>
5:13 pm - Saturday April 19, 7434

ሰውን በማፈን  ኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬስ ነጻነት አለ ብሎ መደስኮር የትም አያደርስም (ከጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ)

ሰውን በማፈን  ኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬስ ነጻነት አለ ብሎ መደስኮር የትም አያደርስም

 

ከጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ

 

ኢትዮጵያ ላለፉት  በርካታ አመታት የፕሬስ አፈናን በማፈንና በማሰር ከኤርትራ በመቀጠል እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሁለተኛ ስፍራን በመያዝ ግንባር ቀደም ሀገር ነበረች።

የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ስልጣን ከተረከቡ በኋል የተሳሩ ጋዜጠኞች የተፈቱ ከመሆኑም ባሻገር የተዘጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ድህረ ገጾች ሲከፈቱ በውጭ የሚገኙ የሚታፈኑ በአማርኛ የሚተላለፉ  የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች  የመታፈናቸው ሁኔታ ቀርቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሮ ጭምር ከፍተው እንዲንቀሳቅሱ ተደርጓል ይህ ብቻ አይደለም የተለያዩ  በውጭ የሚገኙ የፖለቲካ አራማጆች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል ይህ ኢህአዲግ እንደ አንድ ትልቅ በጎ እርምጃ አድርገን የወሰደው ነገር  እንደሆነ እናምናለን።በዚህም የተነሳ በዓለም አቀፍ የሰበአዊ ድርጅቶችና በጋዜጠኞች ተሟጓቾች ዘንድ ጥሩ ተቀባይነት እንድታገኝ አስችሏታል።

በሌላ በኩል  በሀገራችን  እያየን ያለው  ሁኔታ ግን ለውጥ ሳይሆን ቁማር ጨዋታ መሆኑን በበኩሌ ተገንዝቤአለው ይህ ደግሞ  በኢህአዲግ  ብቻ ሳይሆን በተቀዋሚ  ፖለቲከኞች ጭምር መሆኑ በጣም ያሳዝናል ። በተለይም  ኢህአዲግም ሆነ ላለፉት በርካታ አመታት በውጭና በኢትዮጵያ ተቀዋሚ ሆነው ፖለቲካቸውን ሲያራምዱ የነበሩ ወገኖች ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን ውስጥ እያሳዩት ያለው ሁኔታ በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ ላለነው ወገኖች ለውጥ ሳይሆን ከአራድነትና ከአፍ ጅምናስቲክ ያልዘለለ መሆኑን አብዛኛዎቻችን  ያራዳ ልጆች  የምናውቀው እውነታ  ከመሆኑም ባሻገር ለውጥን ከእግዚአብሔር በስተቀር ማንም እንደማያመጣ ተገንዝበን  በአሁኑ ወቅት የጣለውን ተስፋ በፖለቲካኞች ላይ ቆርጦ አርፎ ተመልካች ሆኖ ቁጭ ብሏል። በፊትም ሆነ አሁን ሁሉም ኢህ አዲግ ካልሆነ ወይንም በፎረምና በጥቃቅንና በአነስተኛ ካልተደራጀ በስተቀር ሥራ መስራት እስካሁን ድረስ አይቻልም። አሁን ደግሞ በተለይም በፕሬሱ ላይ እያየሁት  ያለው ሁኔታ ከዚሁ ያልዘለለ ከመሆኑም ባሻገር ለውጥ ሳይሆን  ቁማር ጨዋታ እየሆነ መምጣቱ በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ሆኖ አይቸዋለሁ  ። በጣም የሚገርመው በፊት  ጋዜጣኛውን የሚያሳስሩት እየጠቆሙ ጋዜጣ አከፋፋዮች ነበሩ አሁን ድግሞ ጭልጥ ያሉ ወያኔ ጭምር ሆነዋል።

«የፕሬስ ነፃነት አለ ፤ ከበፊቱ የተሻለ ነው ፤ በፊት መሐይምጋዜጠኛ  ብቻ ነበር የሚሰራው ፤ አሁን ግን የተማሩ ናቸው !» በማለት እያናፉ ይገኛሉ።  ይህ ብቻ አይደለም ታስረው የነበሩና ውጭ የሚገኙ ጥገኝነት አግኝተው ጋዜጠኝነቱን ትተው ወደ ፖለቲካ ውስጥ የገቡ በጋዜጠኛ ስም የሚነግዱ የደርግ ካድሬ የነበሩ መቶአለቃዎች ዛሬ ደግሞ እንደ ጅምናስቲክ እየተገለባበጡ  የወያኔ አፈቀላጤዎች  መሆናቸው ብቻ ሳያበቃ ፤በተለይም መስዋትነት በከፈልነው በነፃ ፕሬስ ስም እየነገዱብን መሆኑ የሚያሳዝን ነው። የግል ጋዜጠኞች ያልሆኑ በስደት የሚገኙ የመንግስት ጋዜጠኞች ዛሬ የግል ጋዜጠኞች ተብለው ስማቸው ተደርድሮ  ከግል ጋዜጠኞች ጋር ተካተው ማየቴና በዓለም አቀፍ መድረክ መሰደባችን በጣም የሚያሳዝን ነው። ሌላው ቀርቶ ታስረው የነበሩ የግል ጋዜጠኞች ለምሳሌ እንደ ወሰንሰገድ ገብረኪዳንን ያሉ አድርባዮችም እንደዛ በርካታ መስዋትነት እንዳልከፈለ ዛሬ ደግሞ አድርባይ ሆነው ያሉ  የወያኔ አጨብጫዎች  በርካታ ናቸው ።እንዲያውም ጭራሽ  እራሴን እንድፈትሽና ከማን ጋር ነበር የምሰራው እንድልና እራሴንም እንድጠራጠር አድርጎኛል።  እኔም « ሳላውቀው እኔም ወያኔ  ነበርኩ ? »  እንድል ና እራሴን እንድጠይቅ አስግድዶኛል።

ሕንድ ሀገር ውስጥ በአንድ ስም  ስር ውስጥ የተለያዩ ፍቃድ አውጥተው ተመሳሳይ ሥራ የሚሰሩ በርካቶች ናቸው በፕሬስ ነጻነም ቢሆን  በአሁኑ ውቅት ሕንድ ከኢትዮጵያ አትሻልም ምክንያቱም በፎርጅድና በማጭበርበር ስለምትታወቅ፤  ኢትዮጵያ ውስጥም ያለው እውነታ ይኽው ነው ፤ አብዛኛው ሚዲያ የግል ተብለው የግል ያልሆኑ ናቸው።

በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የግል ጋዜጠኛ የነበሩ ፍቃድ ተከልክለው ተመልካች ሆኑዋል፤ እስክንድርም ነጋም «ኢትዮፒስ» ን  ይዞ ያለማስታወቂያ እስከጊዜው እየተፍጨረጨረ ነው ፤በየጊዜው የወረቀት መናር  እሱንም እስከተወሰነ ጊዜ ብቻ ቢሰራ ነው ፈንድ ካላገኘ የእሱም  ጋዜጣ ቋሚ ነው።በእርግጥ እሱም ብዙ ስለታሰረና ስለተንገላታ ወያኔ  ለፖለቲካ መነገጃው ሲል ጋዜጣውንና እሱን ስለሚፈልገው  «ኢትዮፒስ» ብዙ ልትቆይ ትችላለች የሚል እምነት አለኝ ።ይህ የእኔ አመለካከት ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔ እራስምታት በእሥራ በተለይም እውነትን ይዘው የሚጓዙ ከሆኑ ሀገር ውስጥ ገብቶ መወጣት አስቸጋሪ ነው የሚሆንቦት እንደቤርሙዳ  ትሪያንግ ተውጦ መቅረት የሚቻልበር ሀገር ሆኗል። ስለዚህ  ወደ ኢትዮጵያ አለመምጣት ይመረጣል። አንድ ምሳሌ ላቅረብ የራሴን፤  ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ኢትዮጵያ ለመቅረት ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ለማየትና ለማጥናት  እንዲሁም መጽሐፍቶቼን ለማሳተም ነበር ፤ ይህንንም ሳደርግ ቤተሰቤን ትቼ የሚመለከታቸውን  የሀገሪቱን ሰዎች አስፈቅጄ በሕጋዊ መንገድ ነበር  ወደ ኢትዮጵያ የገባሁት ሆኖም እረዳትና አጋዥ ወደ ሌላቸው ቤተሰቦቼ  ቶሎ መመለስ ግን እንዳሰብኩት አልቻልኩም።በፊት ያለሁበት  ሀገር ሰዎች «እንዴት እንዲ ያረጉኛል ? ፈቅደውልኝ፤ችግር የለም ብለውኝ !» ብዬ ተናድጄባቸው ነበር ም በኋላ ግን ሳጣራ የወያኔ እጅ እንዳለበት ለማረጋገጥ ስለ ቻልኩ ቅሬታዬን አንስቻለው፤ በኢትዮጵያ ያሉ ኢምባሲዎች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በጣምራ ይሰራሉ በመሆኑም ኢምባሲ ውስጥ ያሉ አበሾች «ምን ታደርግ ትሄዳለ? ጃፓኒስቶችን ኢትዮጵያ ውስጥ አግኝቼ  ስለነበረ እንዲረዱኝ  ስጠይቅ ተመልክተው እነሱ እኮ ምንም አያገባቸውም እኛ ካልፈቀድን ፤ በጊዛዊ ቪዛ  ደግሞ መሄድ አትችልም ወዘተ» በሚል  የኢምባሲው ሰዎች ጭራሽ ለፖሊስ አሲዘውኝ  ይሄው ሥራ ፈት ሆኜ ኢትዮጵያ ውስጥ አለው፤ በጣም የሚገርመው ጀርመን ለሥራ ለመሄድ ግብዥ ተደርጎልኝ ሁሉንም አጠናቅቄ ለኢምባሲው ጥያቄ አቅርቤ ያውም ጃፓን ሆኜ ስሠራላቸው  የነበረው ጀርመኖች ችግር ሳይፈጥሩብኝ  አበሾቹ «ጀርመን ስለምትጠፈ (ትጠፋለ)ተብሎ ቪዛ ተከልክለሀል» መባሌ ደግሞ ይበልጥ ነው ያስገረመኝ ፤ያውም ለውጥ እየታየ  ነው በተባለበት  ሀገር «ትጠፋለ» ተብሎ አበሾቹ ቪዛ መከልከላቸው ምን ይባለል።ብጠፋስ ምን አገባቸው። አበሻ እንደሚታወቀው ምቀኛ አይደል ? በዚህ ላይ እኮ ሕግ ያለማወቃቸው  ነው ያስገረመኝ።

ጃፓን ውስጥ ጥገኝነት ማግኘት ከባድ ነው ፤ እንደሌላው ሀገር በደቦ  ትርኪምርኪውን  አይቀበሉም፤ እስካሁን ጃፓን ጥገኝነት ካመለከቱት ከ50 ሺህ የተለያዩ  ሀገር ስደተኞች መካከል  ጥገኝነት የሰጠችው ከ650 በታች ነው ይህ የሚያሳየው ጃፓኖች በዚህ በኩል ጠንቃቆች መሆናቸውን የሚያሳይ ነው ፤ ከተሰጣቸው ጥገኝነት መካከል ደግሞ ኢትዮጵያዊ  አንዱ ደግሞ እኔ ነኝ ፤አሁን የደረሰብኝ ሁኔታ ሲታይ ደግሞ ጃፓኖች ለእኔ ጥገኝነት መስጣታቸው ትክክል መሆናቸውን  በትክክል የሚያሳይ ነው ።

አንድ ሰው ጥገኝነት አንድ ሀገር ጠይቆ ተሰጥቶት እያለ ሌላ ሀገር ጥገኝነት ትጠይቃለ ብሎ ቪዛ  እንድከለከል ማድረግ ሕግን  አለማወቅ ብቻ ሳይሆን አንገት የሚያስደፋ ጭምር ነው፤ይህ ብቻ አይደለም   የበርካታ ሰዎችን ጉሮሮ ጭምር መዝጋት ሆኖ ነው ያገኘሁት ።

ሰውን በማፈን  ኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬስ ነጻነት አለ ብሎ መደስኮር የትም አያደርስም ምክንያቱም እኔ የምኖርበት ሀገር በጣም ያደገ ሀገር ብቻ ሳይሆን በመንፈስ የሚመራበት ሀገር ጭምር ነው ይህ ብቻ አይደለም በፋክት ፤በሪያሊቲና በሎጂክ የሚታመንበት ሀገር ውስጥ ነው ያለሁት ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳዬ እስከሚያልቅልኝ  ድረስ ሥራ ፈት የበዛበት ሀገር ስለሆነ ያለሁት ሕሊናዬን ሸጬ ከምኖር ሥራ ፈት ሆኜ  መቆየትን መርጫለው ፤ ለማንኛውም  ፍርዱን ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነው የምጠብቀው። ሰላም!

Filed in: Amharic