>

<በህዝብ ሀብት የተቋቋመውን ተቋም ለህዝብ መልሱ> (ከአፋን ኦሮሞ የተተረጎመ -  ያሬድ አብዲ)

ከአፋን ኦሮሞ የተተረጎመ –  ያሬድ አብዲ
<በህዝብ ሀብት የተቋቋመውን ተቋም ለህዝብ መልሱ> በሚል ርዕስ ዶ/ር ሚልኬሳ ስለ OMN እንዲህ ከትቧል
* “OMN የቦርድ አባል የለውም፤ ማነጅመንት ቦርድ የለውም፤ በአለም ዙርያ የሚሰበሰበው ገንዘብ በአንድ ሰው ስም ነው የሚገባው። የተሰበሰበው ገንዘብ የትና ለምን እንደሚውል አያወቅም። ብሩ ለህዝቡ ይመለስ።”
* በርካታ ሰራተኞች ከOMN ማባረራቸውንና ድርጅቱም ወደ ግልሰብ ድርጅት ተለውጧል ።
ዶ/ር ሚልኬሳ ሚዴጋ የ ODP አመራር ስለ ጃዋርና OMN ሚዲያ የተናገሩት። .. 
 
OMN ኃ/የ/ግ/ማ(PLC) ሆኗል። ትላንት ድጋፍ ሰጪ ተቋም (ቻሪቲ) ነበር ።ዛሬ ለግል ባለሃብት ተሸጧል። እነኚህን ባለሀብቶችም በሂደት ታውቁታላችሁ።
እውነት ነው OMN በችግር ጊዜ ነው የተወለደ። ይህን ነገር በማመንጨት መሃዳመድ አደሞ፣ ሰለሞን ኡጉሼ ምስጋና አላቸው፤ ጀዋር መሀመድም ወጣቶች ገንዘብ እንዲያሰባስቡ በበኩሉ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርጓል።እኛ ሁላችንም OMNን መሳርያ አድርገን ለኦሮሞ ነፃነት እንቅስቃሴ ህዝቡን ስናነቃበት ነበር። መሀመደ አደሞ፣ ሰለሞን ኡሼ፣ ገረሱ ቱፋ፣አህመድ ጊሼ፣ ደነቃ ነጋሳ፣ አብዲ ፊጤ፣ ሌሊሳ ካሳሁን፣ ዳንኤል በሪሶ ታዋቂው ምሁር ፕ/ር መሀመድ ሀሰን፣ ፕ/ር ሀምዛ የቦርድ አመራር የነበሩት፣ አንድ በአንድ ተባረዋል። አሁን ይህ ተቋም የግል ሆኗል። ተቋሙ ደግሞ የተገነባው በህዝብብሀብት መሆኑ ይታወቃል።
ይህ ለህዝብ ግልፅ መሆን አለበት እከሌ ሌባ ነው ከማለት በፊት መጀመሪያ ንፁህ ሆኖ መገኘት ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የOMN ዋናው ዳይሬክተር ወርሃዊ ደሞዝ 150,000 ብር ነበር።አሁን ግን ስንት እንደሆነ ግልፅ አይደለም። (አሁን p.l.c ስለሆነ ለመንግስት ብቻ ነው ግልፅ የሚሆነው። ለህዝብ ግልፅ ለማድረግ አይገደድም።)
<<በቅርብ ጊዜ እንኳን ከኦሮሚያ በሙሉ ለOMN የተደረገው ድጋፍ። በመቶ ሚሊዮኖች እንደሚቆጠር ከነ አየለ ደጋጋ፣-ደረጄ ቤጊ ሰምተናል።ነገር ግን OMN ለህዝብ ይፋ አላደረገም። ግልፅ መሆን አለበት። ከተለያዩ የአለም ሀገራት ከሳውዲ አረቢያ፣ ከአውስትራሊያና ከአውሮፓ የሚሰበሰበው ብር በአንድ ሰው አካውንት ነው የሚገባው። ይህ ደግሞ አሳሳቢ ነው። አሁን ተቋሙ ቦርድ የለውም፤ ማኔጅመንት የለውም፤ የፋይናንስ አስተዳደር እና ኦዲት የህግ ማዕቀፍ የለውም ፤ ወጪ እና ገቢው የመይታወቅ ከሆነ ችግር ነው። ስለዚህ OMN ንብረትነቱ ተመልሶ ለህዝብ መሆን አለበት።
ምንጭ፡ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ
Filed in: Amharic