>

አቶ እስክንድር ነጋ መስተዋትዎ ሆነልዎት፤ ዶ/ር ዐቢይ አህመድም መለስ እንደማለት እንዳይሉ። (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ)

አቶ እስክንድር ነጋ መስተዋትዎ ሆነልዎት፤

ዶ/ር ዐቢይ አህመድም መለስ እንደማለት እንዳይሉ።

ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ፤(

 

ክብር ጠቅላይ ሚንስቴር
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ  
ባሉበት፤
   የዛሬው መልዕክቴ “ሰውና መስተዋት”የሚል ሲሆን፣ብቅድሚያ(ለፍቅር የሐይማኖት ልዩነት ቦታ የለውም)ሁለታችሁም ክርስቲያን ወንድሞቼ ስለሆናችሁና ለአንድ በጎ ዓላማ ከአንድ ምንጭ የምትጠጡ ስለሆነ እጠቅሳለሁ።የያዕቆብ መልእክት ም፩ ፥ቁ፳፫:-
 ” ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል።”ይላል፤የትኛውን ቃል የፍቅር ቃል፤ከዓለማዊውም ልጨምርበትና ይነበብ
የዲባቶ ከበደ ሚካኤል የምሳሌ ማዋዣ ትምህርታቸውንም ያስታውሰኛል፤መልክና መስተዋት፣ታሪክ እና ምሳሌ  ፫ኛመጽሐፍ ገፅ ፴፭ ።ሲያነቧት ትንሽ ሃሳብ ያላት ትመስላለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግን በክብር መልክቱ አስፍሮታል።
 ተመለስኩ ከብላቴን ጌታ ከበደ ሚካኤል
 
“ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አናት፤
ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት፤
አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ፤
እመሬት ላይ ወድቀው ሳይንከባለሉ።”ገፅ ፸፭
 
ክብር ጠቅላይ ሚንስቴር  
             ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ዐይናቸው እያየው እነሱ የማያዩት ነገር ሞልቷል፤ይሄን ጊዜ ያላየው ዐይናቸው ሳይሆን ድንገት ልባቸው እንዳላየ የምናውቅ ስንቶቻችን ነን?ያጋጥማል እንበል እንጂ ሁላችንም ነን፤በሠይጣን አመካኘንም አላማካኘንም።ትናንት እስክንድር ነጋ የተባለውን መስተዋት ሰባት አመታት ሙሉ ቀጥቅጦ፣የማርያምን ሕጻን በግርግም ውስጥ ሳይሆን በግም እስር ቤት ውስጥ እንዲወለድ ሠይጣናዊ ሰገሎቹን አዝዞ፣ሚስቱን በግፍ እዚያው እንደሙሴ የግብፆች ግፍ ዘመን ጭቃ እለመኖሩ እንጂ አዋርዶ እስክንድርን ለመስበር ሰባት ዓመታት ሙሉ ያለርህራሄ ቀጥቅጦ ወቸገሉ ለገሰ ዜናዊ ላይመለስ የት እንደሄደ እስከዛሬ ድረስ እርግጠኞች አይደለንም፤እሱም በግፉ የትም ቀርቷል፣የነበረውን የቀብር ታያትር የምናውቀው ሆኖ።
           በአገራችን ኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እግዚአብሔር ብዙ የማይታዩ ነገሮችን እያሳየን ነው፤ፈተናው ደግሞ ሥጋዊም መንፈሳዊም ነው።እስኪ ልብ እንበል ሁለት የመንፈስ አባቶች እንዲያ ነበር፤ዛሬ ዛሬ ደግሞ ሁለት የሕዝብ ነን የሚሉ እና ሕይወታቸውን ለመገበር በፆም በፀሎት የሚያምኑ፤ቢያንስ ክርስቶስን ይዘው ለሕዝባቸው ሌት ተቀን ደፋ ቀና የሚሉ ሐቀኛ ሰዎች ምን እያደረጉ እንደሆኑ ስንታችን ተገንዝበናል?ልብ እንበል።
 
                  ዶክተር አቢይ አህመድ ወደሥልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የወዳጅ ጠላቶች ከጎናቸው ተለይተዋቸው አያውቁም፤ለዚህም ነው ከደምና ከአጥንት በላይ የሰው ሕይወት በደም የተገበረበት።ስለወዳጅ ጠላቱ ወርቅነህ ቀምዚሎ ደጋግመን ብንነግርዎትም አልተበሉንም ነበር፣እንዲያውም አምባሳደሮችን በይፋ ለአስቸኳይ ስብሰባ ብሎ ጠርቶ በእርስዎ ላይ ከጉጅሌዎች ጋር ሲዶልትና ጠቅላይ ሚኒስቴርነት ቃል ተገብቶለት ተፍተፍ ሲል የቅርብ አማካሪዎችዎ ደርሰውበት ያ እኛ ስንለው የነበረው ተጋልጦበት ርምጃ ወስደውበታል።
           እንደገና የሚያሳዝነው ደግሞ ጁሃር ጠረባ ቡድን አደራጅቶ የመንግሥትነት እንቅስቃሴ ሲያደርግ፤ኦቦ ታከለ ኦማ ለአዲስ አበባ ሕዝብ የተሰሩትን ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለራሱና ለአርባ ጋዜጠኛዎችና ኦሮሚያ ባለሥልጣኖች ሲያድል ዝም ብለው አንድ ሰላማዊ የአዲስ አበቤ ነዋሪ የሆነ ዜጋ እስክንድር ነጋ ግን ሰላማዊ የሆነ እና በሕጋዊ ምዝገባ የተፈቀደ ሕጋዊ ስብሰባ አድርጎ ጉባኤው ያሳለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ ሕዝባዊ ጥያቄ ገና ይዞ ሳይቀርብ በደረሰኝ ሪፖርት ብለው መግለጫ አውጥተውበታል።
     ዛቻም ያዘለ የጦርነት ማስፈራራትም ነው።ሕዝብ ከጎኑ ያለው እስክንድር ነጋም እንደተለመደው ልሣኑ”ኃይል የእግዚአብሔር እንደሆነ” የዘነጉትን አስታወስዎት።አስተዋይ ነዎትና በጥሞና አለ የተባለውን ጥፋት ለማጣራት ቀጠሮ ይዘው ያነጋግሩታል ብዬ ነበር የጠበቅኩት፣ምክንያቱም እነዚያ ገጀራ ይዘው የደነፉትንም ሆነ ኬላዎችን እዘጋለሁ አሊያም”እኔ ከንቲባ ነኝ ማነው የሚነካኝ?”የሚለውን ችላ ብለው፣መደንፋት በሚመስል የሰጡት መግለጫ እኔን ጨምሮ በሚሊዮን የምንቆጠረውን ደጋፊዎችዎን አሳዝኗል።
      ድብቅ ነገር ብሎ የለም፤ድብቅ እጆች ግን አሉ፣”ሦስተኛው እጅ” ነው።መቼም በኢሃድግ ጆንያ ውስጥ ያለ ሁልጊዜም “ኢሃድግ ኢሃድግ ኢሃድግ ኢሃድግ” እንዳለ ነው፤ትርጉሙ ደግሞ”ልብላው ልብላው ልብላው ልብላው”ማለት ነው።እናም ብላው የሚል ሰው ስለሌለ አመቺ ጊዜ ይጠብቃል፤መረጃ ቢያስፈልግ ሞልቷል።የእነ ኦቦ ታከለ ኦማ አሰራር፣የእነ እስክንድር ነጋ ስብሰባ በደህንነት መወረር፤ብዙ ሩቅ እንድንፈልግ አያደርገንም።የዶክተር ዐቢይ አህመድን ጠቅላይ ሚኒስቴርነታቸውን ተቀብለን፣ ስለሰንደቅ አላማችንም ባንዲራነት ከነቀንዶቹ ዝም ያልነው፣በመልካም ተግባራቸው ነው።
     ስንቱን ውትፍትፍ በዝምታ የተቀበልነው ከዛሬ ነገ የተሻለ ይመጣል በሚል እንጂ “አይጧ ትለፍ”ብለን አይደለም፤ምጣድ ቢሰበር ምጣድ ይመጣል።የት አባቷ ታልፋታለች እዚሁ ድብን ትላታለች እንጂ፤ አንላቀቃትም።ሃያ ሰባት ቢሊዮኗን ቅርጥፍ አድርጋ በልታ ምድረ-ሐበሻ እንዲከፍለው ያምራታል?ይቅርታ ይሁን ተባለ እንጂ የሃያ ሰባት ዓመታት ባለሥልጣናት በሙሉ ካድሬዎች ሳይቀሩ ከቀበሌ ጀምሮ የሰሩት ቤት ከሚያገኙት ደሞዝ በላይ መሆኑ ሲረጋገጥ ግዴታ ነው አንገታቸው ተጠምዝዞ ቢሊዮኗን ከቀበሩበት ቆፍረው ማምጣትአሁን ለቅጥር ሕዝብ በጥብጦች የሚከፈላቸው ያው ገንዘብ ነው፤በግምት አይደለም ራሳቸው ገበሬዎቹ በቴሌቪዥን መስኮት ሲያዙ ተናግረዋል።እዚህ እነታማኝ አለገብረ-ማርያም ከስደተኛው ይሰብስባሉ፤በየከተማዎች ውስጥ ዥርፊያውን የሚያስቆም ጠፍቷል፤ይህ የየዕለት ክስተት ነው።
   ጉጅሌ ሌት-ተቀን ተንኮል የሚሸርብብዎት ደግሞ ተሳካልኝ ብሎ እየፈነጠዘ ነውደብረ-ፂዮን ከበሮውን ሲደልቅ ይሰማል።።በአቋም ግን ከርስዎ ጋር ነን፤ሠይጣኑ ፋሺሽቱ-ወያኔ በምንም ታምር ርግብ አይሆንም፤ ስለዚህም በሕዝብ ከመ ጨ ፍ ጨ ፍ አይድንም፤እርስዎም ቢሆኑ ይሄ ኢሃድግ የሚሉት “የልብላው”ቃል ለምን ከአፍዎት አይጠፋም?ዳግመኛ እንዳይሉት  በትህትና እናሳስብዎታለን።ዕውነቱን ይጋቱ፤ሕውሃት እኔ ከናንተ ተለይቻለሁ ብሏል አይደለም፣ወስኗል።ታዲያ በምንድን ነው የምትግባቡት?በይሉኝታ?የትዕቢተኛን ባሕርይ ኣታውቁም?ሃላፊነትዎን ለመወጣት አባርሩት፣ራሱን አባርሯል።
መዝሙረ ዳዊት   ፵፥፬ እግዚአብሔርን የታመነ ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ምስጉን ነው።
            ስንቴ ነው በትዕቢት በኢትዮጵያ የሚያላግጥ?በትግራይ ሕዝብ ሥም የተወሰኑ ቡድኖችን እያማለለ፣በኢትዮጵያ ግዛት፣ግለሰብ የሕዝብ ሥልጣን ይዞ ደጋግሞ እየተነገረውም ለጥፋት የሚፎልለው?  “ትዕቢትና ውርደት አካልና ጥላ ናቸው።ሳይለያዩ ሁል ጊዜ ቀዳሚና ተከታይ ሆነው ተያይዘው ሲሄዱ ይኖራሉ።”
ብላቴን ጌታ ከበደ ሚካኤል
                   የአቶ እስክንድር ነጋ ኢልም* ነውእንደመስተዋት የማይደበቅ ጥፋቶችዎን እንዲያዩ ሊያሳይዎት እንደ እርስዎ በእግዚአብሔር የተመረጠ ሰብዓዊ አጋርዎ ነው፤ወደፊት ጀግንነቱን ከዕምነትዎ አንፃር እስኪያረጋግጡ።ዳሩ ግን ወደ ኋላ መለስ (ሸረጥ)**ብለው የከፋ ጥፋት እንደወቸገሉ መለስ እንዳይፈፅሙና እንዳይሰብሩትይህ ሲር*** ነው።።ይገባኛል ለሁለት ጌቶች መገዛት ከባድ መሆኑንም ባውቅም፣በሽግግር ወቅት ሊከሰት ይችላል።በቅርብም ይከታተሉ ሰሞኑን የሚዲያ ሰዎች ጥሪ ቀርቦላቸዋል እና በቦታው ይገኛሉ፤እርስዎም ይህን መግለጫ ተከታትለው ማሳለጫ መንገድ እንዲፈልጉ አሳስበዋለሁ።
 ማስታወሻ:-
 *ኢልም  የተማረ ቀለም የገባው
**ሸርጥ  ገሸሽ ሲል
***ሲር  ምሥጢር
 

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

Filed in: Amharic