አንድ ዓመት ሞላው፤ብቻ ከጫንቃው ላይ የገለማውን የዘረኛ መንግሥት ነኝ ባዩን የፋሺሽት ቡድን እንዴት እንደሚላቀቅ ነበረ ትግሉ፣ተሠነጣጥቆ ተገመሠ እንጂ።ዕድሜ ለዶ/ር ዐቢይ አህመድ ቢልም ባይልም  የፋሺሽቱ-ሕውሃት ፓርቲ ባለጭምብል መንግሥት ባይሽቀነጠር ኖሮ፤የጉጅሌዎች ሬሳቸው ባደባባይ እየተጎተተ በመጨረሻ ሲዖል ነበር የሚወረወረው፤እንደ ጋዳፊ አምባ-ገነናዊ ሥርዓት።በነገራችን ላይ ከዚያን ወዲያ አዲስ አበባ ዲሞክራሲዋ “ነፍ” ነው፤መቀሌ ግን”ባዶ”ፍፁም የለም፤ይህንን ሐቅ የግዛቱ ነዋሪዎችና የፖለቲካ ባለሙያተኞቹ የዜግነት መብትን ባዶነት አረጋግጠዋል። የግለ-ሰብ መብት፣የእኩልነት፣የለውጥም ተስፋ እና የትግል ጉዞው ልዩነታቸው እንዲሁ ነው።
           ከአዲስ አበባ ጀምሮ በመዝነብ እየተዛመተ ያለው ነፃነት በሌሎቹ ግዛቶችም እያካፋ ይገኛል፤ለውጡ ደግሞ በሕዝብ አመፅ ባጠቃላይ ባገሪቱ በመስዋዕትነት እየሰከነ ያብባል፤ከመቀሌ በስተቀር።በዚህ የለውጥ ጉዞ ግዛቱ ተቆልፎበት እንዳያይ እና እንዳይሰማ ተሸብቦ፣ የሚያሳዝነው የግዛቱ ነዋሪ የትግራይ ሕዝብ ብቻ ነው፤”እኛ በጣም ደህና ነን፣እናንተ ምን አገባችሁ?” የሚሉት እና ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በፋብሪካ ቅጥርም ሆነ፣የሥራ ዕድል እየተባለ ከሕውሃት የሚቸረቸርላቸው ብቻ የጥቅም ተቋዳሽ በመሆን ጉርሻ እና ፍርፋሪ ሲያገኙ የነበሩ ብቻ እየወጡ ድጋፍቸውን እንዲናገሩ ብቻም ሳይሆን በፀያፍ ስድብ እንዲባልጉ ጭምር አይከፈላቸውም አይባልም።
          በነዚያ ሃያ ሰባት የግፍ ዓመታት በየወንበሩ ላይ ከነበሩት ባለሥልጣናት መካከል እያጭበረበሩ ሲገድሉንና ሲዘርፉን የነበሩትን፤ ከሸበጥ ጫማ ተነስተው ያለምንም ሙያ እና ህጋው የገቢ ምንጭ በኢትዮጵያ ላይ ምን እንደፈፀሙ ስናስታውስ፤ ባጠቃላይ የነበረው ሁኔታ ሁሉ “እዚያም ሄደሽ በላሽ፣እዚህም መጥትሽ በላሽ፤ሰው ታዘበሽ እንጂ ሆድሽንም አልሞላሽ፤ “መባላቸውን አንዘነጋውም።በአሁኑ ጊዜ ግን ያ የሥልጣን በደም መጨማለቅ ሁሉ የህልም እሩጫቸውን እንደጥላ እያለፈ የምጥ፣የፍርድ እና የጭንቅ ጊዜያቸው ከድጃፋቸው ይጠብቃቸዋል።በዚህም መሠረት ሁለት ምርጫዎች አሏቸው፤ምርጫው የየግላቸው ነው።
     በይቅርታና በምህረት ተፀፅቶ አዲስ ሕይወት መጀመር ወይም አሁን እየተደረገና ማንም አያውቅብኝም ብለው በሦስተኛ እጅ ሕዝብ እያጋደሉ መቀጠል።ምርጫው የሕዝብ አይደለም፤ሕዝብ ምኑ ሲጎድልበት?ቀድሞውኑ ተዘርፏል፣ተገድሏል፣ ተፈናቅሏል፣ ታርዟል፣ተርቧል፣ተጠምቷል ስንቱን ሆኗል፤ከዚህስ በላይ ምን ይሆናል?የሚያደርገውን ያውቃል፤ወይ መኖር አሊያም መሞት። እነዚህ ሕዝብን ሲዘርፉት ሲገድሉትና ሀብት ሲያካብቱ የነበሩት ግን እነማንና የት እንደሚኖሩ፣ምን እንዳላቸው ስለሚያውቅ መጀመሪያ ለራሳቸው ሲሉ ምርጫቸውን ዛሬ ማወቅ ይኖርባቸዋል።
         እናም የዶክተር ዐቢይ አህመድ መምጣት”ፅድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም፤ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም፤” ያስብላል። እሳቸው በአይናችን የምናየውን እንዲፈፀም ሲያደርጉ ላንክደው እያየን ነው፤በሌላ በኩል “ሲያታልል ነው፤ ሊያሞኛችሁ ነው” የሚሉን የሚያዩትን ክደው ነው።ከጅምሩ ለውጡ በፍፁም ውሸት ነው የሚሉም ምሁራን ተብዬዎች ከመጀመሪያው የሚጮሁ ሞልተዋል፤በየመረቡ ውስጥ ናቸው እንጂ።ይልቅስ መረጃቸውን በነገረ-ነብስ(ሎጂክ)እንኳን ለሕዝብ ለምሁራኑ በቀላል የማይረዳ የዕውነት ቀመር ያላቸውም ሞልተዋል።
       አደገኛውና ቁማርተኛው ግን፣ዋሻው ውስጥ መሽጎ፣ቀን ተሸሽጎ፣ሲያይ አጮልጎ፣ሲበላ ጠራርጎ፣ሲያጋድል ጭምብል አድርጎ፣ሲያጋጭ ተሰግስጎ በመሆኑ ሰዎች ጠንቅቀው አያውቁትም፤የሕውሃትን ፋሺዝምነት።እንግዲህ በደምብ እንወቀው የኢትዮጵያ ችግር የፋሺዝም ሥርዓት ተፈረካክሶ አለማብቃቱ ነው፤በቅድሚያ ግን እባብ አንገቱ ቢቆርጥም እንኳ ድንገት ከነከሰ ሞቶ ለመመረዝ እንደሚችል ሁሉ፤የሕውሃት-ፋሺዝም ሥርዓት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደነበርና አናቱ ቢቆረጥም በደመ-ነብስ እንዳለ በመረጃዎች መተማመን አለብን።ስለዚህም ሕውሃት-ፋሺዝምን በደምብ ከባሕርዮቹ ካወቅን በኋላ፣በትክክል የባንዳው ፋሺዝም በኢትዮጵያ ውስጥ እንደነበረ ከጨካኝ የጣሊያን ፋሺሽት ጋር እያመሳከርን ካረጋገጥን በኋላ “የጣሊያን ፋሺዝምን” በዓለም እንደተደረገው እና ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ እንደተሽቀነጠረው፣ፋሺሽቱ ሕውሃትንም አውግዘንና ረግመን ወደመቃብሩ ልንወረውረው ይገባናል።
     እናም በቀላል አቀራረብ በምሳሌ በማስቀመጥ ልጀምርና፦ሕመም ሲሰማን መጀምሪያ የምናደርገውን ዕርምጃ እናገናዝብበት። ምክንያቱም በሽታ ሲያመን እና ስንሰቃይ ስሙን አናውቀውም፣ባለሙያው መርምሮ እስከሚያገኘው ድረስ።በሽተኛውም ሃያ ሰባት ዓመታት ቢፈጅበትም እንኳ፣እኛ አመመን ከማለት በስተቀር በሽታውን ለይተን ይሄ ነው ማለት አንችልም።በተለይ ሥልጣኔን እናመስግንና ዝሬ ዛሬ አይደለም በሽታና ሕመም፤ሌሎችንም መረጃዎች በቀላሉ ማግኘት ይቻላል።እናም ስለፍሺዝም ምንነት ከተማርነው እና ከምናውቀው በላይ በቂ ትንታኔዎች ተሰጥተዋል፤ስለዚህም ትንታኔውን ለማወቅ ከባድ አይሆንም። በዚህም ምክንያት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት መሠረታዊ መገለጫዎቹ ትንታኔዎቹን በጥንቃቄ ከተጨባጮች እንመለከታለን:-
*እንግዲህ ሕውሃት የሚባለው ፓርቲ በባሕርይው የፋሺዝም ሥርዓት እንደሆነ በመረጃዎች ከጣሊያኑ የፋሺሽት ፓርቲ አንፃር እንመልከትና በሕሊና ዳኝነት ሕውሃት ፋሺሽት ፓርቲ መሆን ወይም አለመሆኑን እናረጋግጥ። ፋሺዝም የአንድ ፓርቲ አምባገነናዊ ፀረ-ዲሞክራሲ ሥርዓት ነው፤ይህ ሥርዓት በቀላሉ አቀራረብ ፀረ-ሕዝብ ነው።
*ፋሺሽት-ህውሃት ለግድያው ማስፈፀሚያ አጋዚ የሚባል የራሱ ገዳይ እና አፋኝ ጦር-ሠራዊት አቋቁሞ ባደባባይ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ረሽኗል።በተለይ በአማራ ክልል እናቶች እንዳይወልዱ የምክነት መርፌ እንዲወጉ አድርጎ ጅምላ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሟል:-ጋምቤላ፣ኦሮሚያ፣ኮንሶ እና ወዘተ
*የሕውሃትን ፋሺዝም ፓርቲ ለትግራይ ካቋቋሙት ቀንደኛው መለስ(ለገሠ)ዜናዊ ነው፤ለጣሊያን ፋሺዝም ፓርቲ ደግሞ ያቋቋመው ቤኒቶ ሞሶሎኒ ነው።
*ሁለቱም አምባገነናዊ መሪዎች ነበሩ፤ለአምባ ገነንነት ሥርዓታቸው ማስፈፀሚያ ሲጠቀሙ የነበሩት የፍትህ አካላቱን ነበር።
*ለፋሺሽታዊ ሥርዓታቸው የየራሳቸው ፀሐፊ መሳሪያዎች ነበሯቸው፤የሕዝቡን ዐይን በቃላት እና በልብ-ወለድ ታሪኮች የሚጋርዱ፣ተስፋዬ ገ/አብ ለመለስ ዜናዊ እና ጊኦቫኒ ጌንቲሌ(Giovanni Gentile) ለቤኒቶ ሞሶሎኒ።
*ፓርቲዎቹ ሽብርተኞች ለመሆናቸው ራሳቸው እያጋደሉ(ኦሮሞው ጨክኖ ሱማሌውን ገደለው ወይም አማራው ነው ቅማንቱን የገደለው በማለት) በሕዝብ ያመካኙ ነበር።
*ሁለቱም ፋሺሽቶች ወንጀሎችን ለመፈፀም ፖሊስን እንደ መሳሪያ አድርገው ይጠቀሙ ነበር፤ዳኞቹም ሆኑ ፖሊሶቹ ለፋሺሽት-ወያኔ ወይም ለጣሊያን ፋሺሽት ፓርቲ አባል ናቸው።
*የሚያሳቅቀው እንደመቀጣጫ ግድያ የሚሉትን አፈፃፀም ሁለቱም ለማድረጋቸው ሕፃናትን፣ሴት ልጆችን በጠመንጃ ሲገደሉ፣ ስቅላት ርሸናና ቀጥታ ግድያ በሞሶሎኒ ሆነ በለገሠ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ተፈፅሟል።
*ያልተቋረጠ ስደት ማፈናቀል እና ጅምላ ግድያ በአደባባይ እና በድብቅ ተፈፅሟል፤እነዚህ ሁሉ የፋሺዝም ባሕርይዎች የነበሩ ሲሆን ይህንን የፈፀመው ሕውሃት እንደ ፋሺሽቱ የጣሊያን ፓርቲ የፋሺሽት ፓርቲ ተብሎ ወደ መቃብሩ ሊወረወር ይገባዋል።አለበለዚያ በየቦታው ያጠመዳቸውን ለማክሸፍ ብዙ መስዋዕትነት ያስከፍለናል።

ይህም ማለት ባደባባይ ፋሺሽትነቱ ተነግሮ አባላቱም የለውጥ-ተሃድሶ ትምህርት ሊሰጣቸውና ሰላማዊ ሕይወታቸውን እንዲቀላቀሉ ማድረግ ይገባል።ይህ ካልተፈፀመ ግን የፋሺሽት-ሕውሃት አባላት ለፋሺሽት ዓላማ አስፈፃሚዎች ሆነው ማገልገል ይቀጥላሉ፤በሕዝብ ውስጥም ግድያና አፈና በመፈፀም በፀረ-ሕዝብ ተግባር ላይ ባለማወቅ በተሳሳተ ዓላማ ውስጥ ይሰማራሉ። ይህ ክፉ የግድያ ማምረቻ መሳሪያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተሰባብሮ የተቀበረ የአምባ-ገነኖች ርኩስ እና እሥስት ሕዝብን  መጨቆኛ ነበር፤የፋሺዝምን ባሕርይ ለሚያስተውሉና ልብ ላላቸው የሕውሃትን ከስህተቶች

ያለመማር

ን ከዚህ ክስተት ያዩታል።

 
 
ኢትዮጵያ ለዘላለም በነፃነት እና በሠላም ለዘላለም ትኑር!!!
Filed in: Amharic