>

ዘንዘልማ ላይ ከነበረ የ አሳምነው ጠባቂ የተገኘ መረጃ !!! (ወልቃይት ጠገዴ)

ዘንዘልማ ላይ ከነበረ የ አሳምነው ጠባቂ የተገኘ መረጃ !!!
ወልቃይት ጠገዴ
 ጠባቂው ይህንን መረጃ ከሰጠ ከሰዓታት በሗላ ማግኘት አልቻልንም ( ምናልባት ገለውታል )
በግድያው ሰዐት የነበሩት አብዛኛዎቹ የካቢኔ አባላቶች ያልሆኑ ሰዎች ነበሩ። እነ ጀነራል ሰዐረ በስብሰባው አዳራሽ ግቢ ውስጥ ከ አሳምነው ፅጌ ቀድመው ነበር የተገኙት።
ስብሰባው ከመጠራቱ በፊት አሳምነው ያስመረቃቸው የክልሉ ሚሊሻዎች በባጀት ምክኛት ደሞዝ እንደማይከፈላቸው በክልሉ ሊቀመንበር ለ አሳምነው በደብዳቤ ደረሰው
ይህንን ተከትሎ የ እስክንድር መምጣት ላይ ከፍተኛ እሰጣ ገባ ከመፈጠሩ አልፎ እስክንድርን ለመቀበል ክልሉ ባጀት ስለሌለው የእስክንድር ስብሰባ መዘረዝ አለበት ብለው ይጠይቁታል።
ከዚህ በተጨማሪ አሳምነው ከስልጣን መውረዱን አንዳንድ የክልል ባለስልጣኖች ቀድሞ የተነገራቸው ሲሆን ፣ ከ ብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ የተወሰኑት እነ ሰዐረ አሳምነውን ለመውሰድ እንደሚመጡ ቀድሞ መረጃው ደርሧቸው ነበር።
የ አምባቸው ጠባቂዎችም በቅርብ ጊዜ የፌደራል ፖሊስ ጠባቂዎች እንዲሆኑ ተደርጎ ነበር። ይህ አሳምነው ድሮም አምባቸውን መግደል ይፈልግ ነበር ለማለት በነ አብይ የተቀመረ ቁማር ሊሆን እንደሚችል እንገምታለን።
አሳምነው ወደ ስብሰባ አዳራሹ ለመግባት ከ አጃቢዎቹ ጋ ሆኖ ሲመጣ በሩ ላይ አምስት የፌደራል ወታደሮች ያያል። ጀነራል ሰዓረም ወደ አዳራሹ ለመግባት በቀስታ እየተጓዘ ነበር። ምናልባች የ ሰዐረ እርምጃ ሆን ብሎ በጥናት የተደረገና የ አሳምነውን ሃሳብ ለመሰብሰብ ታስቦ የተደረገ ሊሆን ይችላል። አሳምነው ግን ሃሳቡን በሙሉ በስብሰባው አዳራሽ ላይ ባሉት አምስት ፌደራሎች ላይ ያደርጋል። ፌደራሎች በተጠንቀቅ እርምጃ ለመውሰድ ትዕዛዝ ብቻ ይጠብቁ እንደነበር አሳምነው በሁኔታቸው ይረዳል። ይቁነጠነጡ ነበር። ሁለቱ እጃቸውን የያዙት የክላሽ ምላጭ ላይ አድርገው ፣ ክላሻቸውን አፈሙዙን ወደ መሬት አዙረው ይዘዋል። አሳምነው ለ አጃቢዎቹ በፍጥነት እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጁ ፣ አፍነው ሊወስዱኝ ነው የመጡት አላቸው። የ አሳምነው አጃቢዎች ትዕዛዙን ቢሰሙም አዲስ ተመራቂ በመሆናችው እና ልምድም ስለሚጎላቸው ምላጩኝ ለመሳብ እርግጠኞች አልነበሩም ፣ አሳምነው ወደ ስብሰባ አዳራሹ ሲጠጋ ፣ እጁን የመሳሪያው አፈሙዝ ላይ ያደረገው አንዱ ፌደራል ፣ በዝግታ አፈሙዙን ወደ አሳምነው ለመደገን መሳሪያውን ቀና ሲያደርግ ፣ አሳምነው በፍጥነት እርምጃ ወሰደ። ከ አምስቱ ሶስቱን ሲመታቸው ፣ ሁለቱ ዘለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ገቡ፣ አሳምነውም በፍጥነት ወደ አዳራሹ ተከትሏቸው ገባ። በወቅቱ የ አሳምነውን መያዝ እንዲቀርፅ የተላከው ካሜራ ማን ይህንን ትዕይንት በሙሉ ቀርፆታል።
ጀነራል ሰዐረ ወደ አዳራሹም ሆነ ወደ መኪናው ሮጦ ለመግባት ጊዜ ያገኘ አይመስለኝም ይለኛል ይሄ ሰው።
መረጃውን እንደሰጠኝ ሰው ከሆነ ( ይኽ ሰው ከ አሳምነው አጃቢዎች አንዱ የነበረ ሲሆን ዘንዘልማ ላይ ሳለ ለማነጋገር ችለን ነበር ) ፣ ምናልባች ካሜራ ቀራጩ የሶስቱን ፌደራሎች እና የ ሰዐረን ሞት በካሜራው እይታ ውስጥ ማስገባት ችሏል። ምናልባችም አብይ ይህንን ካሜራ ቀራጭ በ ጀነራል ሰዓረ ሞት ( አዲስ አበባ ላይ ሰዓረን የገደለው ጠባቂ ) በሚል የተቀዳውን መረጃ በ እጃቸው ካስገቡ በሗላ ገለውታል የሚል ግምት እንዳለውም ነግሮኛል። ወይም ደሞ ለቤተሰቦቹ በተኩስ ልውውጥ ጊዜ ሞተ ብለው የድብቅ መርዶ ( ህዝብ የማያውቀው መርዶ ) ሊያረዷቸውም ይችላል። የህወሓት ባለስልጣኖች ይህንን መረጃ ከ አብይ አህመድ ዘንድ ኮፒውን ልከው እንዲያዩት እንደሚያደርጉ እንገምታለን።
በሌላ መረጃ ህወሓት ሰዐረን የገደለው አብይ አለመሆኑን ፣ ይልቅ ሰዐረ አሳምነውን አፍኖ ለመውሰድ የሔደውን የፌደራል ስኳድ ለመምራት እንደሔደና ፣ በ ጊዜው ስለተፈጠረው ሁሉ ሙሉ መረጃ እንዳላት ማሳወቅ እንወዳለን። የ አብይን ድራማ ብልሽትሽቱን ያወጣው የ አሳምነው ያልተጠበቀ ቅፅበታዊ ውሳኔ ሲሆን ፣ አሳምነው ከስብሰባው አዳራሽ በደረሰ እና ተኩስ በተከፈተ በ ግምት በ ስምንት ደቂቃ ውስጥ የደረሰው ኄሊኮፕተር እንደታቀደው አሳምነውን ሳይሆን አምባቸውን እና ሰዐረን በፍጥነት ወደ አዲስ አበባ ይዞ ለመሄድ ተገዷል።
ዝርዝር መረጃዎችን እና ከግድያው በፊት የነበሩ የቃላት ልውውጦችን ወደፊት እንደ አስፈላጊነቱ ለህዝብ ይፋ አደርጋለሁ።
በይበልጥ በ አሳምነው መሪነት ወልቃይትን የመታደግ ሚሽን ላይ ከተሰማሩት ውስጥ ለህወሓት መረጃ አሳልፈው በመስጠት የወልቃይት ሚሽን መኮላሸትና ፣ በይበልጥ ዘንዘልማ ላይ ገበሬው << አሳምነው እዘዘን ገደለው >> የሚለው መረጃ ቀድሞ መድረሱና እዘዝ የዚያ አካባቢ ተወላጅ በመሆኑ አሳምነውን አላሳልፍ ማለታቸው፣ ገበሬው ባለማወቅ ጀግናቸው ላይ መንገድ መዝጋታቸው እና መሰል ታሪኮችን በዝርዝር እፅፋለሁ።
Filed in: Amharic