>
5:13 pm - Saturday April 19, 3732

አጅሪት ፍትሕና ዐማራው  (ዘመድኩን በቀለ) 

አጅሪት ፍትሕና ዐማራው 
ዘመድኩን በቀለ
~ ፍትሕ ማለት እኮ የጉልበተኞች፦
• አገልጋይ ናት።
• አሽከር ናት።
• ገረድ ናት።
• ባርያ ናት።
• ታዛዥ ናት።
• ሎሌ ናት።
•••
ያውም በዚህ በዐማራ ጠል የብሔር ፖለቲካ ዘመን ኢኮኖሚውን፣ ወታደሩን፣ ደኅንነቱን፣ ፖሊሱን፣ ቢሮክራሲውን፣ ሚዲያውን ያለከልካይ፣ ያለ ገደብ፣ ያለተፎካካሪ የተቆጣጠረ ዐማራ ጠል ገዢና መንግሥታዊ ሥርዓት በነገሠበት ዘመን  99.9999 ያለምንም ጥርጥር እሱ ለአንተ፦
• ፊውዳልህ ነው።
• ባላባትህ ነው።
• አሳዳሪህ ነው።
• አሳዳጅህ ነው
• ገራፊ አስገራፊህ ነው
• ጌታህ ነው።
• ገዢህ ነው።
•••
እናም ወዳጄ ልቤ ሆይ አንተ ግን ውቧን ፍትሕ፣ ሚዛኗ ትክክል የሆነውን አጅሪት ፍትሕን ከፈለካት እንዲሁ፦
• በዋዛፈዘዛ አታገኛትም።
• በልመናም አታገኛትም።
• በልምምጥም አታገኛትም።
• በመሽኮርመም አታገኛትም፣
• በማልቀስም አታገኛትም።
• በመቅለስለስም አታገኛትም።
• በመብከንከንም አታገኛትም።
• በመብሰልሰልም አታገኛትም።
• በስብከትም አታገኛትም። አከተመ።
•••
ወዳጄ በጠማሞች ስብከት በ #መሲአ ዎች አንደዜ የለህም ከተባልክ ወዲያ አስሬ ብትፈራገጥ፣ ላይ እታች ብትል፦
• ብትገደል ለእነሱ አንተ የለህም።
• ብትታረድ ለእነሱ አንተ የለህም።
• ብትሰደድ ለእነሱ አንተ የለህም።
• ብትታሰር ለእነሱ አንተ የለህም።
• ብትቃጠል ለእነሱ አንተ የለህም።
• በቀስት፣ በመትረየስ፣ በጦር በገጀራ፣ በሰይፍ በካራ፣ በፈንጅ፣ በቦንብ፣ በመጥረቢያ፣ በድሽቃ፣ በሜንጫ ጭምር ብትገደል አንተ ለእነሱ አንድጊዜ የለህም ስለተባልክ የለህም። ስለሌለህ ደግሞ በጅምላ ብትረሸንም፦
አንደዜ በእነ #ፕመጋሲዶአ በአደባባይ የለህም ተብለሃልና ለአንተ ፦
• የሐዘን መግለጫ አይወጣልህም።
• በቴሌቭዥን መሞት መገደልህ አይነገርም።
• ጋዜጣው ራዲዮው ስለመታረድህ ትንፍሽ አይልም።
• ፓርላማው አያገባውም።
በቃ አንድ ጊዜ ፕሮፌሰሩም፣ ዶክተር ነኝ ባዩም። ጋዜጠኛውም የለህም፣ “ ዐማራ የሚባል የለም” ብሎ ዐውጆብሃልና አንተ ለጊዜው የለህም። ሞትህም፣ ስደትህም አይነገርም። እውነቱን ነው ደግሞ መኖርህን ማሳየት ያለብህ አንተው ራስህ ነህ እንጂ ከሌላ ስፍራ የሚመጣ ነብይ መጠበቅ የለብህም። ከሌለህ የለህም ነው።
•••
እደግመዋለሁ የለህም የለህም ነው። በቃ “ዐማራ የሚባል ብሔር የለም” ብለው በአደባባይ ማንንም ሳይሳቀቁ ሲሰብኩ በዐይንህ እያየህ፣ በጆሮህ እየሰማህ “ዐማራ ሲገደል” “ዐማራ አለ”  እንዲሉህ መጠበቅህ በራሱ ሌላ፦
• ዥልነት ነው።
• ሞኝነት ነው።
• የዋኅነት ነው።
• ፋርነት ነው።
• ሰገጤነት ነው።
•••
ልብ በል። በሰሜን ጎንደር ሰውን ከነ ከብቱ በእሳት ሲያቃጠሉ ፍትሕ የለችም። የራስ ደጀንን ተራራ ሲያጋዩ ፍትሕ የለችም። 90 ሺ ዐማራ ቤት ንብረቱን አጥቶ ዐውላላ ሜዳ ላይ ሲሰጣ ፍትህ የለችም። የገዢዎች ቅምጥ ስለሆነች ፍትህ ብቅ አትልም። ከሳሎን አትወጣም።
•••
ከዚያ በምሥራቅ ወሎ ዐማራው ሲገደል፣ ሲታረድ፣ አብያተ ክርስቲያናቱ በቦንብ ሲጋዩ አጅሬ ፍትሕ ከጊዜያዊ አሳዳሪዋ ጋር በሃላል ታሽቃብጥ ነበረ። ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር አብራ ታዘጠዝጥ ነበረ። ለገዳዮች ፍትሕ በራሱ በመከላከያ መኪና ስንቅና ትጥቅ ሲቀርብ አሳምራ ታውቅ ነበር። ንፁሐን ሲገደሉ፣ ሲሰደዱ፣ ሲዘረፉ ከጊዜአዊ ባሏ ከመከላከያው ከፍትሕ አስከባሪው ጋር ቆማ ታይ ትመለከትም ነበር። ፍትህ ጡንቻ ትወዳለች። ገንዘብ ያለው ትወዳለች። ደረቱ የተከፈለ ትወዳላች። መሣሪያ ያለው ወንድ ነፍሷ ነው።
•••
በካራ ቆሬ አዲስ አበባ ጫፍ፣ በለገጣፎ፣ በድሬደዋ፣ በሐረር፣ በጅጅጋ፣ በጋምቤላ፣ በናዝሬት፣ በምንጃር፣ በኢሊአባቦር፣ በወለጋ፣ ኢትዮጵያዊው ዐማራ ሲታረድ፣ ሲሰቃይ፣ ሲሰደድ ፍትሕ አሳምራ ታውቃለች። በቦታዎቹም ሁሉ ይሄ ግፍ ሲፈጸም ታውቃለች፣ በአካልም እዚያው ነበረች። ነገር ግን ዐማራው የፍትህ ተጠቃሚ እንዳይሆን በቁሙ ስለተፈረደበት ከመቁለጭለጭ በቀር፣ ከማለቃቀስ በቀር፣ ከመማጸን በቀር ምንም ሊያደርግ አልቻለም። ፍትሕም አልቃሻ ወንድ አይመቸኝም ብላ ታፌዝበታለች። ሁል ጊዜ እዬዬ አይመቸኝም ባይም ናት።
•••
ጃዋርና ኦህዴድ የሆነ ቦታ ሄደው ጉብኝት ካደረጉ በሚቀጥለው ቀን በዚያ አካባቢ ያለ ዐማራ በጅምላ ይገደላል፣ ይዘረፋል፣ ይደበደባል፣ ይፈናቀላል። ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ለጉብኝት ብሎ ከሀገር ከወጣ በማግስቱ የሆነ ቦታ፣ የሆነ ክልል የሆነ ነገር ተፈጥሮ ያየፈረደበት ዐማራ ጭዳ ይሆናል። ይታረዳል። ይሰደዳል። ደሙ እንደ ዓባይ ወንዝ በምድሪቱ ይፈሳል።
•••
አሁን የተያዘው እስትራቴጂ ዐማራውን እረፍት መንሳት፣ ሰላም ማሳጣት፣ በኢኮኖሚ ማድቀቅ ናቸው። ዐማራን እየረዳ ያለው ዐማራው ብቻ ነው። ለተፈናቃዩ እየደረሰ ያለው ዐማራው ለዐማራው ነው። ይሄ ከባድ የኢኮኖሚ ጫና በነገደ ዐማራው ላይ ለመፍጠር የተቀየሰ ስትራቴጂ ነው። እሳት፣ ግድያ፣ የጅምላ ፍጅት ይሄም የዐማራውን ስነ ልቦና ለመጉዳት የሚደረግ የሥነ ልቦና ጦርነት መሆኑ ነው።
•••
ዐማራውን አሁን ያለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አይረዳውም። አይታደገውምም። መከላከያ ሠራዊቱ ዐማራውን ከማንኛውም ወረራ አይታደገውም። አያስጥለውምም። ሱዳን ብትወረው፣ ህወሓት ብትዘርፈው፣ ኦነግ ቢገለው ሠራዊቱ ደንታም አይሰጠው። በዐማራ ጠል አዛዦች የሚመራው መከላከያ ዐማራውን ይረዳዋል ተብሎ በጭራሽ አይታሰብም። የመከላከያ ዋነኛ ሥራው በጅምላ ዘራቸው እንዲጠፋ ለሚደረጉት ዐማሮች ወገኖቻቸው እንኳ ደርሰው ከእልቂት እንዳይታደጓቸውና እንዳይደርሱላቸው መንገድ ዘግቶ ገትሮ መቆም ነው። ከዚያ የሚዘረፈው ተዘርፎ፣ የሚደፈረው ተደፍሮ፣ የሚገደለው ተገድሎ ሲያበቃ ሬሳ ለማንሳት መንገዱን ይከፍታል። ቀጥሎም በአሰቃቂ ሁኔታ የተጨፈጨፉ የዐማራ ፎቶዎችን በስልኮቻቸው እያነሱ በየማኅበራዊ ሚዲያው እንዲለጠፍ ያደርጋሉ። ይሄ ማለት ነገ በሌላ ቦታ የምትኖር ተረኛ ዐማራ ተገዳይ የሆንክ ዐማራ ራስህን ለመገደል፣ ለመሞት አዘጋጅ የሚል የስጋት መልእክት ለማስተላለፍ መሆኑ ነው። ይኸው ነው። በቀዳሚ ጦማሬ ላይ ያልኩትን አሁንም መልሼ እደግመዋለሁ።
•••
ፍትሕ የጉልበተኞች፦
• አገልጋይ ናት።
• አሽከር ናት።
• ገረድ ናት።
• ባርያ ናት።
• ታዛዥ ናት።
• ሎሌ ናት።
•••
እናም ሲጠቃለል ፍትህ አልቃሻ ወንድ አትወድም። አታፈቅርምም። አታገባምም። አትጋባም። አትጠጋም። ወዳጇም አታደርግም። ለፍትህ ወፍራም መሆንህ ደንታዋ አይደለም። ቀጭንና ትንሽ መሆንህም ጉዳይዋ አይደለም። ፍትህ ብቻ ወንድ እንድትሆንላት ብቻ ነው የምትፈልገው። ወፍራሟን አሜሪካ፣ ሰፊዋን ራሺያ፣ ትንሿን እስራኤል ፍትሕ ያገባቻቸው አቅም ስላላቸው። ገንዘብ ስላላቸው። ኅብረትና አንድነት ከጡንቻ ጋር ስላላቸው መሆኑን እወቅ። የኩባዋና የአሜሪካ ፍትሕ ይከባበራሉ። ሁለቱም የጉልበተኛ ቅምጦች ስለሆኑ ይከባበራሉ።
•••
ራስን መከላከል በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በቁርዓን፣ በሕገ መንግሥቱም ጭምር የተፈቀደ ነው። አልሞት ባይ ተጋዳይ መሆን እኮ የአባት ነው። መሞትህ፣ መገደልህ፣ መሰደድህ፣ መዘረፍህ ካልቀረና ዕጣ ፈንታህ እስኪመስል ድረስ ከተመላለሰብህ ጥፋቱ የሌላ የማንም አይደለም። የራስህና የራስህ ብቻ ነው። አከተመ።
•••
ስለ ፍልስጤም ህፃናት ሞት፣ ስለ በርማ እልቂት፣ ስለ ፈረንሳይ የአሸባሪ ጥቃት የፕሮፋይል ፒክቸሩን ቀይሮ ሲያለቃቅቅስ፣ ሙሾ ሲያወርድ፣ የምታየው ጎፍላ ሁላ ስለ ዐማራው መገደል እሰይ፣ የትአባቱ፣ ገና ይቀረዋል፣ በለው፣ ሲል የምታየው ከሆነ ያለመጠንቀቅ፣ ያለመዘጋጀት፣ የአንተው ችግር ነው ማለት ነው። ከምድረ ገፅ እስክትጠፋ ድረስ አይፋቱህም ማለት ነው። እናም ራስን መከላከል፣ ራስን ከጥቃትና ከእልቂት ከጅምላ ጥፋትም ለማዳን ያለመዘጋጀት የአንተና የአንተ ብቻ የራስህም ችግር ነው ማለት ነው። የትም ብትሆን ደግሞ አይቀርልህም። የትም ብትሆን አልኩህ። ሃላስ።
•••
የተቃዋሚ ፓርቲዎች የተፈጸመብህን አሰቃቂ ድርጊት ያወግዙልኛል ብለህ የምት ጠብቅ ከሆነ አንተ እልም ያልክ ሞኝ ነህ።
★ በሱማሌ ልጆች ላይ የተፈጸመውን ግድያ እናወግዛለን።
★ በኦሮሞ ልጆች ላይ የተፈጸመውን ግድያ እናወግዛለን።
★ በጋንቤላ ልጆች ላይ የተፈጸመውን ግድያ እናወግዛለን።
★ በትግሬ፣ በወላይታ፣ በሲዳማ፣ በጌዲኦ፣ በአፋር፣ በጉራጌ ልጆች ላይ የተፈጸመውን ግድያ፣ መፈናቀል ወዘተ እናወግዛልን ባዮቹ #የልጥና_የጨርቦሌ ፓርቲዎች #ለዐማራ ሲሆን የት እንደሚገቡ ታጣቸወለህ። ድርሽ ትንፍሽ አይሏትም። ድንገት ቢመጡ እንኳ ሟቹ ዐማራን ከመውቀስ በቀር ማዘናቸውን አይገልፁለትም።
•••
በሰሜን ጎንደር የሚገኙ ዜጎች ሞቱ ይሉልሃል እንጂ ዐማራ ሞተ አይሉልህም። በከሚሴ በተፈጠረ የእርስ በእርስ ግጭት በተፈጠረው የዜጎች ሞት አዝነናል ይልሃል እንጂ ዐማራ ሞተም አይሉም። በአዲሲቱ ኢትዮጵያ ዐማራ አዲሱ ስሙ ዜጋ ነው። ዜጋ ማለት በአራዶች ቋንቋ ደግሞ የውጭ ሀገር ፈረንጅ ነው። ፈረንጅን አራዶች ሲጠሩት ዜጋ ነው የሚሉት። እናም ዐማራ ማለት ለእነሱ ፈረንጅና የውጭ ሀገር ዜጋ ነው ማለት ነው። ሞተ ማለት እኮ ነውር ነው። እንዲያውም ሞቶም ይወቀሳል።
•••
የብሔር ፖለቲካ ያጠፋናል ይልሃል የኦነጉ አባል፣ የኦህዴዱ መሪ። ዐማራ ሲደራጅ ብቻ ነው ለነ ጨርቦሌ ኢትዮጵያ ስጋት የሚገባት። ዐማራ ሲደራጅ ብቻ ነው ለእነ ልጥ ነስር የሚመጣባቸው። የትግሬ ነፃአውጪ ነኝ ብሎ የፓርላማ ወንበር ይዞ፣ የሚንስትር መሥሪያ ቤት እየመራ የተቀመጠውን ጮጋ ብሎ ጥቃት በዛብኝ ብሎ ራሱን ለመከላከል ጎንበስ ቀና የሚለውን ድራሹን ለማጥፋት ይንበጫበጫሉ። ለማንኛውም በመጨረሻም ልንገርህ።
•••
ፍትሕ የጉልበተኞች፦
• አገልጋይ ናት።
• አሽከር ናት።
• ገረድ ናት።
• ባርያ ናት።
• ታዛዥ ናት።
• ሎሌ ናት።
•••
ሻሎም !  ሰላም ! 
ሚያዝያ 21/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic