አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
አሁንም ለውጥ፣ የለውጥ ኃይል እያላቹህ ያላቹህ ፖለቲከኛ ነኝ፣ ምሁር ነኝ ምንንትስ ነኝ የምትሉ ወገኖች ሆይ! የቅዠት ሰዎች ሆናቹህ እንዲያው በከንቱ ተጃጃሉ ሲላቹህ ነው እንጅ በየት ሀገርና መቸስ ዘመን ነው ዋነኛ የችግር አካል የሆነ ኃይል እንደገና ደግሞ መልሶ ዋነኛ የመፍትሔ አካል ሆኖ ታይቶ የሚያውቀው??? አገዛዙ ቢለወጥ ነው ወይ አሁንም በአገዛዙ አካላት በየቦታው ዜጎች በማንነታቸው እንዲፈናቀሉና ዘር ለይተው እንዲጋጩ እየተደረገ ያለው???
“ይሄንን እያደረገ ያለው የታችኛው የኢሕአዴግ መዋቅር ነው!” እንዳትሉ በቀን ቅዠታቹህ ተውጣቹህ ማስተዋል መረዳት ተሳናቹህ እንጅ “የለውጥ ኃይል!” የምትሏቸው እነ ዐቢይ እነ ለማም እናንተን ካጃጃሉበት፣ ከደለሉበትና ካታለሉበት የኢሕአዴግን ርዕዮተዓለምና መመሪያዎች የሚቃረኑ አማላይ የአንድነት፣ የኢትዮጵያዊነት፣ የዜግነት መብትና የነጻነት አስከባሪ ቃላት በተቃራኒ እንደገና አስመስለው አንተን ለማታለል ሲተቹትና ሲያብጠለጥሉት ወደ ነበረው የኢሕአዴግ ርዕዮተዓለምና መመሪያዎቻቸው በመመለስ ጠባብና ጽንፍ የረገጡ ተግባራትን በግልጽና በስውር በተደጋጋሚ በመፈጸምና በማስፈጸም አገዛዙ “ተለወጠ!” የምትለውን ወይም “ከአገዛዙ የለውጥ ኃይል ወጣ!” የምትለውን ነገር ሐሰት መሆኑን በደንብ አድርገው አላረጋገጡም ወይ???
ሀቁ በዚህ ደረጃ ፍንትው ብሎ እየታየ ባለበት ሁኔታ ሰው የለየለት ዘገምተኛና የቅዠት ሰው ካልሆነ በስተቀር እንዴት አሁንም የለውጥ ኃይል እና ለውጥ እንዳለ አድርጎ ሊያወራ ይችላል???
እየው እንከፍ እንከፉን ለማጃጃያ የሚሆን የተወሰደ እርምጃ አለ እንጅ ፈጽሞ ለውጥ የሚባል ነገር እንዳልነበረና እንደሌለም እየሆነ ያለው በሸፍጥ በሴራ በደባ የታጀበ በሕዝብና በሀገር ላይ የሚፈጸም ግፍ ሁሉ ማሳያ ነው!!!
በመሆኑም አሁንም “ለውጥ፣ የለውጥ ኃይል!” ምንንትስ እያልክ እራስህን የምታደነቁር ፖለቲከኛና ምሁር ነኝ ባይ ሁሉ ከድንቁርናህ ንቃና ወደ ትግልህ ግባ!!!
አሉ ደግሞ “ዐቢይ ሥልጣን ቢለቅ ምን ይውጠናል?” እያሉ የሚጨነቁ ብስለት የሚባል ነገር ጨርሶ የሌላቸው እንደተፈጠሩ ያሉ ወገኖች፡፡ ወገኖቸ ሆይ! ከወያኔ ትዕዛዝ እየተቀበለ እያሸበረን ያለው ዋነኛ አሸባሪያችን ማን ሆነና???
ይሄንን እየሆነ ያለውን ቀውስ “ከስምንት እስከ ዐሥር ወር ድረስ ይቀጥላል፣ ገና ከዚህም የከፋ ነገር ትሰማላቹህ!” ብሎ በአደባባይ ሲናገር ምን ማለቱ ነው የሚመስላቹህ??? ከዐሥር ወር በኋላ ማቆም የሚችሉ ከሆነ ለምንድን ነው አሁኑኑ ለማቆም ያልፈለጉት??? እነማን ተፈናቅለው እስኪያልቁና እነማን ተገድለው እስኪጨረሱ ድረስ ለማቆየት ታስቦ ነው እስከ ዐሥር ወር መቀጠል የተፈለገውና ከእስከአሁኑ የከፋ ነገር እንደምንሰማ በግልጽ የተነገረን??? ከዚህ የዐቢይ አባባል እንዴት ይሄ ቀውስ በእነሱ የሚፈጸምና እነሱ ሲፈልጉ የሚቀሰቅሱት ሲፈልጉ ደግሞ የሚያቆሙት መሆኑን ማሰብ የሚችል ጭንቅላት ያለው ሰው መረዳት ይሳነዋል???
በመሆኑም እየሆነ ያለው ሁሉ ቀውስ አገዛዙ ሆን ብሎ የሚያደረገው መሆኑን መረዳት የግድ ይኖርባቹሃል ማለት ነው፡፡ ይሄም ማለት የለውጥ ኃይል እያላቹህ የምትጠሯቸው ዐቢይ አሕመድና ጓዶቹ አገዛዙ እንዲጠፉ የሚፈልጋቸውን እንዲያጠፋ ሽፋን በመስጠት የሚንቀሳቀሱ ልንዋጋቸው የሚገቡ ጠላቶቻችን እንጅ “እነሱ ከሌሉ ምን ይውጠናል?” ብላቹህ ልትጨነቁላቸው የሚገቡ ሰዎች አይደሉም!!!
ወያኔ እሱ ከሌለ ወይም እሱ የማይገዛት ኢትዮጵያ ከመጣች ሀገሪቱ ልትፈርስ የምትችልበትን ሁኔታ አመቻችቶ በማስፈራራት “ሀገር ከምትፈርስ አርፈን ብንገዛ ይሻላል!” እንድንል አድርጎ ሲገዛን እያለ “ወያኔ ከሌለ ሀገር የምትፈርስ ከሆነማ አርፈን እንገዛ!” ብለን ወያኔን መታገል እንዳላቆምን ሁሉ አደጋን የመከላከያ ብቸኛው አማራጭ አደጋውን ተጋፍጦ የተባለው አደጋ እንዳይደርስ ቆርጦ መታገል እንጅ ፈርቶ ተሰብስቦ መቀመጥ ግን ለመበላት መመቻቸት እንደሆነ አውቀን “ሀገር ትፈርሳለችና!” ብለን ፈርተን ለውጥ ከሚባለው ድራማ (ትውንተ ሁነት) በፊት ምንም ተስፋ ሳይኖረን ወያኔ/ኢሕአዴግን ከመታገል እንዳልተቆጠብን ሁሉ አሁንም “ዐቢይን ከመደገፍ ውጭ አማራጭ የለንም!” የምትሉ ሰዎች ይሄንን ማለታቹህ በወያኔ/ኢሕአዴግ ቁማር መበላታቹህ ወይም መጃጃላቹህ እንደሆነ ዐውቃቹህ ንቁና ተዋጉ!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!