>

ሕዝቅኤል ጋቢሳ እና ሌንጮ ለታ በመቀሌ (ሀብታሙ አያሌው)

ሕዝቅኤል ጋቢሳ እና ሌንጮ ለታ በመቀሌ
ሀብታሙ አያሌው
*  “ኦሮ-ማራ ታክቲክ ነው እንጂ ስትራቴጂክ
        ሶሊዳሪቲ ኣልነበረም። ያልነበረ ስለሆነም
        አምቦ ላይ ሙቷል!!!”
 
በሁለቱ የኦዴፓ ቁልፍ ሰዎች (በሪፐብሊኩ ጋርድ መሪ በሌ/ጀ ብርሃኑ በቀለ እና በብሔራዊ ደህንነት ኃላፊው ደመላሽ ወ/ገብርኤል)  ተገቢው ጥበቃ እና እንክብካቤ የሚደረግላቸው ኢትዮጵያን አፍርሰው ኦሮሞ ሪፐብሊክ የመመስረት አላማቸውን ለማሳካት ቀን ከሌት በነፃነት እየሰሩ ያሉት ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ጋቢሳ አቶ ሌንጮ ለታን አስከትለው መቀሌ ከትመዋል።
ባለፈው አንድ ዓመት ከቦረና እስከ ወሎ የሚደርስ ካርታ አሰርተው ያለማንም ከልካይና ገላማጭ በፌደራል መንግስት የተሟላ ድጋፍ እየተደረገላቸው የወረራ አላማቸውን ለማሳካት ሲቀሰቅሱና ሲያደራጁ የነበሩት እነ ሕዝቅኤል ጋቢሳ አጀንዳቸውን ሸክፈው ወደ መቀሌ ማምራት መርጠዋል።
በተጠና መንገድ በጃዋር የሚመራው  ክንፍ ደቡብ ክልልን ወደ ዘጠኝ ትናንሽነት ለመቀየር ሲሰራ የደህንነቱም ሆነ የሪፐብሊኩ ጋርድ ሙሉ ጥበቃና ድጋፍ እንዳልተለየው ልብ ይሏል።
ህወሓት አቅም ከድቷት መቀሌ ከትማለች፤ ደቡብ ክልል በስልት እንዲበታተን ተደርጓል፤ የአማራ ክልል በረቀቀው “መፈንቅለ መንግስት”  የሚል ሴራ አሉ የሚባሉ መሪዎቹን በግድያ እና በእስር  እንዲያጣ ተደርጓ ባልተቋረጠ ሁኔታ ወጣቶቹም መለቀማቸው እንደቀጠለ ነው።
የአራት ድርጅቶች ግንባር የነበረውን ኢህአዴግን በዚህ መንገድ በማሽመድመድ ብቸኛ ኃይል እየሆነ ያለው ኦዴፓ (የኦሮሞ ዴሞክራሲ ፓርቲ)  በጦር ክንፍነት የክልሉን ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ  በአንድ በኩል፤  በሌላው ጫፍ ባንኮችንና የመንግስት መሳሪያ ግምጃ ቤት ጭምር ዘርፎ እንዲደራጅ የተደረገውን የኦነግ ኃይል በማፈርጠም ግስጋሴውን ቀጥሏል።
ወሎ ” ሰሜን ኦሮሚያ ነው”  የሚል ግልፅ አቋም እያራመደ ያለውን  የዚህን አደገኛ  የተቀናጀ ቡድን  አሰላለፍ  በሚገባ ተረድቶ የነበረው  ጀነራል አሳምነው ፅጌ “በታሪክ ከገጠመን ሁሉ የሚከፋ አደጋ ከፊታችን ተደቅኗል”  ያለበትን አውድ ሆን ብሎ በማንሻፈፍ ሐይማኖታዊ ገፅታ እንዲይዝ  መደረጉ አይዘነጋም።
አሁን ነገሮች የበለጠ ግልፅ እየሆኑ ይመስላል።  የተፈፀመው  የተቀናጀ ሴራ የአማራ ክልልን አከርካሪ ሰብሯል የሚል እምነት በአሜሪካዊው ኸርማን ኮኽን ብቻ ሳይሆን  የተጠራቀመ ጥላቻ አዝለው በሚኖሩት ገንጣይ ኃይሎችም ጭምር የተያዘ መሆኑ እየታየ ነው።
ያቀዱት የአማራ ክልልን በአውራጃዊነት አባልቶ የመበታተን ሴራ ባልተጠበቀ ሁኔታ ከሽፎ “የሞትንም እኛ ያለንም እኛ” የሚል አቋም መያዙ ከባድ ድንጋጤ ፈጥሯል።  ይፈርሳል ያሉት አዴፓ ባልጠበቁት ፍጥነት ከታቀደለት ወጥመድ መሹለኩን ሲያዩ ህወሓት በመግለጫ ወደ ፉከራ ስትሸጋገር ኦነጋዊ ክንፍ ለአጋርነት መቀሌ ተገኝቷል።
ማለዳ ገስግሶ ሌንጮን አስከትሎ መቀሌ የገባው ሕዝቅኤል ጋቢሳ  መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባደረገው ንግግር ህንዲህ ሲል አስጨብጭቧል።
       “ኦሮ-ማራ ታክቲክ ነው እንጂ ስትራቴጂክ
        ሶሊዳሪቲ ኣልነበረም። ያልነበረ ስለሆነም
        አምቦ ላይ ሙቷል።
አሁን ሁሉም ነገር ግልፅ እየሆነ መጥቷል ያልኩህ ለዚህ ነው።  የአማራ ህዝብ ህልውና ያሰጋኛል የምትል ማንኛውም ፖለቲከኛ  የተደገሰልህን እያየህ በአይረቤ ምክንያት እርስ በእርስ ከተሻኮት በራስህ አንገት ላይ ሰይፍ እንደመዘዝክ እወቀው።   መግለጫ ላይ ተንጠልጥለህ ጉልበትህን ህወሓትን በማውገዝ ከጨረስክም መስመር ስተሃል።
ተናበብ፣ መረጃ ተለዋወጥ፣ ተጠባበቅ…ሴራውን ለማክሸፍ ተረባረብ።  ዛሬ ከነችግሩም ቢሆን ለአዴፓ ጉልበት ሁነህ ቀን ሲመጣ  በጊዜው ውቀሰው።                      ይቆየን !!
Filed in: Amharic