>

ሁለቱ ገትጋታ የነጋዎቹ ልጆች፤  ለኢትዮጵያዊነት መጓተት ማነውሳ ዱቤ* ???...(ዐቢይ ኢትዮጵያዊ)

ሁለቱ ገትጋታ የነጋዎቹ ልጆች፤  ለኢትዮጵያዊነት መጓተት ማነውሳ ዱቤ* ???…
ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ መንፈሳዊ
 
*ተጎድጓዳ ሥፍራ ይበቅላል ደደሆ፤
*የፈራነው ነገር መጣ ድሆ ድሆ።
*እኔም ተናገርኩኝ አላህ ያውቃል መሌ፤

*እስንት ከፋ

ፈሏት ያበሻን ቀበሌ።
*ቲገቡ እንደትኋን ቲወጡ እንዳንበጣ ነው የሚሆኑት፤
*መጋዘን ይበጃል ብረት ማስቀመጫ ጥይት ለሚሉት።
አርባ አራት ዓመታት ደም እየመጠጡ፤
እንደትኋን ገምተው አሉ እንዳበጡ።
አይኖሯትም ፍፁም እንዲያ እንዳላገጡ፤
እናት ሆድ አይገቧት የትም አያመልጡ
                                 * ከሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢቶች ለዘመናችን እንዲያመች ሆኖ የተቀየጠ፤(፲፱፻፰-፳፻፭)
 

           የኢትዮጵያን የፖለቲካ ችግር   ለመፍታት ፖለቲከኞች ለአርባ አራት ዓመታት ራሳቸው ሳይግባቡ አንዳንዶቹም በድብቅ የፋሺሽትን አደራ  በባንዳነት ተቀብለው ሲያስፈፅሙ በሕዝብ ተጋልጧል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲከኞች ምክር እምብዛም እንደማያስፈልግ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አክሮ አሳቧል።ያለፍንበትን መንገድ በሙዚቃም ሆነ በዘፈን ከአባታችን ንግግር በኋላ አመላከ

ቶናል

፤አንዱ ሌላውን ሲገድለው፣ያቺም እህቷን ስትክዳት ከሃዲ መሆኗን ከነመረጃው አሳየችን።እነዚያ ሁሉ ዓመታት ቢያንስ እርስ በራሳችን የተረዳዳንበት ሳይሆን የተራረድንባቸው አሳዛኝ ዓመታት እንደነበሩ በጸጸት እናስባቸዋለን።እነዚያ የፋሺሽት-ወያኔ ባንዳዎች ለዘላለም ላይመለሱ በትውልድ ተረግመው ወደመጡበት ዋሻ መሽገዋል፤ሌላው የጊዜ ጉዳይ ነው፤ወደዱም ጠሉም የኢትዮጵይ ሃያ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ባለዕዳዎች እነሱ ናቸው።

        አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የሕሊና ፍርድ በልቦናቸው ጽላት ውስጥ ተፅፎ:- ሕዝብን ያሉና ዕውነትን ፍለጋ ለመጀመር የስብስብን(ሴት ቲዎሪ)ሳይሆን የድምርን(ስሌት)በመፍትሄነት አምጥተናል ብለው  የመ+ደ+መ+ርን ቀመር ያስተጋባሉ። ሌላው ደግሞ ግፈኞችን(ቁስ) በማጥፋት ሳይሆን ግፍን(ሀሳብን)እንዳይኖር በማድረግ ግፈኞች ይጠፋሉና ዘላቂውና በደም የማያጨማልቀን ብቸኛው መፍትሔ ይኼው ብቻ ነው ብሎ በፅኑ ይሞግታሉ።
     እነዚህ ሁለት የችግር አፈታት ዘዴዎች ናቸው፣ዛሬ በአዲስ አበባም ይሁን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እልህ እያስጨረሱ ያሉት።እኔ የማምንበት ደግሞ ቀመራችሁን እንደፈለጋችሁ ያዙት፤ለመተግበር ግን የውጤታችሁ ዳኛ ሕዝብ መሆኑን ቀድማችሁ ተቀብላችሁ በበቂ ሁኔታ ፊት ለፊት መወያየት ይገባል ባይ ነኝ፤ተወደደም ተጠላም፣የጡንቻ ትግል ዘመን አክትሟልና መሪ በመሆን የሚገኘው ኃይል ከሕዝብ አመፅ በፍፁም አይበልጥም።  
   እናም ስ+ለ+መ+ደ+መ+ር ከሁሉም ኢትዮጵያዊያን ቀመሩን ያውቃሉ ብለን አንጠበቅም፤ለምን ቢባል ቀመሩ በቀላል መስዋዕነት ስላልመጣ ብቻ ሳይሆን፣ፍቅርን መሠረት የሚያደርግ መራራ በመሆኑ።ቀድሞ ቅንነት ለሌላቸው ግን ይበልጥ በጣም አስቸጋሪ ሊሆንባቸው እንደሚችል ማወቅ የሚገባቸው ግለሰቦች ይኖራሉ ብዬ እተማመናለሁ። ለዚህም ነው መ+ደ+መ+ር ያልገባቸው መሸነፍ አድርገው የሚተረጎሙት፤የእነርሱ መደናገር ሕዝቡን ለመከራ፣ለስደት እና ለእንግልት አልፎ ተርፎም ለነብስ ማጥፋት ዳርጓል። በዚህ ላይ ደግሞ የአብዮትን ትንተና  ከሚያውቁ፣አሁን ያለንበትን ለኢትዮጵያዊነት የመረዳዳት ሁኔታ ባለመረዳት:-ሂደቱን ሽግግር ነው ውይስ ለውጥ ብለው የሚጠይቁ፤ያልተጠበቁ የለውጥ ችግሮችን ማየት ጀምረናል።እነፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ፤የለየለት ፖለቲከኛ ነኝ ብሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደካደው የማይዘነጋው ክህደቱ አያሌው እንኳ፣ፍቅር ይቅርታ እና መወያየት የሚለውን ከተማረው የምረቃ ድግሪ ውስጥ እንደሌለ በሚገርም የዕብደት ቋንቋ በአደባባይ ተናግሯል፤ለምን ቢባል?የሃያ ሰባት ዓመታት የወቸገል ዜናዊ ጭፍጨፋ ዓይነት ግድያ ሳይኖር ነገሮች በቀና መንገድ ሲጓዙ በማረጋገጡ።በቅንነት መደመርን ከልብ ካስተዋልን ግን የሀሳብን መስተንግዶ ካወቅንና ዳኛው ሕዝብ ወይም ድምፅ መሆኑን በመደመር ቀመር ከተማመንን እንኳን ልዩነት ሊኖረው ይቅርና የምንፈራው ነገር አይኖርም ይላሉ፤”እኛ የምንፈራው ራሱን ፍርሃትን” ነው እንደማለት።
      የ+መ+ደ+መ+ር ቀመር ለእኔ በግርድፉም ቢሆን የገባኝ ሲሆን፣ይበልጡንም በበቂ ሁኔታ ባይረዳኝም ለ+መ+ደ+መ+ር በመጀመሪያችን ርምጃ አስፈላጊ የሆኑትን በጎ ተግባሮች ሁሉ ቅንነትን በሙሉ ልቤ ደግፌዋለሁ፤እደግፈዋለሁም።የመጀመሪያው ምክንያቴ እነዚያ በአሁኑ ጊዜ ፀረ-መ+ደ+መ+ር ርምጃ በድብቅም ሆነ በቀጥታ እየተወሰዱ የሚያጋድሉን ሰበቦች ስላሉና፣በቅርቡም ከተራ ካድሬ እና ከቀበሌ ኃላፊነት ላይ የነበሩት የኢሃድግ አባላት የነበሩት በሙሉ የተሃድሶ ሥልጠና ካልወሰዱ ብለን ስለምንተማመን የትግል አቅጣጫችንን እንዳይዘውሩት ዛሬ ርምጃዎች ሊወሰድባቸው ይገባል።
        ማንኛውም ፀረ-መ+ደ+መ+ር ችግሮች የሚፈጠሩት ከፋሺሽት ወያኔዎች የሚመነጩ እንደሆኑ በቂ መረጃዎች በተጨባጭ ተይዘዋል፤የአዲስ አበባ ችግር ጉዳይም ይህ የሦስተኛው ስውሩ እጅ ሴራ መሆኑን ከግምት ውስጥ ልንይዘው ይገባናል።የሚያሳዝነው ችግሮቹ እየታወቁና ችግር ፈጣሪው ፋሺሽት ወያኔ ቡድን መሆኑ በአደባባይ እየታወቀ፤ጠቅላይ ሚኒስቴራችንንም ሳይቀር እየዘለፈ፣ሲያዋርድ ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድ መቀጣጫ ማድረግ ሲገባ፤የዲሞክራሲ መብቱ ነው በማለት መሸፋፈን ሕገ-ወጥነት ነው።አለበለዚያ መሆን የሚገባው ዶክተር ዐቢይ አህመድ ይህን ርኩስ ተግባር በግል ለሕዝብ ሊመልሱለት ይገባል።
         ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱት ኢትዮጵያውያን መካከል በሥም”ዳያስፖራ”የተባልን  እና ለትግሉ አስተዋፅዖ ለማድረግ የሚንከራተቱ ሌት-ተቀን የሚደክሙ እንዳሉ ይታወቃል።ከእነዚህ ቅን፣ሰብዓዊ፣እና ጀግና የአርበኛ ልጆች መካከል በዚሁ የሃያ ሰባት ዓመታትም ሆነ ለባርነትና ለበላይነት የአርባ አራት ዓመታት ግድያዎችን፤እንዲሁም ከትግላችን ውስጥ ሆነው  ሲሰርቁት፣ሲዘርፉት እና ሲያመሳቅሉ ነበርዳሩግን ሕዝቡ መብቶች ቢመዘበሩበትም ጀግናዎቹ ክትግሉ ውጭ እና ውስጥ ሆነው በህቡዕና በቀጥታ ቀስ በቀስ እየተፋለሙ ፍትህ እንዲገኝ በማድረግ ላይ ናቸው፤ ከነዚህም ሁለቱ የነጋዎች ልጆች፣ፕሮፌሰር ብርሃኑ እና አቶ እስክንድር ነጋ ይገኙበታል።
            የትግል መድረኩን በነፃነት ያመቻቸው ደግሞ ጠ/ሚንስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሲሆን፤እነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የወቅቱን ሁኔታ በማገናዘብ የደገፉት የዶክተር ዐቢይን የ+መ+ደ+መ+ር ቀመር መሠረታዊ አድርገው ነው።በሌላው በኩል ግን እነአቶ እስክንድር ነጋም ከእነዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በመሠረታዊ ሃሳብ ቢስማሙም ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ:-እነርሱ ደግሞ የራሳቸውን ቀመር በመያዝ  ሰላም እና ፍቅርን ይዘው ትግሉን በሐቀኛ ውይይት እየሳሉ ሊያፋፍሙ “እኛ የምናጠፋው ግፍን እንጂ ግግፈኞችን አይደለም”በማለት በግልፅነት ጎራ ተለይተዋል፤ለዚህ ሁሉ የሃሳብ ልዩነት ጡንቻ ቦታም አልተሰጠውም።
 
     የሁለቱም ነጋዎች ልጆች ብርሃኑና እስክንድር በቅርቡ በፖለቲካ ልዩነት ቢጓተቱም በዓላማ ግን አንድ ናቸው።አዲሱ ጠቅላይ ምኒስቴራችን ዶክተር ዐቢይ አህመድ የእኛ የኢትዮጵያውያን መሪያችን ነዎት ብለናቸዋል።እኔም ጠ/ሚ ስለተባሉ ሳይሆን ተመድበውም ይሁን ተመርጠውልን ብቻ የሹመት ካባ ለብሰው ባደባባይ”በፓርቲ አሰራራቸው መሠረት ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደስአለኝ ይኼው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ብለውናል።“(በወቅቱ አሻንጉሊት ጠ/ሚ እያልን በተገኙበት ሁሉ ስናፌዝባቸው የነበሩት የእቃው ጠ/ሚ፤) ”   “ሕዝቡ አልዋሸም እኔም ከአቅሜ በላይ ነው”አሉንና ወረዱ።
      ወዴት ነው የሚሄዱት እንዳንል አዲሱ  ጠ/ሚ   በልሳናቸው አማለሉን፤ለተሰራው በደል እኔ በፓርቲዬ ሥም ይቅርታ እጠይቃለሁ አሉን።ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደስአለኝ(ደስ አይበላቸውና)አርፍደው ዓለምን እየዞሩ በኢትዮጵያ ሥም ሲንሸራሸሩ፣በወቸገሉ ዜናዊ ውቃቤ ሲምሉ፣በሃይማኖት ቃላት እንደ ደብተራ”ክርስቶስን ለሠይጣን ተግባር እንዳመቻቸው  እየካዱ “:- ለጉጅሌዎች ዓላማቸው ማስፈፀሚያ ሲጠቀሙባቸው፣ስንቱ ተነግሮ ያልቃል?ባጠቃላይ የኢትዮጵያን ነገር ሁላ ገደል ጨምረው ልጃቸውን ቤተመንግሥት ሲድሩ፣የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን በየከተማው በአጋዚ ሲጨፈጨፍ፣በየባላገሩ በዘረኝነት ሕዝቡን ሲያጋድል፣በሽታና ድርቁ ተጨምሮበት በርሃብ ሲቆላ፤ባንክ ቤቶች እየተዘረፉ ገንዘቡ በየኬላው ሲዘራ:- ባልተጠበቀ ጊዜ ጠ/ሚ ኃይለማርያም እጅግ ዘግይተው ከሥልጣን ወርጃለሁ አሉን።ይታወቅ፤ሁሉም የኢሃድግ አባላት ነበሩ ሁሉ፣ የሚጠሩበት ጊዜ አሁን አይደለም፤መቼ የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግሥት  አቋቋመና።በነገራችን ላይ አሁን የኢሃድግ አባላት ፋሺሽት-ወያኔ ባንዳዎች በሚያደርጉት ፀረ-ሕዝብ ድርጊት ምክንያት የሕዝብን ይቅርታ እየተፈታተኑት ይገኛሉ።
          እናም እሳቸው ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የ+መ+ደ+መ+ር ቀመራቸውን ይዘ፤በዓይነ-ህሊና ስናያቸው የትግል አካሄዳቸው በየጊዜው የምናየው የሚለዋወጠው ነገር በአንድ ወቅት ያየሁትን ጨዋታ አስታወሰኝ፤እንደ”የመንገድ ላይ አስማተኛ” ቀይዋን ያየ ይብላ አይነት ጨዋታ ሆኖብኛል።የያዝኳትንም የፓውንድ ሃሳብ በእጄ ላይ እንዳስቀመጥኩ እሳቸው ግን ጮክ ብለው”ቀይዋን ያየ ይብላ”እያሉ በፈገግታቸውና በመልከ መልካም ገጻቸው ወዲያ ወዲህ የታደመውን ሰው እየተመለከቱ እጃቸውን ያወናጭፋሉ።እኔም እጅ እጃቸው ላይ ቀይዋን(ሥልጣን)ወዴት እንደሚጥሏት በዐይኔ እየፈለግኩ እክታተላለሁ።
   የተጫዋቾቹ መብዛት፣አንዱ ከጎኔ ቆሞ”ያቺ አይደለችም”የሚለኝና፣”እሷ ካጠገቧ ያለችው”ነች እያለ ከሚያወናብደው ጀምሮ፤እዚያ በሩቅ ሆኖ ለቅጥረኛው”በል እንጂ   አጁሃ ንገረው”ከሚለው ድረስ(ድሮም ሁሉም ተጫዋች የሚያውቀው ርኩስ ጡንቸኛና አጭበርባሪ)ባሉበት፣ዶ/ሩ በሰፈሩ ሰዎች በእነ ለማ መገርሣ ተከቦ፣በአድመኞቹ በእነ ጃዋር ጓደኞቹም ጨዋታው በሹክሽክታ እየተረበሸ ሰላም ሆኖ ይቀጥላል ብሉ ማመን አይቻልም፣ምንም እንኳን የብልጠት ዕውቀት ያለው ቢሆንም።ዶክተሩ ግን አላረፈም፤”ይህች…ጥቁር፣ይህችም…ጥቁር ይህቺ ግን ቀይ…ይሄው…ይየኔ ነች የሚል…ድፍረቱ ያለው፣እዚህች ላይ ይጨምር?ይህን ሁሉ ሸክፎ ይወስዳል”ይላል፤እነ ለማ “እዚያ የቆማችሁ አትጋፉ ተጠጋጉ”እያሉ ሥነስርዓት ሊያሲዙ ይጮሃሉ፤ዶ/ር እጁን አወናጨፈ..ጠረጴዛው ላይ…ጧ…ቀይዋን ያየ ይብላ!ይላሉ እየደጋገሙ፤እሳቸው።ሰዉም እየተጋፋ ጨዋታውን ለማየት ይራወጣል፤በዚህ ጨዋታ ውስጥ ለመታደም ምድረ ኢትዮጵያዊ ከዓለም ነው የመጣው፤መግቢያው ኢትዮጵያዊነት ብቻ በቂ ነው።አንዳንዱ “ጨዋታው በግድ ኢትዮጵያዊነት መሆን የለበትም፣የየራሳችን ምንዛሪ(ብሔር)አለን”ይላሉ፤ሌላው ተጫዋች ደግሞ ከጎኑ ሆኖ”ጌታው ቢሆንም ይህ ግዛት የኢትዮጵያ ለመሆኑ ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው”ይለዋል፤ስንቱ ሰው ይሟገታል።
         በዚህ መሃል ነው እንግዴህ ጨዋታው እንደሰዉ አመለካከት መሆኑን የተገነዘብኩት፤ለኢትዮጵያ ብሎ፣ለገንዘብ ያሸመቀ፣ለዘረኝነት የተደበቀ፣ለሥልጣን የረቀቀ፣ለምናምን የተጨማለቀ፣ ስንቱ ይነገራል?እስኪ ከጎናችሁ ያሉትን በዐይነ-ሕሊናችሁ መድቧቸው፤ሲቁነጠነጡ ታይዋችኋላችሁ።
       እንዳይገርሟችሁ ስለዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጨዋታ እና ችሎታ ስትጠይቋቸው፣ አንዳንዱ በተገቢው መንገድ እንደሚጫወቱ ሲገልፅ፣ሌላው ደግሞ ገና ሳይጠየቅ እኔ ድሮም”አይሻልም”ብዬ ነበር፣ብሎ ይዘላብዳል፣አንደኛው ደግሞ ቀበል ያደርግና”አፍ አለኝ ብለህ ትናገራለህ?”ኣጭበርብረህ የተጫዋቹን ገንዘብ ስትሰርቅ ብትክድም’ኮ “ይቅርታ አድርጉለት ብሎ ያዳነህ ዐቢይ ነው፤”ይላል።የማፊያውን ፋሺሽቱን ሞሶሎኒ ተጫዋቹ(ሕዝቡ)እንዴት እንዳደረገው ታውቃለህ?አንዱ ይጠይቃል ሌላውን፣ይመልሳል ሌላው፤ከፈለግክ ከዩ ቲዪብ እየው”ከነሚስቱ ነው ተዘቅዝቆ በስቅላት የተገደለው፤”ያ ዕጣ ነበር የሚደርሳችሁ።እያለ ይናገረዋል”ገና አይቀርም እጃችሁን ካላሰረፋችሁ፤ይህ ሁሉ መፈናቀል እና የእርስ በእርስ ግድያ የናንተ ፈንጂ ነው”ለማያውቃችሁ፤እያንድንድሽን የት እንዳለሽ እናውቃለን እያለ ተጫዋቹ እየሰማ ይናገራል።
      ዶ/ር ዐቢይ አህመድም ጣልቃ ገባና የከረረውን ንግግር አስቁሞ ጨዋታችንን እንቀጥል እያለ፣ቀይዋን ያየ ይብላ…ገና ሲል፤አንዱ እዚያ’ጋ ተስፈንጥሮ የተቀመጠው፣”አንተ’ኮ ድሮም እነዚህን ርኩስ አጭበርባሪ ፋሺሽት-ሕውሃቶችን ለማዳን ብለህ እንጂ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብለህ አይደለም፣አሁን ዝም ብለህ ተጫወት”አለው።
  ይሄን ጊዜ ነው ከዚያ በኩል የቆመው እስክንድር ነጋ ጠጋ እያለ”ድሮም ስትጫወቱ ዝም ብዬ ስመለከት የነበረው ይህንን ሐቅ ልወቅ ብዬ እንጂ ቀይዋን ለማወቅ አቅቶኝ ኣይደለም፤እስኪ ያለግልፅነት ንክች”ብሎ ባለበት ቆመ።ዶ/ር ዐቢይ ተናዶ “ምን አልክ”ሲል፤ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከተቀመጠበት ወንበር ድንገት ጠረጴዛውን እየገፋ ተነስቶ”ሃይ እስክንድር ወቅቱን ተገንዝበሃል?”ብሎ አከታትሎ ጠየቀው።ሲሳይም አበበም ከዶክተር ዐቢይ ጀርባ እንደነበሩ ያልጠበቀው እስክንድር ነጋ፣ታከለ ዑማ ሥም ዝርዝር ቆሞ ሲያስመዘግብ በአግራሞት እያየ ከጎኑ የከበበውን ሕዝብ አስተውሎ”ኦፍ ኮርስ እኛ የምናጠፋው ግፍን እንጂ ግግፈኞችን አይደለም፤ለዚህም ነው በግልፀኝነት ግፍ እንዳይሰራብን የምንታገለው”ብሎ ሳይጨርስ፤ዶክተር ዐቢይ ጨዋታውን በንዴት በተነው።ለካስ ደብረጺዮን ጨዋታውን ከሩቅ ሆኖ ይከታተል ነበርና”እኔም ብዬ ነበር ዐቢይ ቁማር ጨዋታ አያውቅም”ብያለሁ፤ግን ብልጥ ነው መውጫ አያጣም።
          እንቅስቃሴው ከዚህ ጨዋታ ውጭ ሆኖ ትግሉ አይሳካም ማለት፣ለማጭበርበር ካልሆነ በስተቀር ሽግግርም ተባለ ለውጥ ሌላ ትርጉም የለውም አፈፃጸም ብቻ ነው።እኛም  ብንሆን ዶ/ር ዐቢይን ከመሠረቱ በደብዳቤ ጠይቀናል።ኢትዮጵያ አሁን የሚያስፈልጋት ሕገ-መንግሥት አይደለም ሕገ-ሕዝብ ነው ብለቸዋል፤ለምን ቢባል ከመሠረቱ ሕገ-መንግሥቱ የመንግሥት ሕግ ነው(ለዚሁም ሕጋዊ አይደለም)ሕገ-ሕዝብ ግን የእያንዳንዱ ዜጋ የሕዝብ ሕግ ነው።የሚኖሩትም ክፍለ አህጉራት እንጂ ክልል አይኖሩትም፤የወሰን ግጭት ብሎ ነገር የለም በአስተዳደር እንድሚፈታ ይደነገጋል፤ሌሎችም ተዛምጅ ጉዳዮችንም ሆነ ችግሮችን ሕገ-ሕዝቡ ይፈታል።የፕሮፌሰሮቹም ሆነ የዶክተሮቹ አሊያም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎቹ ችግሮች በሕዝቡ ነፃ ሕዝበ-ውሳኔ ድምፅ ይፈታል።እንደሙሴ በሥጋም ለመታገል እንበርታ እና በፀሎትና በፆም አጠንክረን በስግደት ችግራችንን ወደምድራችን እንቅበረው።
ጐቤ* ግብዝ፣አስመሳይና ወሬኛ  ገፅ ፪፻፲፰-አ/ገ(ደስታ ተ/ወልድ) 
ኢትዮጵያ በነፃነቷ ለዘላለም ትኑር
Filed in: Amharic