>
10:12 am - Wednesday November 30, 2022

በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በአማራው ክልልና በአዲስ አበባ ወጣቶችን እያፈኑ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በእስር ቤት ማጎር በአስችካይ እንዲቆም ለኢትዮጵያ መንግስት የተላለፈ ጥሪ።

ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት
Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE)
PO Box 1836, Rancho Cordova, CA 95741 Telephone: (877)746 -4384
Website: www.globalethiopia.org
Email: info@defendethiopians.org
All Lives Have Equal Value!

 

በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በአማራው ክልልና በአዲስ አበባ ወጣቶችን እያፈኑ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በእስር ቤት ማጎር በአስችካይ እንዲቆም ለኢትዮጵያ መንግስት የተላለፈ ጥሪ።

 

ግሎባል አልያንስ ከተቋቋመበት ግዜ ጀምሮ ለአለም አቀፍ መርሆወችና ለስብአዊ መብቶች መከበር በኢትዮጵያም ውስጥ ይሁን በወጪ አገራት ኢትዮጵያኖች በሚደርስባቸው የስብዓዊ መብት ጥስት በግንባር ቀደምትነት ስብአዊ መብታቸው እንዲከበር ለዓለም አቀፍ የስብአዊ መብት ተቋማትና ለኢትዮጵያ መንግስት ያለምንም ቅደመ ሁኔታ የዜጎቻችን መብት እንዲከበር የራሱን አስተዋጽኦ ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው። በተለይም ላለፍት 27 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞችና የመብት ተማጋቾች በነጻነት ሃሳባቸውን ስለገለጹ ብቻ ያለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ ሲታስሩ፤ ሲገረፉ፤ ሲገደሉ እና ሲስቃዩ ያሳለፉት ዘመናት ገና ሳይረሳ በተለይም በአሁኑ ስአት በሃገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ መጥቷል በሚባልበት ግዜ እና ሃገሪቱን የሚመሩት ጠቅላይ ሚንስትር በኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ይሁን ማን አስቀድሞ ማጣራት ሳይደረግና የፍርድ ቤት ትእዛዝ ሳይወጣ አንድም ስው እንዲታስር አንፍቅደም በማለታችው ምክንያት ከአለም አቀፍ ተቋማት አምንስቴ ኢንተርናሽናልና የመሳስሉት ድርጅቶች ሳይቀር እውቅና በተስጣቸው አንድ ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ፤ በተለይ
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ከሁለት መቶ ሰባ በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባና የሊሎች ነዋሪዎች ታፍነው ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል። እየተገረፉ ነው። በሽብርተኛነት እየተከሰሱ ነው።

ይህ የህወሓት መራሹን አፋኝና ጨቃኝ መንግስት ስራ የሚያስታውሰንና የሚመስል አድራጎት በአገሪቷ ውስጥ መጥቷል የሚባለውን ለውጥ ተስፋ ስጪ መሆኑ ቀርቶ ኢትዮጵያዊያኖች መጪውን ግዜ በጭንቀትና በፍርሃት እንዲመለከቱት ከማድረጉም ባሻገር ያለፈው የመከራና የአፈና ዘመን መልሶ መምጣቱን ከወዲሁ አመላካች እንደሆነ ያሳያል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየታየው ያለው የብሄር ልዩነቶች ከጊዜ ወደጊዜ መጠኑ ስር እየስደደ በመሄዱ መንግስት ለዚህ ትኩረት መስጠት እንዳለበት ለመለፅ እንወዳለን:። በተለይ በዐማራውና ኦሮሞ ባልሆነው ሕዝብ ላይ በቡራዩ፤ በሰሜን ሸዋ፤ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ፤ በልዩ ልዩ የኦሮሞ ክልል ስፍራዎች ላይን እጅግ የሚዘገንን ብሄር ተኮር እልቂትና አፈና እየተክሄደ ነው።

ይህ አድራጎት ጠቅላይ ሚንስትር ዓቢይ ገና ወደ ስልጣን እንደመጡ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከአንድ ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች ታፍነው ከተያዙ በኋላ ወደ ጠቅላይ የጦር ማስልጠኛ ካምፕና ወደ ስንዳፋ የጦር ካምፕ ተወስደው ከፍተኛ ድብደባና የስብአዊ መብት ጥስት ከተፈጸመባቸው በኋላ በግድ አጥፈተናል እንዲሉ ከተደረጉ ከወር በኋላ ወደ የቤተስቦቻችው መመለሳቸው የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው። አሁንም ቁጥራቸው የማይታወቅ ወጣቶች ወደ ሰንዳፋ ተወስደው እርህራሄ የጎደለው ግርፋትና እንግልት እየተፈጸመባቸው ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ኢንተርኔት እንዳይተላለፍስለከለከለ ሃቁን መከታተል አልተቻለም። የኢንተርኔት መገናኛ መቋረጥ ዋናው ዓላማ ለአፈናው አመች እንዲሆን ነው።

ስለዚህ በአሁኑ ስአት በማንኛውም ስልጣን ደረጃ ላይ ያሉ የመንግስት ባለስልጣናት የፍትህ አካላት እና የፓሊስ ሃይል ልብ ሊሉት የሚገባው ያለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝና የወንጀል ድርጊት ማስረጃ ሳይቀርብባቸው ዜጎችን በድንገት አፍኖ እስር ቤት ማጎር አለም አቀፍ ህግጋትን የጣስና የግለሰብን ስብአዊ መብት በእጅጉ የሚጎዳ ከመሆኑ ባሻገር ይህንን ህገወጥ አድራጎት የሚፈጽሙትንም የመንግስት አካላት ተጠያቂ እንደሚያደርግ ከወዲሁ ግሎባል አልያንስ ማሳስብ ይወዳል ።

ይህ ጭፍንና አደገኛ የፌደራል መንግሥት አፈና በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን። የኢንተርኔት አገልግሎት ያለምንም ገደብ እንዲሰራጭ እንጠይቃለን። በመጨረሻም በአዲስ አበባ ውስጥ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታፍነው የታስሩ ዜጎቻችን ያለምንም ቅደመ ሁኔታ በአስቸካይ ከእስር እንዲፈቱና ዳግመኛም እንዲህ አይነቱ ህገ ወጥ አስራር የሃገሪቱን ዜጎች እጅግ የሚያሳዝንና ሃገሪቱ የምታደርገውን የለውጥ እንቅስቃሴ ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚያሸጋግር እናሳስባለን።

በመጨረሻ፤
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት፤ የክልል ባለሥልጣናት፤ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፤ የማህበረሰብ ድርጅቶች፤ መንፈሳዊ አባቶችና እናቶች፤ ወጣቶች፤ ምሁራንና ሌሎች ባለድርሻዎች በጋራ አስቸኳይ ብሄራዊ ውይይት እንዲያደርጉና ወደማይመለስ ጫፍ የደረሰችውን ኢትዮጵያን ከአደጋ እንዲታደጓት ጥሪ እናደርጋለን።

ሰብ አዊ መብቶች ይከበሩ!!
አፈና በአስቸኳይ ይቁም!!

Filed in: Amharic