>

አጼ ምኒልክ በኢትጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም መኪና በመንዳት የመጀመሪው ናቸው!!! (ጳውሎስ ኞኞ)

አጼ ምኒልክ በኢትጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም መኪና በመንዳት የመጀመሪው ናቸው!!!
ጳውሎስ ኞኞ
ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነችው መኪና አዲስ አበባ  በደረሰች ጊዜ የመኪናዋ አጠቃላይ ሁኔታ ምን እንደሚመስል መኪናዋን ይዞ የመጣው ቤንትሌይ ካስረዳ በኋላ አጼ ምኒልክ ከጓኑ ተቀመጠው ተጓዙ ከዚያም አነዳዱን በሚገባ ሲመለከቱ ስለነበር በሚቀጥለው ቀን መጥተው መንዳት እንደሚለማመዱ ተናገረው ወረዱ፡፡
ንጉሡ እንዳሉትም በሚቀጥለው ቀን ወደ መኪናዋ ሄደው የሹፌሩን ቦታ ይዘው በራሳቸው የመኪናውን ሞተር ማስነሳትና ማጥፋት ለመዱ ከዚያም በአለማማጃቸው አማካኝነት ነዳጅ መረገጫ ፍሬን መያዣውን በሚገባ እየለዩ ተረዱ ፡፡ በዚህ መንገድ ለጥቂት ቀናት ልምምድ ካደረጉ በኋላ በአዲስ ዓለም መንገድ ላይ መንዳት ጀመሩ፡፡
አጼ ምኒልክ አነዳዳቸው እንደጀማሪ አልነበረም ትክክለኛውን መንገድ ይዘው የመኪናውን ሚዛን ጠብቀው ነበር የሚያሽከረክሩት፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ መኪናውን ያመጡትን ፈረንጆች አስገርሟቸው የነበረው አጼ ምኒልክ እየነዱ በመንገድ ላይ መሰናክል ሲያጋጣማቸው ምንም ሳይደናገጡ መስናክሉን የሚያልፉበት ወይም መኪናውን የሚያቆሙበት መንገድ ነበር፡፡
በዚያው ሰሞኑም አጼ ምኒልክ መኪና እያሽከረከሩ ሳለ ከአለማማጆቻቸው መካከል አንዱ የነበረው ሰው አድንቆቱን እየደጋገመ ሲገልጽላቸው አጼ ምኒልክ የመንገዳቸውን ፊት ለፊት ብቻ እየተመለከቱ “መኪና የሚነዳን ሰው ማነጋገር ክልክል” ነው አሉት፡፡ ፈረንጁም ይህን ሕግ ለንጉሡ አልነገረም ነበርና በምን አወቁት ሲል የበለጠ ተገረመ፡፡ የእምዬ ምኒልክ የማሽከርከር ብቃት የተመለከተው ሄልም በመጽሐፉ “Perfect Deriver ” ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡
ምንጭ፦ ዳግማዊ ምኒልክ የአዲሱ ስልጣኔ መስራች በሥርግው ሐብለሥላሴ
– አጤ ምኒልክ ጳውሎስ ኞኞ

ጎግልና ዳግማዊ ምኒልክ!!!

ቻምየለህ ታምሩ
Google;
“112 years ago,  in 1907, King of Kings Menelik II was the first African to drive a car”
የዘመኑ ገጣሚ፤
 ባቡሩም ሰገረ፤ ስልኩም ተናገረ፤
ምኒልክ መልዓክ ነው፤ ልቤ ጠረጠረ።
Google (translate); 
The train is running and the phone is ringing;
MENELIK is Angel that’s what I’m feeling !  🙂
Filed in: Amharic