>
10:29 am - Wednesday December 7, 2022

እምዬ ሚኒልክና ኦነጋውያን!!! (ዘመድኩን በቀለ)

እምዬ ሚኒልክና ኦነጋውያን!!!
ዘመድኩን በቀለ
★ የኦነግ ሰራዊት የዱር እንሳቱን እየጨረሷቸው ነው፤ ወይ ያሉበት ድረስ ሰንጋ ላኩላቸው!!!
 
★ የምንሊክ ቤተመንግስት እድሳት በገለልተኛ አካል ይጎበኝ ። በእድሳት ስም ታሪክ የማጥፋት አሻጥር ይቁም !!!
 
 ጥፋቱና ውድመቱን የዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጭምር የሚያውቀው ቢሆንም አንዳቸውም ጉዳዩን አንስተው ሲቃወሙ፣ ጋዜጣዊ መግለጫም ሲሰጡ አይሰሙም፣ አይታዩምም።
 
ሀ ፦ የሚኒልክ ቤተ መንግሥት 
•••
እድሳቱ ከቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን እውቅና ውጪ መደረጉ አነጋጋሪ ሲሆን የዳይሬክተሩ ከስልጣን መባረር ለዲፕሎማቶች መረጃ ሸጧል መባሉ እና ጥያቄ ስለጠየቀ ጥርስ እንደተነከሰበት በቂ ማስረጃዎች እየሰማን እያየን ነው። እድሳቱ በታሪክ አዋቂዎች ይገምገም።
በምንሊክ ቤተመንግስት እድሳት ላይ የታሪክ አሻራዎችን ለማደብዘዝና ኢትዮጵያዊ ጥበቦችን ለማበላሸት የሚደረገው የእድሳት አሻጥር ሊቆም ይገባል ። እድሳቱን ከታሪክ አዋቂዎችና ከቤተመንግስቱ ሰወች ደብቆ ማካሔድ ወንጀል ነው። እድሳቱ በገለልተኛ ዜጎች ሊገመገምና ሊታይ ይገባል ። ታሪክን ለመበረዝ የሚኬድበት መንገድ ከሽብር አይለይም
እምዬ ሚኒሊክ በዘመነ መንግሥታቸው በልዩ ጥበብ ያሳነፁት ቤተ መንግሥታቸው ከሳዑዲና ከፓኪስታን የመጡ ናቸው በተባሉ ባለሙያዎች እየታደሰ እንደሆነ ተነግሮናል። በምን ያህል ወጪ? በጀትና ዕቅድ የሚታወቅ ነገር የለም። አይ ፓኪስታንና ሳዑዲ? ስለዚህ ጉዳዩ የተጠየቁት የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣኑ አቶ ዮናስ ሀጎስ “ ስለ እድሳቱ የምናውቀው ነገር የለም ” በማለታቸው ምክንያት ባለሥልጣኑ ንግግራቸውን ተናግረው ሳይጨርሱ በንግግራቸው ብስጭት የገባቸው ወጣቱ ጠሚዶኮአችን ባለሥልጣኑን በፍጥነት በቀይ ካርድ ከሥልጣናቸው አስወግደዋቸዋል። [ አቶ ዮናስን በላሊበላ ጉዳይ ገና ፈጣሪ ራሱ የሚጠይቃቸው ቢሆንም] በዚህ በቤተ መንግሥቱ ዕድሳት ጉዳይ የጠሚዶኮው ግልጽ ያለመሆን ምክንያት መባረራቸው ግን ገራሚ ሆኗል።
ሁ ፦ የሚኒልክ ድኩላ
•••
የሚኒልክ ድኩላ ይህ ብርቅዬ እንስሳ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝበየዱር እንስሳ እንደሆነ ይነገራል። ይህ የዱር እንስሳ  በእምዬ ሚኒልክ ስም በመጠራቷ ምክንያት ብቻ በነጭ ሳርና በባሌ ተራሮች አካባቢ የሰፈረው የኦነግ ታጣቂ በአደን እየጨረሳቸው መሆኑን በድፍረት ከሚለቁት ፎቶ ግራፎችም  ማየት ተችሏል።  የኦነግ ወታደር የዱር እንሳትን እየጨረሰ ነው በህግ አምላክ።
ይህ የምትመለከቱት ምስል በባሌ ሲሆን በወለጋም ተመሳሳይ ድርጊት የኦነግ ወትደሮች ጥበቃዎችን እያሰሩና እየገደሉ የዱር እንስሳትን ለምግብነት ለመጠቀም እየጨረሷቸው ነው:: ይህን ጉዳይ በኢትዮጵያ የሚገኘው ብሔራዊ የዱር እንስሳት ጤና ጥበቃና መንግስት እንዴት እንደሚመለከተው የታወቀ ነገር የለም::
በተያያዘ መረጃ በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ ጥበቃዎች እየገረፉ እያባረሯቸው ነው፣ ጫሞ ሀይቅ ላይ አሳ የሚያጠምዱ ሰዎችም ቀን በቀን ያጠመዱትን ዓሳ ታጣቂዎቹ እየወሰዱባቸው ሲሆን የአ/ምንጭ ህዝብ አንድ ቀን ታጣቂዎቹ መጥተው ሊያጠቁን ይችላሉ የሚል ስጋት አድሮበታል፡፡
ይህን ጉዳይ በኢትዮጵያ የሚገኘው ብሔራዊ የዱር እንስሳት፣ ጤና ጥበቃም ሆነ የእንስሳት መብት ተሟጋቾች እንዴት እንደሚመለከቱት የታወቀ ነገር የለም፡፡
 የዐቢይለማጁሀር መንግሥትም በቸልታ እያየው መሆኑም ታይቷል።
በቀጣይ በኦነጋውያን ብላክ ሊስት ውስጥ ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁም ሚኒልካውያን የሚከተሉት ናቸው።
 
ሂ፦ የባህር ዛፍ።
በኢትዮጵያ የሚገኘውንና ለቤት መሥሪያም ሆነ ለማገዶ ኢትዮጵያውያን በሰፊው የሚጠቀሙበት የባህር ዛፍ ከአውስትራሊያ ያመጡት እምዬ ሚኒልክ እንደሆኑ ይታወቃል። እናም ከሚኒሊክ ቤተ መንግሥትና ከሚንሊክ ድኩላ ቀጥሎ ኦነጋውያኑ ባህርዛፍን ከምድረ ኢትዮጵያ በአዋጅ መልክ ያጠፉታል ተብሎም ይጠበቃል። ባህርዛፍ ጉድሽ ፈላ።
ሃ፦ የሚኒልክ ሆስፒታል
ሄ ፦ ሚኒልክ ትምህርት ቤት
ህ፦ ሚኒልክ ያስመጡት
• ባቡር
• ስልክ
• ፖስታ
• ቧንቧ ውኃ
• ወ.ዘ.ተ  በቀጣይ በኦነጋውያን እርምጃ ሊወሰድባቸው ይችላል ተብሎም ይጠበቃል። የሚኒሊክ ሃውልትም በመሃል አራዳ በፒያሳ ከመዘጋጃ ቤቱ ፊት ለፊት ተገሽሮ መቆሙ የብዙዎቹን ኦነጋውያን ጨጓራ እየላጠ መሆኑ ይነገራል።
•••
ነገርየው በአጭሩ ካልተቋጨ ወደፊት ሚኒልክ በሚል ስም የሚጠሩ ሰዎችም እንደ ድኩላዎቹ መታደን የሚቀርላቸው አይመስልም።
•••
Filed in: Amharic