>

ተረኛው ኦህዴድ/ኦነግ የህወሀትን ተንኮል ሳይቀንስ ሳይጨምር እየተገበረው ነው!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ተረኛው ኦህዴድ/ኦነግ የህወሀትን ተንኮል ሳይቀንስ ሳይጨምር እየተገበረው ነው!!!
ቬሮኒካ መላኩ
#ህወሀት ስልጣን እንደያዘች!ወታደሩን ህወሀት በምትፈልገው ልክ አሰፋችው።ከዛ ከአማራ የምትፈልገውን የራያና ወልቃይት መሬት ጠራርጋ ወሰደች።ያኔ የራያና የወልቃይት ህዝብ በመከላከያ ሳይቀር ተጨፍጭፏል።
አሁንም ተረኛው ኦህዴድ/ኦነግ የህወሀትን ተንኮል ሳይቀንስ ሳይጨምር እየተገበረው ነው።በማን ላይ?በአማራ ላይ!
ኦህዴድ/ኦነግ!ከሞላ ጎደል ወታደሩ የኦሮሞን ጥቅም በሚያስከብር መልኩ አደራጅቷል።ኦሮሞ ከአማራ ሽዋን መጠቅለል ይፈልጋል።ከሚሴን መጠቅለል ይፈልጋል።ራያን መጠቅለል ይፈልጋል።ስለዚህ ህወሀት ስታደርግ እንደነበረው ሁሉ ኦህዴድ/ኦነግም ማድረግ ፈለገ።ወደ ኦሮምያ ማጠቃለል የሚፈልጋቸው የአማራ ቦታወች ድረስ ዘልቆ ጦርነት ከፍቷል።
የህወሀት አሽከር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ የብአዴን አመራሮች!ህወሀት ይቀየመናል:አለቃችን ህወሀትን ማስቀየም አንፈልግም በሚል የአጎብዳጅነት ባህሪያቸው የህወሀትን ተንኮል ደብቀው በመኖር ወልቃይትንና ራያን አስረክበዋል።
እነዚህ የብአዴን አመራሮች ዛሬም አሉ።ስልጣን ላይ ናቸው።የተቀየረ ባህሪ የላቸውም።ከህወሀት አጎብዳጅነት ወደ አብይ አህመድ አለቅላቂነት ብቻ ነው የተቀየሩት።
ኦነግን መውቀስ!አብይ አህመድን መንካት ነው ብለው ያስባሉ።አብይ አህመድ ንጉሳችን ነው ብለው ያምናሉ።ንጉሳቸው የፈለገውን ሴራ ቢሰራ ተሳስተው እንኳ መናገር አይፈልጉም።
ኦህዴድ በኦነግ በኩል ወረራ ፈጽሞብናል።ሽዋን ለመጠቅለል።
በቀጥታ ወረራ እያደረገ ያለው ኦነግ ነው!የብአዴን አመራሮች ግን ይሄን ደፍረው መናገር እንኳ አልቻሉም።ወራሪውን በግልጽ መናገር እንኮ ያልደፈሩ መሪወች ባህርዳር ላይ ምን ይሰሩልናል?!ኦነግ ክልላችን ድረስ መጥቶ ጦርነት እስኪከፍት የጸጥታው ክፍል ምን ሲሰራ ነበር?የክልሉ ደህንነት የማንን ጸጉር እያበጠረ ነው?
በአጠቃላይ!ኦህዴድና ኦነግ በስም እንጅ በአላማ አንድ ናቸው።የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም ማስከበር!ግዛቱን መለጠጥ አንዱ የጥቅማቸው መለኪያ ነው። ለዚሁ አላማቸው ከ25 እስከ 30 ሺህ የሚገመት የኦዴፓ ልዩ ሀይል ወደ አማራ ክልል በማስገባት ላይ ናቸው። ኦነግ ሸዋንና ወሎን በሀይል ወደ ኦሮሞ መጠቅለል ይፈልጋል።ኦዴፓም በሀሳቡ ብቻ ሳይሆን በተግባርም ከጎኑ መሆኑን እያሳየ ነው።
እየተደረገ ያለው ይሄ ነው!!
ኦ.ዴ.ፓ~ኦነግ የከፈተብንን ጦርነት በግልጽ መናገር ያልቻለ አድርባይ መሪ ይም ድርጅትምን ይሰራልናል?
Filed in: Amharic