>

ግርግር ለማን እንደሚያመች የሚያውቀው ገንዘብ ዘርፎ ያስጫነው ነው (አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

ግርግር ለማን እንደሚያመች የሚያውቀው ገንዘብ ዘርፎ ያስጫነው 

ፋሺሽት-ወያኔ ሲሆን፤አህያዋም የማትከፍተው ዋሻ የለም።

 

አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

 

የባሰውን መግደል ነገ ሳያመጡ፤
ወደ ሕዝብ ለመግባት 
ከፓርቲ ልብ ውጡ።
“ቅማል እንኳን ባቅሟ፤
አሳብጧት ደሟ፤
ጥርሷን ከተከለች፤
ጥብጣብ ታስፈታለች።”
እንደተባለው ሁሉ ትንሿን ነገር መናቅ የለብንም።
 
እነዚህ ስምንቱ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ቤኢትዮጵያ ውስጥ ተፈፅመዋል፤አስፈፃሚ የነበረው ደግሞ ፋሺሽቱ-ወያኔ በሕውሃት ፓርቲው ውስጥ ተደራጅቶ ነው።
 
The 8 stages of Genocide…. (By Gregory H. Stanton)
1. categorization- “እኛ” እና “እነርሱ” ብሎ መመደብ
2. symbolization – ለጥፋት የታሠበውን ብሔር/ቡድን ልዩ ማንነት አመላካች መስጠት ‘መመሠል’!
3. dehumanization – ለዕልቂት የታጨውን ሕዝብ ስብዕና አውርዶ የአውሬነት ምስል መስጠት
4. organization – የተቀናጀ ጥፋት ለማድረስ መዘጋጀት
5. polarization – በሁለት ወገኖች/ሕዝቦች መካከል ልዩነት ፈጥሮ ልዩነቱን ወደማይታረቅ የእርስ በርስ ፍጅት መምራት
6. preparation – እንዴት እንደሚጠፉ ዝግጅት ማድረግ
7. extremination – የዕልቂቱን ንድፍ ተግባራዊ ማድረግ
8. denial – ድርጊቱን እየፈፀሙ አላደረግንም፣ አልሠማንም ማለት ናቸው።
            ፋሺሽት-ወያኔ ስውር-እጁን ከኢትዮጵያ ላይ ካላነሳ፣አባላቱም ሆኑ አጋሩ፣በአስቸኳይ ሁሉም የመደመር ስልጠና ሊገቡ ይገባል።
            ይህ የፋሺሽት ፓርቲ በዕርቀ-ጉባዔ ንስሓውን ያቀርባል ተብሎ የዕርቅ ኮምሽን ቢቋቋምም፤ያንን የሐቅ-ሠላም ሁኔታ ላለማየት ከወዲሁ ለቅልበሳ ጅምላ  ግድያ እያስፈፀመ ይገኛል።ሁሉም የኦሮሞ ነፃ አውጪ ድርጅቶችም አይደሉም፣ከአራቱ የኦሮሞ ድርጅቶች እራሱ ጠፍጥፎ የቦደነው ኦነግ የሚባል አንድ ስብስብ አለው፤ተግባራቸውም ወርሮ-በላነት ሲሆን፣ግልገል ጅቦች ናቸው።እነዚህ ግልገል ጅቦች ኦነግን አይወክሉም፤እንኳን የኢትዮጵያ ሕዝብ እራሳቸው ኦነጎች አያውቋቸውም።ለዚህም ምክንያቱ የርኩሰት ባህርያቸው በሰይጣናዊ እና በእሥስት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ነው።ትናንት እየላጨ በየእሥር ቤቱ እግራቸውን ሲቆርጥ፣ኣካላችውን ሲበልት የነበረው ፋሺሽት-ሕውሃትን በስንት ሚሊዮን ብር ነው የተጎዳኟቸውና ምክራቸውን የተቀበሏቸው?ለነገሩ ጥንትም የተባለ ነው፤”ገንዘብ የተጫነች አህያ የማትከፍተው ዋሻ የለም”እንዳለው ሳይንቲስቱ ጨርሶታል፣ምንም ይሁን ምን እየተወሰደ ያለው እርምጃ ግን፣መንግሥት ነን የሚሉትን ዝም ሲያሰኝ ኣብዛኛውን ኢትዮጵያውያንን ግራ የሚያጋባ ሆኗል።
          በሌላ በኩል ግን የምንሊክ ልጆች የኢትዮጵያን ሕመም አግኝተናል፤ሕመሟ የፋሺሽት-ወያኔ ስውር-እጅ መሆኑ ተረጋግጧል።እንዴት ብትሉኝ በያንዳንዱ ክልል ያለው መፈናቀል እንደተጠመደ ቦንብ የሚፈንዳ ነው፤አዲስ አበባ ሳይቀር።ማነም ሕመምተኛ በሽታው ሳይታወቅለት መድኅኒት ሊታዘዝለት አይገባም።አለበልዚያ ልምዱ ወይም ዕውቀቱ አለኝ ብለን በግምት የምንሰጠው ቅድመ-ህክምና በአስተማማኝነት ህመምተኛውን ላያድነው ወይም ሊያድነው ይችላል። እናም ቁምነገሩ በቂ ምርመራ በባለሙያ ሳይደረግለት መድኅኒት ሊታዘዝለት አይገባም ነው፤በሚገባ ከተመረመረ ግን ያለምንም ችግር የህመምተኛው በሽታ ይታውቅለታል፤መድኅኒትም ይታዘዝለታል ከበሽታውም ይፈወስል።
         ተምሳሌቱ ይኼው ነው፤የየማሕበረ-ሰቡን ዕድገት እየተከተለ የሚተነትነው የፖለቲካ ዕውቀት ይሄንኑ ነው የሚያመላክተው።ኢትዮጵያ አሁን ያለባት ችግር ምንድን ነው?ተብሎ ሲጠየቅ ሺህ ዓይነት ችግሮች መልሶች ሆነው ይሰጣሉ፤ትክክለኛ መልስ አይደለም፤ጥፋታችን ከዚህ ይጀምራል።ያሉን ችግሮች ሁለት ዓይነቶች ብቻ ናቸው፤የአጣዳፊ እና የረጅም ጊዜ ችግሮች ናቸው፤አጣዳፊው አሁን የሚደረጉት ለውጦች በሙሉ እንዲቆሙ ማድረግ ሲሆን እና የረዥሙ ጊዜ ደግሞ ለውጡን ለማስቀጠል በውስጥ ያሉትን ችግር ፈጣሪዎች ሁሉ ለጊዜው ማስወገድ ናቸው።
          ማፈናቀል ለውጥ አይደለም፤ማፍረስ ነው።እኛ ለረጅም ዕቅድ ደፋ ቀና ስንል እነማን ናቸው ጣልቃ የሚገቡት፣ለይቶ ማወቅ በሚገባ ይገባል።በአሁኑ ጊዜ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እንመልከት፤ ሁለት ተቃራኒ አካላት መንግሥት ለማቋቋም የቃል-ኪዳን መመሪያቸውን አፅድቀዋል፤እጃቸው የማይታየው ፋሺሽት-ሕውሃት፣(ኢሃድግ የሚባሉት አገልጋይ ጀሌዎች ናቸው) ባለጭምብሎቹ ግን ሕዝብ ውስጥ ተሰግሥገው ፀረ-ሕዝብ ድርጊቶችን እየፈፀሙ ይገኛሉ፤እነዚህን ባለሥልጣኖችንም ሆነ ግለሰቦችን ይዞ በቁጥጥር ሥር ማድረግ ካልቻለ እንዴት አድርጎ ሁለቱን ዓላማዎች ማሳካት ይችላል?ስለዚህ የዶ/ር ዐቢይ መንግሥት ሆደ ሰፊ ነው ተባለ እንጂ፣ቦርጫም ነው አልተባለም፤እሱ በሽታ እንደተሸከመ ያለ ከርሳም ነው።
              ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ቅንነትም ሆነ ትዕግስት ፍቅርን ለመስጠት የሚያስከፍሉት መስዋዕትነት መጠን አላቸው፤ይህን ከሙሴ ታሪክ ይገነዘቡታል ብዬ እተማመናለሁ።
              እናም ፋሺሽት-ወያኔ ስውር-እጁን ከኢትዮጵያ ላይ ካላነሳ በስተቀር፣አሊያም አባላቱም ሆኑ አጋሮቹ(የኢሃድግ አባላት)፣በአስቸኳይ ሁሉም የመደመር ስልጠና ለመውሰድ መጠለያ ጣቢያ ካልገቡ ሕውሃት ትግሉን ቀልብሶ ሕዝብን ሊያጋድል ቋምጧል፤ለምን ቢባል ግርግር ለሌባ ይመቻልና ነው።
Filed in: Amharic