>
5:13 pm - Thursday April 19, 2266

ከሆላንድ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን የተሰጠ የአቋም መግለጫ

ከሆላንድ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን የተሰጠ የአቋም መግለጫ

እኛ በኔዘርላንድ ሃገር የምንገኝ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፤  በወቅታዊ የሃገራችን የፖለቲካ ጉዳዮች እና በለውጡ ዙርያ የተጋረጡ ተግዳሮቶችን፤  እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ዙርያ እየተፈጠሩ ያሉ ውዝግቦች ላይ ሰፊ ውይይት አካሂደናል። ውይይታችን  የተቋጨው በእለቱ በተገኙ ተሳታፊዎች በወጣ  የአቋም መግለጫ ነው።  በውጭ ሃገራት የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ተወያይተው ተመሳሳይ የእቋም መግለጫ ያወጡ ዘንድ እንመክራለን።   በተከሰተው ችግር ዙርያ ያወጣነው ባለ ሶስት ነጥብ   የአቋም መግለጫ  የሚከተለውን ነው።

1. ለውጡን ተከትሎ የመጣውን መልካም የፖለቲካ ድባብ እያደነቅን ከዚህ ድባብ በተጻራሪ መልኩ በየክልሉ የሚታየው ህዝብን የመፈናቀል ተግባ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን።
2. ሃገራችን አሁን ያለችበት ችግር መዋቅራዊ መሆኑን እናምናለን።  ይህም የመነጨው ሕዝብ ሳይመክርበት የተጫነው ህገ- መንግስት ነው።  ዘላቂና መዋቅራዊ መፍትሄ ይገኝ ዘንድ ህገ- መንግስቱ በህዝብ ተሳትፎ ይሻሻል ዘንድ እንጠይቃለን።
3. አዲስ አበባ ላይ በአሁኑ ሰዓት እየታየ ያለው ውዝግብ መፍትሄው አፈና እና የሃይል እርምጃ ሳይሆን፣  ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር መምከር መሆኑ በጽኑ እናምናለን።  ለዚህ ግብ ተብሎ የተቋቋመውን አዲስ አበባ ባለ-አደራ ምክር ቤት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በሞራል፤ በፋይናንስ እና ዲፕሎማሲ የምንደግፍ መሆኑን ቃል እንገባለን።
21 አፕሪል 2019
አምስተርዳም
Filed in: Amharic