>

"በኢትዮጵያም ይሁን በኢንዶኔዢያው አደጋ የሞቱት ሰዎች ቤተሰቦችም ይቅርታ ያድርጉልን"  (የቦይንግ ኩባንያ)

“በኢትዮጵያም ይሁን በኢንዶኔዢያው አደጋ የሞቱት ሰዎች ቤተሰቦችም ይቅርታ ያድርጉልን” 

የቦይንግ ኩባንያ

ኢ.ቢ.ሲ
የቦይንግ ኩባንያ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነው በቦይንግ 737 ማክስ8 ላይ ለደረሰው አደጋ ኃላፊነቱን በመውሰድ ይቅርታ ጠይቋል።
የኩባንያው ስራ አስፈፃሚ ደኤኒስ ሙሉንበርግ በኢትዮጵያውም ሆነ በኤንዶኔዥያው ላየን ኤር በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ላጡ መንገደኞችና የበረራ ሰራተኞች ከልብ ማዘናቸውንና ዳግም እንዲህ አይነት ክስተት በቦይንግ 737 ማክስ 8 እንዳይደርስ ኩባንያቸው ችግሩን በመለየት የበረራ ደህንንት ሶፍትዌርን እያሻሻለ መሆኑ ገልፀዋል።
ለደረሰው አደጋም ሃላፊነቱን ወስዷል!
ቦይንግ ካምፓኒ ማምሻውን በሃላፊው በዴኒስ ሙሊንበርግ በኩል በሰጠው መግለጫ በድምሩ 346 ሰዎች ለሞቱበትና በቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች ላይ ለደረሱት ሁለት አደጋዎች ሃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል።
በኢትዮጵያም ይሁን በኢንዶኔዢያው አደጋ የሞቱት ሰዎች ቤተሰቦችም ይቅርታ ያድርጉልኝ ነው ያለው ።
ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ከደቂቃዎች በፊት እንደዘገበው ቦይንግ  የኢንዶኔዥያውም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የደረሰው አደጋ ከሶፍትዌር ጋር የተያያዘ መሆኑን አምኗል ብሏል።
ስራ አስፈፃሚ ደኤኒስ ሙሉንበርግ ሀዘናችን  የከፋ ነው ልባችን ተሰብሯል ቢሆንም ችግሩን ፈተን አውሮፕላኖቹን በአስተማማኝ ሁኔታ ወደ በረራ ለመመለስ እንሰራለን ብለዋል።
የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ትላንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የአደጋ ምክንያት ቅድመ ሪፖርት ይፋ ሲደረግ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አውሮፕላን ከበረራ በፊት ደህንነቱ የተጠበቀና አነሳሱም ቢሆን ትክክለኛውን አቅጣጫ የተከተለ እንደነበር ማስታወቁ ይታወሳል።
በትራንስፖርት ሚኒስቴር ስር ያለው የአውሮፕላን አደጋ የምርመራ ቡድን ከአውሮፕላን አምራቹ ኩባንያ፣ከአሜሪካ ፣ ከፈረንሳይና አውሮፓ ህብረት የተውጣጡ የአቬሽን ባለሙያዎችም የተሳተፉበትን የቅድመ ምርመራውን ግኝቱን ይፋ ሲያደርግ የነሳቸው ነጥቦች በቦይንግ ኩባንያም ይሁንታ ማግኘቱን የዴአኒስ ሙሉንበርግ ይቅርታ ያሳየል እየተባለ ነው።
ቅድም ሪፖርቱ ሲገለፅ ከተነሱ ዋናዋና ጭብጦች  አውሮፕላኑ መብረር በሚያስችል አቋም ላይ የነበረ መሆኑ፤አውሮፕላኑ ሲነሳም መብረር በሚችልበት አቅጣጫ ላይ እንደነበርና አብራሪዎቹ አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን መመሪያ ተከትለው ለመቆጣጠር ጥረት አድርገው ከአቅማቸው በላይ ሆኖ አደጋው መከሰቱን ተነግሮ ነበር።
Filed in: Amharic