>

"የኦሮሚያ ክልልን ልዩ ጥቅም ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰው ሊደግፈው የሚገባ ነው!!!" (ጠ /ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ) 

“የኦሮሚያ ክልልን ልዩ ጥቅም ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰው ሊደግፈው የሚገባ ነው!!!”

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ 

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች
. “አዲስ አበባ የሁላችንም ናት፡፡… አዲስ አበባ ለዘመናት ከፍቶት የመጣን ኢትዮጵያዊ ሁሉ እጇን ዘርግታ ትቀበል ነበር፤ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ የጎረቤት ሀገር ዜጎችንም እንደዛው፡፡ ሁሉንም አቅፋ የምትኖር ከተማ ናት፡፡ ስለዚህ እቺ ከተማ የእከሌ የእከሌ ሳትሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ናት፡፡” ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ!
• በህገመንግስቱ የተቀመጠው የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለው የልዩ ጥቅም መብት ግን ሊረጋገጥ ይገባል፤ የሚለውን ሀሳብ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰው ሊደግፈው የሚገባ ነው።
• ኢህአዲግ የቀድሞ ጥምረቱ አለ፤ ብዙዎች የተለያየን የሚመስላቸው የልዩነት ሀሳቦች ሲኖሩ አራቱ ፓርቲዎች በውስጣዊ ውይይት ብቻ ይገድቡት የነበረው ሂደት ቀርቶ ፓርቲዎቹ የልዩነት አቋማቸውን በአደባባይ መግለፃቸው ነው ጥምረቱ የሌለ የሚያስመስለው።
• ይህ አካሄድ ወደፊትም ይቀጥላል ሆኖም ተግባራዊ የሚሆነው በጋራ የወሰነው ሀሳብ ነው
• ይበልጥ ወደ አንድ ለመወሃድ የጀመርነው ሂደትም ይቀጥላል።
• የፌደራል መንግስት ተዳክሟል ለማለት መለኪያው መሆን ያለበት ሀገር ስትወረር መመከት ሲያቅተው ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን በብቃት መመከት አልችል ሲል ነው።
አሁን ግን በዚህ መልኩ የሚገለፅ አንዳችም ተግዳሮት አልገጠመንም በክልሎች የሚፈጠሩ ችግሮች ላይ ጣልቃ የማንገባው ክልሎች በራሳቸው መፍታት አለባቸው ብለን ስለምናምን ነው፤ ይህ ደግሞ ተገቢ ነው።
• ከኤርትራ ጋር ያደረግነው ስምምነት መሰረት ያደረገው ሰላምን ነው፤ በቀጣይ ኢኮኖሚ: ንግድ እና መሰል በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመስማማት በሂደት ላይ ነን፤ ስለዚህ ከህዝብ የተደበቀ ሌላ ስምምነት የለንም፡፡
• ዲያስፖራው አሁንም ሀገሩን ለመደገፍ የጀመረውን መንገድ ሊገፋበት ይገባል፤ ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ በሚወጡ መረጃዎች ተስፋ የመቁረጥ ነገር ይታያል ይህ ተገቢ አይደለም ሁሉም ነገር ቀድሞ በተግባባንበት መልኩ እየተተገበረ ነው፤ ስለሆን ወደ ኋላ ማለት አይገባም
Filed in: Amharic