>

ንጉስ ከወደደህ እንዲህ ከጠላህም እንዲያ ይደረግብሀል!! (ሀብታሙ አያሌው)

ንጉስ ከወደደህ እንዲህ ከጠላህም እንዲያ ይደረግብሀል!!
ሀብታሙ አያሌው
እኔ ከምልህ በላይ ፎቶው ይነግርሃል።  ነገሩ መፅሐፍ ቅዱስ “ንጉስ ለወደደው እንዲህ ያደርግለታል” እንዲል… 
—-
ንጉስ ከወደደህ =  ለደህንነትህ ተጨንቆ እንዲህ በጠባቂ አጅቦ  በድፍን ኢትዮጵያ ተዘዋውረህ የዘረኝነት መርዝህን እንድትረጭ እድል ታገኛለህ።
ንጉስ ከወደደህ = አጣና ይዘህ ወጥተህ መንግስት ላይ ዝተህ ህዝብ አስፈራርተህ ደህንነትህ ይጠበቅልሃል፤ ዛቻህን ፈርቶ አቋም የሚቀይረው መንግስትም ሦስት ቀን ሳያድር ጥያቄህን ደግፎ ለማስፈፀም የአቋም  መግለጫ ያወጣልሃል።
ንጉስ ከወደደህ=  17 ባንክ ዘርፈህ እንደ ቅዱስ ታቦት “በዎት ግባ በዎት” እየተዘመረ በር ይከፈትልሃል።  ለክብርህ ደግሞ ጠፍቶ እንደተገኘው ልጅ ‘የሰባው ፍሪዳ’  የደለበው ሰንጋ ይጣልልሃል።
ንጉስ ከወደደህ = አንድ ሚሊዮን ዜጎች በግፍ አፈናቅለህ፤ የእርዳታ እህል እንዳይደርስ ከልክለህ በረሃብ ስትፈጃቸው  እንደ ጽድቅ ይቆጠርልሃል።
ንጉስ ከወደደህ = ህዝብ  የተራቡት አይቶና የሞቱትን  ዜና ተሰምቶ  እንዳያወግዝህ  መንግስት  ይከላከልልሃል። እውነት እልሃለሁ  እረሃብ የፀናበት ያ’ ምስኪን ህዝብ ጮሆ ቁጣውን እንዳይገልፅብህ እንኳን ንጉስ በቁጣው ፀጥ ያሰኝልሃል ።
ንጉስ ከወደደህ …
*  ጠኔ ከመሬት ያጣበቃቸውን የእናቶችና የህፃናት ምስል  ፎቶ ሾፕ ነው ይልልሃል።
*  እርዳታ እንዳያደርሱ ተቋማት ማገድህንም በህዝብ ስም  እርዳታ እንዳይለመን  ለመከላከል ነው ሲል    ምሎ ይገዘትልሃል።
*  የሚዲያው ጩህት ፌክ ኒውስ ለማለት የሚዲያ አጀብ     ቤተመንግስት ይጠራልሃል።
እናም እንደነገርኩህ…  ንጉስ ለወደደው ይህን ያደርግለታል።
ንጉስ ካልወደደህ ግን=  ሰንደቅ አላማ ተሸክመህ ሰለሰላም እየዘመርክ፤  ኢትዮጵያዊነትን እያወደስክ ስትራመድ መንገድህ ላይ እሾክ ይነሰነሳል።
ንጉስ ካልወደደህ = ታፍሰህ ጦላይ ትጋዛለህ፤ አለፍ ሲል የጦርነት ዛቻ ትቀምሳለህ።
ንጉስ ካልወደደህ = ዛሬ እንደተደረገው ሰላማዊ ስብሰባህን እንዳታደርግ ጡጨኛ በመኪና ተጭኖ ሲመጣ ፖሊስ ቁርስ ላይ ነኝ ያንተን ስብሰባ ለማስከበር አልመጣም ሲልህ አትቆጣ አትናደድ…  ንጉስ ላልወደደው እንዲህ ያደርግበታል ተብሎም ተፅፏል።
እና ምን መሰለህ ብታምንም ባታምንም ለውጥማ አለ። ንጉስ ለወደደው እንዲህ ይደረግለታል።
Filed in: Amharic