>
9:36 am - Wednesday November 30, 2022

ኦነግ እያደረገ ያለው የውክልና ጦርነት መሆኑን ነው የምረዳው - ከኦ.ዴ.ፓ እና አ.ዴፓ!!! (አምሳሉ ገ/ኪዳን)

ኦነግ እያደረገ ያለው የውክልና ጦርነት መሆኑን ነው የምረዳው – ከኦ.ዴ.ፓ እና አ.ዴፓ!!!
አምሳሉ ገ/ኪዳን
ሰሞኑን ኧረ ሰሞኑን ብቻም ሳይሆን ለውጥ ከሚባለው ድራማ (ትውንተ ሁነት) በፊትም ሆነ በኋላ እየሆነ ያለውን ነገር ሁሉ በገዛ ዓይናችን እያየን በገዛ ጆሯችን እየሰማን ቆይተናል፡፡ አንድም ሰው ግን እየሆነ ያለውን ሁሉ በትክክል የገባውና የነቃ አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ግን እኮ ይሄ እየሆነ ያለው ሁሉ ግልጽ ነበረ እንዴት ግን አይገባቹህም???
ኦነግና ኦሕዴድ ኦሮሚያ የሚሉት ክልል አካል ለማድረግ የሚፈልጉትን በርካታ የወሎና የሸዋ አካባቢዎችን ከአማራ የማጽዳትና የመጠቅለልን ከብአዴን ጋር በትብብር የሚሠራ ዘመቻ ወይም ተልእኮ ክፍል የሆነው ከሰሞኑ የአጣዬ፣ የካራቆሬ፣ የማጀቴ የኤፍራታና ግድም፣ የምድረገኝ (ከሚሴ) አካባቢዎች በተደረገ ዘመቻ በተለይ በኤፍራታና ግድም በስኬት እየተጠናቀቀ ነው፡፡
በዚህ በኤፍራታና ግድም በሚባለው አካባቢ ይኖር የነበረ አማራ ሆን ተብሎ የደኅንነት ዋስትና እንዳይሰማውና ሥጋት እንዲያድርበት አሁንም ድረስ በቂና የታመነ የፀጥታ ኃይል በቦታው እንዲሰፍር ባለመደረጉ ባደረበት ከፍተኛ ሥጋት ምክንያት ነቅሎ እየወጣ ነው፡፡
ብአዴን እነኝህ የተጠቀሱት አካባቢዎች በአማራ ክልል ውስጥ ሆነው እያለ በተጨማሪም አብዛኛው ነዋሪዎቻቸው አማራ ሆኖ እያለ አማሮች “ክልላቹህ ነው!” በተባሉት በእነኝህ በገዛ ሀገራቸው ስፍራዎች በተለይም በምድረገኝ (በከሚሴ) በቋንቋቸው በአማርኛ መንግሥታዊ አገልግሎት የማግኘትና ተቀጥሮ የመሥራት ሌላም ሌላም መብት ተነፍጓቸው ለ27 ዓመታት በማያውቁት በኦሮምኛ ቋንቋ እንዲጠቀሙ ተገደውና በገዛ ሀገራቸው ተገልለው ኖረዋል፡፡ አሁንም ለውጥ ከተባለው ድራማ በኋላም በዚሁ መልኩ ነው እየተሠራ ያለው፡፡
በዚህም ምክንያት ነዋሪው “በገዛ ክልላችን ተገልለናል በቋንቋችን እንዳንገለገል ተደርገናል!” እያሉ ለዓመታት ለብአዴን ቢጮሁም ከአሸማቃቂ ምላሽ ውጭ የተሰጠ መፍትሔ ባለመኖሩ በእጅጉ እየተማረረ ሀገሩን ለቆ የወጣው አማራ ቁጥር የትየለሌ ነው፡፡ ልብ በሉ ይሄንን የሚያደርገው ኦሕዴድ አይደለም፡፡ ኦሕዴድማ ክልሉ የአማራ ስለሆነ አይመለከተውም፡፡ ይሄንን የሚያደርገው አማራን ለማጥፋት በአማራ ጠላቶች የተቀጠረው ፀረ አማራው የጥፋት ኃይል የቅጥረኞች ቡድን ብአዴን ነው፡፡
ለዚህም ነው ኦነግ በአካባቢው የጦር ማሠልጠኛ ከፍቶ እያሠለጠነ እንደሆነ ገና ከ11 ወራት በፊት ጀምሮ በክልሉ የፀጥታ ክፍል ኃላፊ በሜ/ጄ አሳምነው ጽጌ ሳይቀር ብአዴን መረጃው ደርሶት እያለ ሰምቶ እንዳልሰማ ከመሆንም አልፎ ይሄንን መረጃ የሚያመጡትን ሁሉ በግምገማ በማሸማቀቅና በማዋከብ አፋቸውን እንዲዘጉ ያደረገው፡፡
ከታማኝ ምንጮች እንደሚሰማው ከሆነ በዚህ አካባቢ የጦር ማሠልጠኛ ከፍቶ አሸባሪ ሲያሠለጥን የቆየውና ይሄንን የሰሞኑን የአሸባሪዎች ጥቃት የፈጸመው ኦነግ አይደለም፡፡ ብአዴንና ኦሕዴድ ናቸው ከላይ ለገለጽኩላቹህ ዓላማ ማለትም አካባቢውን ከአማራ በማጽዳት የኦሮሞ ለማድረግ በኦነግ ስም ሲያሠለጥሉ ቆይተው አሁንም የዓይን ምስክሮች እንዳረጋገጡት እነኝህን አሸባሪዎች በኦራል እያጓጓዙ አምጥተው በማራገፍ የአሸባሪነት እርምጃውን በኦነግ ስም እንዲወሰድ ያደረጉት፡፡
የኦነግ አመራሮች ከዚህ ድርጊት ጋር ተያይዞ የኦነግ ስም መጠራቱን አጥብቀው እየኮነኑ ያሉትም፣ ይሄንን ጥቃት ያደረሱት አካላት የኦነግን አርማ ይዘውና እያውለበለቡ በግልጽ የታዩ ሆነው እያለ የመከላከያና የጠ/ሚ ጽ/ቤት መግለጫዎች “ጥቃቱን የፈጸመው ኃይል ኦነግ ነው!” ያላሉትና የመከላከያው መግለጫማ ጭራሽ “ኦነግ ነው የሚሉ ፀረ ሰላም ኃይሎች ናቸው!” ሊሉ የቻሉት፡፡
ልብ የማንል በድኖች ሆነን ነው እንጅ ኦሕዴድ ከበፊት ጀምሮ አሁንም በቅጥረኛው በዐቢይ አሥተዳደር ዘመን በታችኛው መዋቅሩ እየተፈናቀለ የሚወጣው አማራ ተፈናቅሎ ይቀራል እንጅ ከተፈናቀለ በኋላ “ወደ ቦታው ተመለሰ!” ሲባል ሰምታቹህ ታውቃላቹህ ወይ??? በዚህ ዓይነት ሁኔታ ቀስ በቀስ በየጊዜው አፈናቅለው ያስቀሩት አማራ ቁጥር ምን ያህል እንደሆነስ ቁጥሩን ታውቁታላቹህ ወይ??? ቀሪው አማራም በዚህ መልክ ቀስ እያሉ አፈናቅለው ኦሮሚያ የሚሉትን ክልል ከአማራ ለማጽዳት አስበው እየሠሩ እንዳሉስ ታውቃላቹህ ወይ???
ቢያንስ እንኳ ይሄ አማራን እያፈናቀለ ያለው የታችኛው የኦሕዴድ መዋቅር ባፈናቀለ ቁጥር ለጊዜው ለማስመሰል “ተጠያቂ ይሆናሉ!” ተብሎ ከተገለጠ በኋላ አፈናቃዮቹ ተጠያቂ ሳይሆኑ ሲቀሩና ተፈናቃዮቹም ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ሳይደረግ ከመቅረቱ ማፈናቀሉ ሆን ተብሎ በተጠናና በታቀደ መልኩ እየተደረገ እንዳለ እንዴት መረዳት ያቅታቹሃል???
ልንገራቹህ አይደል ይሄ ለውጥ የተባለ ዘመን ወያኔ/ኢሕአዴግ ከዕይታና ከትኩረት ተሸሽጎ በለሆሳስ አማራን ከየክልሉ ለማጽዳት በሽፋንነት ለመጠቀም በሚገባ ተጠንቶ የታወጀ የጥፋት ስትራቴጅ (ስልት) ነው፡፡ ግፉን ወይም የሚፈጸሙ ጥቃቶችን መሸሸግ ሳይቻል ቀርቶ ፈጦ ሲታይባቸውና ጥያቄ ገፍቶ ሲመጣባቸውም “የለውጥ ዘመን ላይ ነው ያለነው፡፡ ይህ የለውጥ ባሕርይ ነው፡፡ እንዲህ ብሎ ብሎ መስከኑ አይቀርም!” እያሉ በመመለስ ከጥያቄው እንደሚያመልጡ ሰምተሀል ዓይተሀል፡፡ ምድረ ዘገምተኛ አንተ ለውጥ ለውጥ እያልክ ትጃጃላለህ እነሱ የዚህን ያህል ረቀው በመሔድና ለውጥ የሚል መከለያ በማበጀት ከነነፍስህ እየቀበሩህ ይገኛሉ፡፡
እንደምታዩት ብአዴን ለውጥ ከተባለው የድራማ ዘመን ወዲህ እንደ በፊቱ ጠላትነቱን፣ ቅጥረኛነቱንና ዘበኝነቱን በግልጽ እያሳየ ሳይሆን አማራን እየበላና እያስበላ ያለው ለውጥ በሚል የማጃጃያና የመከለያ ጭንብል እራሱን ደብቆ፣ አሳቢና ተቆርቋሪ መስሎ በመቅረብ ነው አማራን እየበላውና እያስበላው ያለው፡፡
በመሆኑም አማራ ተበልቶ ያልቃል እንጅ አጥፊው፣ አራጁ፣ ቀባሪው፣ ቀንደኛ ጠላቱ ብአዴን መሆኑን መቸም ቢሆን ሊነቃ የሚችል አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም የአማራ ሕዝብ ብአዴን በተግባር መሬት ላይ እየፈጸመበት ካለው ግፍ፣ ሸፍጥ፣ ደባ፣ አሻጥር፣ ሴራ ይልቅ አስመሳይ የሽንገላ አንደበቱን የሚያምን ሆኗልና፡፡ የብአዴንን ፀረ አማራነት፣ ጠላትነት፣ አጥፊነት፣ አራጅነት ለማወቅ “የአማራ ሕዝብ ሆይ! እኔ ብአዴን አዳኝህ፣ ታዳጊህ፣ መከታህ ሳልሆን ቀንደኛ ጠላትህ፣ አጥፊህ፣ አራጅህ ነኝ!” ብሎ በራሱ አንደበት እንዲነግረው ይፈልጋልና፡፡ ስለሆነም አማራ መቸም ቢሆን ብአዴን፣ አጥፊው፣ ጠላቱ፣ አራጁ፣ አውዳሚው መሆኑን ሊያውቅ ሊረዳና በብአዴን ላይ ሊነሣ አይችልም!!!
በዚህ አጋጣሚ እነ ሜ/ጄ አሳምነው ጽጌና መሰል ወገኖች እውነት እንደምትሉት ለአማራ ሕዝብ የቆማቹህ ከሆናቹህ እንደምታዩትና እንደምትረዱት የእናንተ ብአዴን ውስጥ ወይም የአማራ ክልል መንግሥት ተብየው ውስጥ መኖራቹህ የፀረ አማራው ቡድን የብአዴን መጠቀሚያ ከመሆን በስተቀር ለአማራ ሕዝብ የጠቀመው ነገር የለምና ወይም አማራን ከጥቃት ሊታደገው አልቻለምና ተጠቃላቹህ ብአዴንን በመልቀቅ ወይም ከብአዴን በመውጣት ፀረ አማራው የጥፋት ኃይል ብአዴን የእናንተን መጠቀሚያነት እንዲያጣና እንዲጋለጥ ታደርጉት ዘንድ አበክረን እንጠይቃለን??? እንዲህ ሲሆንና ሲጋለጥ ነውና የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላቱን ብአዴንን ለመታገል ሊነሣ የሚችለው፡፡ እናንተ እዚያ ውስጥ ካላቹህ ግን ብአዴን እናንተን በመጠቀም የአማራ ሕዝብ በከንቱ ብአዴንን ተስፋ በማድረግ በምታዩት መልኩ ተበልቶ እንዲያልቅ ያደርገዋል!!!
ይሄንን ማድረግ ካልቻላቹህ ግን “ለአማራ የቆምን ነን፣ ለወገናችን የማንከፍለው ዋጋ አይኖርም!” ምንንትስ የምትሉት ሁሉ ውሸት መሆኑንና በድራማው ውስጥ ገጸባሕርይ ተሰጥቷቹህ የምትተውኑብን ተዋንያን መሆናቹህን የምናውቀው ይሆናል!!!
አንተ አሳረኛው ወገኔ! በል እንግዲህ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ይሁንህ!!! አውቀህ “በአውሬ ልበላ!” ብለህ ተጋድመህ ተኝተህ እያለ ማን እንዲያዝንልህ ትጠብቃለህ???
አንተ ተኝተህ በብአዴን እየተጃጃልክ የአንተን ሞት ማን ሞቶ፣ ያንተን ትግል ማን ታግሎ ማን ነጻ እንዲያወጣህስ ነው የምትጠብቀው???
በል የራስህ ጉዳይ! “አውቀሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!” አይደለም እንዴ ተረቱስ የሚለው???
Filed in: Amharic