>
5:13 pm - Sunday April 20, 7664

በእስክንድር አንጎል ውስጥ ያለው የሀሳብ የበላይነት አቢይ ካለው መቶ ሺህ ጦር ይበልጣል!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

በእስክንድር አንጎል ውስጥ ያለው የሀሳብ የበላይነት አቢይ ካለው መቶ ሺህ ጦር ይበልጣል!!!
ቬሮኒካ መላኩ
1-ጃዋር መሀመድ “ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁለት መንግስት ነው ዋናው መንግስት የቄሮ መንግስት ነው ” በማለት አቢይ የሚመራውን መንግስት እርባና ቢስ እንደሆነ ሲነግረው ምንም ትንፍሽ ያላለው አቢይ አህመድ ።
2- ጃዋር መሀመድ ” የመደመር ካልኩሌተሩን የሰራሁት እኔ ነኝ።” እያለ ጆሮው ስር ሲያምባርቅበት አፉን የቆለፈው አቢይ አህመድ።
3-“ቡራዩ ላይ በኦነግና ቄሮ በተባለ ቡድን የሰው ልጅ በሜንጫና በገጀራ ሲከተከት ፀጥ ያለው ጠቅላይ ሚኒስትር ።
4- ወለጋ ላይ ኦነግ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 18 ኩንታልና በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ሲዘርፍ አፉ የተለጎመው ጠቅላይ ሚኒስትር።
5- ለገጣፎ ለይ የድሆች ቤት በጠራራ ፀሀይ በቡልዶዘር ሲፈራርስና ሲደረመስ አላየሁም አልሰማሁም ያለው ይሄው ጠቅላይ ሚኒስትር ።
6-በሚሊዮን የሚቆጠር የጌድዮ ህዝብ በኦነግና በጉጂ ኦሮሞ ሲፈናቀልና በረሃብ ሲሞት ፀጥ ያለውና አንድ ዳቦ ማቅረብ ያልቻለው ጠቅላይ ሚኒስትር
7-ኮዬ ፈጨ ኮንዶሚኒየም ገጀራና ፍልጥ በያዙ ወረበሎች ሲወረር ፀጥ ረጭ ያለው ሰውዬ ……
ዛሬ እስክንድር ነጋና አዲስ አበቤ እጅግ ሰላማዊ በሆነና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ” አዲስ አበባ የብሄር ብሄረሰብ ከተማ እንጅ የአንድ ብሄር አይደለችም” ስላሉ ብቻ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፉ አረፋ እስኪደፍቅ ድረስ ሲያቅራራ አመሸ ። ጭራሽ የቡራዩን ጭፍጨፋ ራሱ እንዳቀነባበረው በሚመስል መልኩ ለአዲስ አበባ ህዝብ ማስፈራሪያ Best Practiceና ሮል ሞዴል ሲያደርገው መመልከት እንደት አሳፋሪ ነዉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ሱፍ ስለለበሰ ነው እንጅ በቀኝ እጁ ሽመል በግራ እጁ ሜንጫ የያዘ ቄሮ ይመስል ነበር።
እስክንድር ነጋን አይታችሁ አቢይን ለማየት ስትፈልጉ እጅግ አንሶ ትንሽ ሆኖ ይታያችኋል ። በእስክንድር ነጋ ኪስ ውስጥ ያለው እስክርቢቶ በእስክንድር አንጎል ውስጥ ያለው የሀሳብ የበላይነት አቢይ አህመድ ካለው መቶ ሺህ ጦር ይበልጣል።
Filed in: Amharic