>
12:41 pm - Thursday December 8, 2022

የሸዋቱለማን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የ“ዋቄፈታ ቄሮዎች” በእሳት ማንደድ ጀምረዋል (ዘመድኩን በቀለ)የሸዋቱ ለማን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 
የ“ዋቄፈታ ቄሮዎች” በእሳት ማንደድ ጀምረዋል
ዘመድኩን በቀለ
★ ይህ ለሸዋ ኦሮሞ “ የምጥ ጣር ” መጀመሪያው ምልክቱ ነው። 
ወዳጄ አብያተ ክርስቲያናትን የማቃጠሉ ዜና ከሩቁ የሱማሌ ክልል እዚህ አፍንጫህ ስር ሰሜን ሸዋ ኤጄሬ ደርሶልሃል። አዲስ አበባ አፍንጫዋ ስር ማለት ነው።  ሰምታችኋል።
ዋቄፈታቄሮዎቹ ጽላቱን ሰርቀው ከወንዝ ውስጥ ቢደብቁትም ሊቀመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተአምራቱን ገልጾ ከተደበቀበት በተአምራት ወጥቷል። 
★ ቤተ ክህነቱና ቅዱስ ሲኖዶሱ ግን በደሞዝ ጭማሪ፣ በመኪና ግዢና ሽያጭ፣ በፎቅ ግንባታ ፈርቅና በአለቆች ዝውውር ይነታረክልኛል። 
* ለኦሮሞ ኦርቶዶክሳውያን ይህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ነው። የእነ ፀጋዬ አራርሳና የእነ ሜንጫ ሠራዊት ውትወታ ፍሬ እያፈራም ይመስላል።
•••
ባለፈው ሰንበት “ባልታወቁ ሰዎች” የሚል የተለመደ የዳቦ ስም በተሰጠው የእሳት አደጋ በኤጄሬ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን የቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ዘርፈው ሲያበቁ እሳት ለቀውበት መሄዳቸው ተነግሯል። በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የነበሩትን ቅዱሳት መጻሕፍትን እና ጽላተ ሕጉንም ጨምረው የሰረቁ ቢሆንም በተደረገ ከፍተኛ አውጫጪኝና ክትትል ጽላቱን ጨምሮ ከእሳት የተረፉት ቅዱሳት መጻሕፍት የተደራጁት ቄሮዎች ከደበቁበት ሥፍራ አውጥተው በኤግዚቢትነት የተያዙ ሲሆን ወንጀለኞቹም በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።
•••
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ የካቲት 16 ለ 17 አጥቢያ እኩለ ሌሊት ላይ በዚሁ በኦሮሚያ ክልል ሕደቡ አቦቴ ወረዳ “ ዋቄፈታ” በመባል የሚጠሩት የሃጂ ጃዋር ቄሮዎች በተመሳሳይ መልኩ በዚህችው በመከረኛዋና በፈረደባት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ በድጋሚ ሌላ ጥቃት ይፈጽማሉ። “ዋቄፈታዎቹ” ቄሮዎች ጥቃቱን የፈጸሙት በሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ሲሆን ቤተክርስቲያኑን ሙሉ ለሙሉ በእሳት ማጋየታቸውም ታውቋል።
•••
በታሪካቸው እንዲህ ዓይነት በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረግ አስነዋሪ ድርጊት ሲፈጸም ዐይተው የማያውቁት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችም የትእግስታቸው መጠን ከልኩ በማለፉ ቁጣቸውን መግለጽ መጀመራቸው ነው የተነገረው።
•••
አሁን ለሰላማዊው የሸዋ ኦሮሞ አክራሪዎቹ ቄሮዎች ቀደም ሲል በእነ ጃዋር በኩል የታቀደውን እቅድ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል ማለት ነው። የሸዋ ኦሮሞ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት በመሆኑ ምክንያትና በኢትዮጵያ አንድነት ላይም ለድርድር የማይቀርብ የጸና አቋም ያለው በመሆኑ በሌሎቹ ኦሮሞ ነን በሚሉ አካላት ጥርስ ውስጥ የገባ ነገድ ነው።
•••
ውጥረት በሰላማዊው የሸዋ ኦሮሞ ላይ ነግሧል። አንድ የፕሮቴስታንትና አንድ የዋቄፈታ የእምነት አዳራሾች መቃጠላቸውም ተነግሯል። የአካባቢው ሚኒሻና ፖሊስ ሁከቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ባለመቻሉና ከአቅሙ በላይ እየሆነ በመቸገሩ ከፌደራልና ከክክል ሠራዊቱ ወደ ሥፍራው መንቀሳቀሱም የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።
•••
አስታውሱ ባለፈው ሐምሌ ወር በእኔ በኩል ከገዳም አባቶች ከመጣው መልእክት መካከል አንዱ “ በኦሮሚያ ክልል ” የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ከፊት ለፊታችሁ ከባድ የመከራ ዘመን ስለሚገጥማችሁ ጸልዩ መባላችሁን እንዳልረሳችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
•••
በመጨረሻም ፦ የአቢቹ መንግሥት ሴራው ግልጽ እየሆነ እየመጣ መሆኑ ይሰማኛል። ደቡብን ማፈናቀል፣ ማስራብ፣ በበሽታና በወረርሽኝ መጨረስ። በሰሜን ዐማራውን ከትግሬው ማባላት፣ ማናከስ፣ ማባላት፣ በመጨረሻም በጦርነት እንዲተላለቁ የመጨዋቻ ሜዳ ማመቻቸት።
•••
ተመልኩቱ። ዐማራውን መንግሥት በሴራ ያፈናቅለዋል። የተፈናቀለውን ዐማራ ደግሞ ራሱ ዐማራው ከመቀነቱ ፈትቶ እንዲረዳው፣ እንዲደጉመው ይደረጋል። ለኢትዮጵያ የሚደረግ ትሩፋት ዐማራውን እንዳይመለከተው ተደርጓል። ሌላው ቢቀር ቀይ መስቀልም ሆነ ቀይ ጨረቃ እንኳ ዐማራውን እንዲረዳ አይበረታታም። ዕዳው ሁሉ ለዐማራ ነው።
•••
በሌላ በኩል ከጅጅጋ ጀምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በእሳት እንድትነድ ያደርጋል። ለዚህ አደጋ ሓላፊነት እሱ አይወስድም። ችግሩ ደርሷል ብሎም  አይረዳትም። አማኙ ከኪሱ አውጥቶ ራሱ ይሠራዋል። ጥሪቱን አሟጥጦ መልሶ ይገነባል። በዚህ በዚህ ዘዴ ህዝቡን በእጅ አዙር አደህይቶ ራቁቱን ለማስቀረት ዕቅድ ነድፎ መንግሥታችን ተግቶ ይሠራል። ይሄ ሴራ ሰይጣን እንኳ የተገረመበትና ከዚህ በፊት በሂትለርም ሆነ በፒኖሼ፣ በናቡከደነፆርም ሆነ በፈርኦን ላይ ያላየው ጭካኔ ስለሆነ በመገረም እጁን በአፉ ጭኖ የሚደመመበት ረቂቅ ሰይጣናዊ ተግባር ነው።
•••
ተመልከቱልኝማ የዐማራን ህዝብ በወር 1 ቢልዮን ብር ለፌደራሉ መንግሥት ደም እያስተፉ ግብር እንዲገብር ያስደርጉታል። ከዐማራ ክልል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩልም በቢልየን ብር የሚቆጠር ብር በትርፍ መልክ ይግጣሉ። ዐማራው ሲፈናቀል ግን ቤሳቤስቲን ሳንቲም ለመርዳት አይፈልጉም። ጭራሽ ብለው ብለው 4ብር ከ50 ሳንቲም እንደ የኔ ቢጤ ልወርውርልህ ይሉታል። እሱም ሲፈጥረው ጅንን ነው ወጊድ ይሁዳ ብሎ ያሸማቀቅልኛል።
•••
በአንጻሩ ደግሞ 30 ሺህ ህዝብ ከሶማሌ ክልል አፈናቅለው 500 ሺህ ህዝብ ከኦሮሚያ አምጥተው እሱን በ ሚልየን ህዝብ ቁጥር ሸቅለው ግጠው፣ ከዚያም 18 ባንክ ዘርፈውና አዘርፈው ባላየ ባልሰማ ጮጋ ይላሉ። በኦሮሚያ ክልል ዐማራ በአንድ ወር ውስጥ የሚሰበስበውን ግብር እነሱ በዓመት 1ቢልየን ብር ለመሰብሰብ አቅደው መንቀሳቀሳቸውን ካሜራፊት ተገሽረው ሲገልጹ ቅሽሽም አይላቸው። በዐማራ ግብር ከኦሮሚያ ክልል ያሰፈራቸውን ዜጎች መኖሪያ ቤት ይገነቡበታል። በዐማራ ግብር የአዲስ አበባና የሸዋ፣ የሻሸመኔና የጥቁር ውኃ ዲሞግራፊ  ለመቀየር ሌት ተቀን ይሠራበታል። ደግሞ ከእነሱም ብሰው በዐማራው ላይ ቡራከረዩ ብለው ጽንፈኞቹ ሌት ተቀን ያቅራራሉ።
•••
እንደኔ እምነት ግን ዐማራ ማለት ኢትዮጵያን ከአቅሙ በላይ የተሸከመ ጫንቃ ብርቱ የሆነ ህዝብ ነው። ኢትዮጵያ የዐማራ ዕዳው ናት። በደቡብ ኦህዴድና ኦነግ ያፈናቀሏቸውን ዜጎች እነ ጌዶን ጭምር በከፍተኛ ቁጥር የሚረዳው ዐማራው ብቻ ነው። ይሄን መማረጋገጥ የታማኝን ጎፈንደረሚ ገጽ ገልበጥ ገልበጥ አድርጎ የለጋሶቹን ስምዝርዝር ማየቱ ብቻ በቂ ነው። አከተመ።
•••
ሻሎም !  ሰላም !
መጋቢት 17/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic