>
5:13 pm - Monday April 19, 9655

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩም በጨለማ ቤት  (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩም በጨለማ ቤት
ብርሀኑ ተክለያሬድ
ጠበቃው አሁን በስልክ እንደነገረኝ ኤልያስ ቅዳሜ ከመያዙ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የባለአደራ ምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ነበር
ዛሬ ጠዋት ፍርድ ቤት ሲቀርብም ከብ/ጄ አሳምነው ሚስት ጋር አባሪ ሆኖ ከ14ሰዎች ጋር ፍርድ ቤት ቀርቧል
ፖሊስ የሽብርተኝነት ድርጊት ፈፅመዋል ህገወጥ ሰነድ አዘጋጅተዋል የጦር መሳሪያ ደብቀዋል ወዘተ ክሶችን አቅርቦ ቀጠሮ ጠይቋል
ጠበቃው በበኩሉ በጥቅል ከቀረበው ነገር ውጪ በእያንዳቸው ላይ የቀረበ የወንጀል ድርጊት የለም ድርጊቱንም መንግስት የግለሰቦች ግድያ እያለ እየገለፀ ፖሊስ ደግሞ ሽብርተኝነት ማለቱ አሳማኝ አይደለም የአያያዛቸውም ሁኔታ አስጊ ነው ብሏል
አስገራሚው ነገር እድሜያቸው ያልደረሰ ህፃናትም በክሱና በእስሩ ተካተዋል
ፍርድ ቤቱ ለሀምሌ 28 ቀጠሮ ሰጥቶ ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል
መንግስት ሆይ ጉዳዩን በግልፅ እና ከፕሮፓጋንዳ በፀዳ መልኩ አሳውቀን!
እርግጥ ነው ህዝቡ መንግስትን ህግ እንዲያስከብር ሲወተውት ነበር፤ ያ ማለት ግን አሸባሪዎችን ጓዳ አስቀምጦ ተሸባሪዎችን ወደ ግዞት አውርድልን ማለት አይደለም ሊሆንም አይችልም።
ይህ የጅምላ  እስር በምን ምክንያት እንደሆነና ለምን አላማ ተፈልጎ እንደሆነ መንግስት በአፋጣኝ የፍትህ ሥርዓትን በተከተለ ሁኔታ  ጉዳዩን ለህዝብ ግልፅ ሊያደርግ ይገባል፡፡
ከለውጡ በፊትም ታስርው የነበሩ ጋዜጠኞችን ዳግም ለእስር ለመዳረግ ተራ ጥርጣሬን እንደምክንያት ማስቀመጥ ነውር ስለሚሆን፣ መንግስት ሆይ ጉዳዩን በግልፅ እና ከፕሮፓጋንዳ በፀዳ መልኩ አሳውቀን፡፡
ይህ ሌሎች ሀገር አቀፍ እስሮችንም የሚመለከት ሲሆን፣ የአንድ ጋዜጠኛ አላግባብ እስር ብቻውን ግን እንደ የሕዝብ ጅምላ እስር እንደሚቆጠር ለለውጡ የታገሉትም ሆኑ ለውጡን በአደራ ተቀብለው የሚመሩትም አይዘነጉትም ብዬ አምናለሁ፡፡
Filed in: Amharic