>

የወከለውን ህዝብ የሚታገል በዓለም የመጀመሪያው ድርጅት!!! (የሺሀሳብ አበራ)

የወከለውን ህዝብ የሚታገል በዓለም የመጀመሪያው ድርጅት!!!
የሺሀሳብ አበራ
” በአዲስ አበባ ላይ ኦሮሚያ ልዮ ተጠቃሚ እንዲሆን እንታገላለን–ብአዴን”፡፡ መልካም ትግል፡፡ ግን ማንን ነው የሚታገለው?  አማራን እኮ ነው፡፡ የሚገርም ነው፡፡ የወከለውን ህዝብ የሚታገል የዓለም የመጀመሪያው ድርጅት ሆነልን፡፡  እነ ጊነስ ቡክ ምናምን ቢመዘግቡልን ጥሩ ነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ በልዮ ሁኔታ ለኦሮሚያ እንድትሆን እታገላለሁ ካለ በኃላ ከሚሴ ሂዶ “በይፋ የኦሮሚያ  ክልል ሰንደቃላማን ዘርግቷል” ፡፡ ብአዴን አልተቻለም፡፡
 …
ስብሰባ  የገቡትም ብዙዎች የሚታገልላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ ድሬድዋ ከተማ 40:40:20 አደረጃጅቶ ተቀይሮ 40:60 ሆኗል፡፡ 40 ሶዴፓ ወስዷል፡፡ 60 በኢህአዴግ  ስም ኦዴፓ ወስዷል፡፡ ሀረር 50:50 ኦዴፓ አልቀበልም ብሏል፡፡ ምናልባት 70:30 ኦዴፓ እና የሀረር ሊግ ሊይዙት ይችላሉ፡፡ ይሄ ሁሉ የለውጡ ውጤት ነው፡፡ አዲስ አበባም የብአዴን ትግል ፍሬያማ ከሆነ 100 ለ 100 ለኦዴፓ ሊሰጥ ይችላል፡፡ ችግሩ ብአዴን ለጃዋር 100 ቢሰጠውም  ብአዴን ፅህፈት ቤቱ የኔ ብሎ ሊከራከር ይችላል፡፡ የብአዴን የከሚሴ አካባቢ ፅህፈትቤት ኦዴፓ ነው የሚል፡፡ ብአዴን የሚመራው ክልል ሰንደቅዓላማ፣ቋንቋ፣ ክልላዊ መዝሙር ከሚሴ አካባቢ አይታወቁም፡፡ መምሪያ ቢሮዎችም ክትትል የሚደረግላቸው ከአዳማ ነው፡፡ ብርጋዴል ጀኔራል ከማል ገልቹ በይፋ አደራጅቸለሁ ብሏል፡፡ ከሚሴ አካባቢ የተፈጠረው ችግር መንስኤም የምኒሊክ ባንዲራ መታየቱ ነው ብሏል፡፡ ከማል  ኦነግ ኦዴፓ ነው ብሏል፡፡ ብአዴን ኦዴፓን አምኖ አሞቦ ተቀምጦ እያለ አቶ ለማ ቻይና ላሽ ብለዋል፡፡ ይመቻቸው፡፡  ከዛ አቶ አዲሱ ብአዴን ከአምቦ እንደወጣ” አኖሌን ስንት ታግለን ያስገነባነው ሀውልት ነው፡፡ በአኖሌ አንደራደርም” ብሎ ብአዴን  ከዳው፡፡ የአምቦው መድረክም ብአዴን ነጥብ ጥሎ እንኳ በኦዴፓ ዘንድ ተቀባይነት ሳያስገኝለት ሰንደቃላማ ቀይሮ ስብሰባ ይዟል፡፡ መልካም ስብሰባ፡፡ መልካም ትግል፡፡
 …
አሁን ያለው ፖለቲካ አዘቦታዊ አይደለም፡፡ ልዮ ስራን ይጠይቅ ነበር፡፡ ወቅቱን የሚረዳ ሰው፣ተቋማትን የሚመራ  ብቁ ሹመኛ፣ ነገን እና ዛሬን  የሚገነዘብ   ካድሬ ይፈለግ ነበር፡፡ ስትራቴጂም ያስፈልጋል፡፡
 …
ሽማግሌ  እየሰበሰቡ  መቀመጥ ከባድ ነው፡፡ የፖለቲካ ሊሂቃንን እያማከሩ፣ቢሮ ቁጭ ብሎ አስቦ እንደመስራት ሁለት ወር ሙሉ ስብሰባ የጤና አይደለም፡፡
 …
ኦዴፓ በጃዋር ይመራል፡፡ ብአዴን ደግሞ  ግራህን ከመታህ ቀኝህንም ደግመህ ስጠው በሚል ለስላሳ ሽማግሌ ይመራል፡፡ ከዛ የሽማግሌ ምክር ሰምቶ ”  ከደራ በተጨማሪ አዲስ አበባንም ልስጥ” ይላል፡፡ ምነው ሸዋ!!
 ብአዴን የትናንት ጠላቱ ትምክህተኛ እና ነፍጠኛ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ  የአማራ ብሄርተኛ ነበር፡፡ የብአዴን የትናንት እውነት ህዋኃት ነበር፡፡ዛሬ ደግሞ ሌላ ሆኗል፡፡
 …
ብአዴን   በከማሴ ቢሮው ኦዴፓ እንደተባለበት በሌሎች  አካባቢም ይሄ በቅርብ ይገጥመዋል፡፡  በብሄራዊዉ ቴሌቪዝን ከሚሴ ዙሪያን በተመለከተ የኦሮሚያ  ክልል ግብርና ቢሮ መግለጫ እየሰጠ  ብአዴን እንኳን በጀት ሰጠሁ እንጂ ምን አገባኝ ይላል፡፡
 ….
ትኩረተ ቢስነት፣ የፖለቲካ ዝለት፣የተዛነፈ የስነ ልቦና  ስሪት  የብአዴን ልማዶች ናቸው፡፡ ብአዴን ባለሙያ እንጂ ፖለቲከኛ አለመሆኑም ሌላው ችግር ነው፡፡
Filed in: Amharic