>

"ህወሓት የ70 አንደርታን ህዝብ በቁሙ እያፈራረሰችው ነው!"(በዘመድኩን በቀለ) 


አሁን ደግሞ ተረኛው ደም እንባ አልቃሽ 
     የመቀሌ እንደርታ ህዝብ ሆኗል!!!
       ዘመድኩን በቀለ
* “ህወሓት የ70 አንደርታን ህዝብ በቁሙ እያፈራረሰችው ነው!” ይላል ከወደ ትግራይ የመጣው ዜና:-
 
……  ትግራይ መቀሌ ትግሬ ወንድሞቻችን በዚህ በክረምት በአጅሪት ህወሓት ቤታቸው በላያቸው ላይ እየፈረሰ ስለሆነ እሱን በተመለከተ የምለው አለኝ:-
★ እኔ ዘመዴ ጦማሬን የሐሰት ቅብ አልቀባውም። ነጭ ነጯን እነግራችኋለሁ። ስትፈልግ መቀበል ሳትፈልግ ያለመቀበል የአንተ የአንባቢው ፈንታ ነው። ጦማሬ እንደ ኮሶ መድኃኒት ያለ መራራ ነው። ለበሽታው መፍትሄ የሚገኘውም ይሄን መራራ እውነት ስንጠጣው ነው። እውነቱን ስንነጋገር ብቻ ነው። እኔ አልሸነግላችሁም። ሃቋን ቁጭ አደርግላችኋለሁ። ተቀበላችሁ አልተቀበላችሁ እሱ የራሳችሁ ደንታ ነው።
★ በዚህ ጦማር የህወሓት ቅልቦችና ምስኪን ትግሬ ወንድሞቼ ሊንጫጩብኝ ይችላሉ እሱም ጉዳዬ አይደለም። የእኔ ሥራ እቅጯን ተናግሬ የመሸበት ማደር ብቻ ነው።
★ በህወሓት እየተጠበጠብክ አነ ወዲ ትግራይ፣ ወዲ ጅጋኑ፣ አነ ወዲ ተጋሩ፣ ቅብጥርሶ፣ ምንጥሶ እያልክ ስትሸልል ብትውል መሬት ያለው እውነታ ግን ሌላ ነው። እና እሱን ዋጡት። መድኃኒቱን ይኸው ሰጠኋችሁ። ጨልጣችሁ ተጋቱት። ትፈወሳላችሁ። አከተመ።
••• የዚህ ጦማር መጻፍ ዋነኛው ገፊ ምክንያት በትግራይ የሚገኙ ከ10ሺ በላይ ቤቶች በዚህ ክረምት ይፈርሳሉ ተብሎ መነገሩን ምክንያት በማድረግ ነው።
•••
የጊዜ ጉዳይ እንጂ ህወሓትና ህወሓት መራሹ የኢህአዴግ መንግሥት በዚያች ምድር በህይወት እስካሉ ድረስ በአንድም በሌላ መልኩ በኢትዮጵያ ያሉ ነገዶች ተራ በተራ ደም እንባ ማልቀሳቸው አይቀርም። የህወሓት ቆሪጥ እንኳን በጉያው ላለው የትግራይ ህዝብ በሩቅ ያለው የሲዳማን ህዝብ ራሱን በራሱ ቆርጥሞ እንዲበላ ከማድረግ አልቦዘነም።
•••
መነሻውን ከዓደዋ ትግራይ ያደረገው ህውሓት፣ መጀመሪያ ትግራይን ከዚያም መላዋን ኢትዮጵያን እንደ ገል አድቅቆ፣ እንደብረት ቀጥቅጦ፣ እንደ ድንጋይ ፈልጦ አንቀጥቅጦ የገዛው ቡድን ነው። ከዓደዋም ያውም የአንድ ሰፈርና ከአንድ ቤተሰብ የተገኘ የአቦይ ስብሐት ነጋ ቤተሰብ የሆነው ሥርወ መንግሥት ነው የዚህ የሁሉ ኮተት አድራጊ ፈጣሪ።
•••
ህወሓት መላውን ኢትዮጵያ በብሔር ከፋፍላ ትግራይን ግን በብሔር መከፋፈሉ ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ የተነሳው ዓይነት እሳት ወደፊት ይነሳብኛል ብላ በመስጋት ነበር ትግሬን በዘር ሳይሆን በአቅጣጫ ከፋፍላ የሸነሸነችው። መእከላዊ ትግራይ፣ ምሥራቅ ትግራይ፣ ደቡብ ትግራይ በማለት ነበር የሸነሸነችው። ነገር ግን በትግራይ ብሔር ብሔረሰቦች ሳይኖሩ ቀርተው አይደለም። እንዲያ ማድረጉ አደጋ እንዳለው ስለገባት እንጂ። አደጋውን ለኢትዮጵያውያን አሻምታ፣ ሻሞ አድርጋ እሷ ግን ብልጥ ሆና አደይ ትግራይን ሀገር ለማድረግ አብዝታ ሠራች። በተከፋፈለች ኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ ሲንጋፖር የሆነች ትግራይን ለመገንባት በብዙ ደከመች። ትግሬዎችም በወቅቱ ተደሰቱ።
•••
የተምቤን ህዝብ፣ የራያ ህዝብ፣ የወልቃይት ህዝብ በግድ ትግሬ የተደረገ ህዝብ ነው። የኢሮብ ህዝብ የራሱ ባህልና ቋንቋ ያለው ህዝብ ነው። አሁን ዋና ከተማ ሆና የተገነባችው መቀለ ያለችበት ቦታ የ70 አንደርታ ህዝቦች ርስት ነው። ነገር ግን እንደርታዎች በገዛ ከተማቸው ተጠቃሚዎች አይደሉም። ሥልጣኑም፣ ሥራውም፣ ንግዱም ሁሉ በዓድዋ ልጆች የተዋጠ ነው። ከቀበሌ ጥበቃ እስከ ክልል አስተዳደር የዓደዋ ልጆች ናቸው የተቆጣጠሩት። እናም እንደርታ በገዛ ከተማው የበይ ተመልካች ነው። የአንደርታ ሥራ መቃም፣ ማጨስ፣ ራያ ቢራ እና ስዋ መቐለ ሲጠጣ መዋል ማደር ነው። የመቀሌ ወጣት እንዲጀዝብ የተፈረደበት ወጣት ነው።
•••
ትግራይ ደሴት አይደለችም። ትግራይ የኢትዮጵያ አንዷ የሰውነት ክፍል ናት። እጅም፣ አንገትም፣ አይንም አፍንጫም ልትሆን ትችላለች። በኢትዮጵያ የሚፈጠር ማንኛውም ችግር እሷንም ይገጥማታል። ይነካታልም። ኢትዮጵያ ስትታመም ትግራይም ትታመማለች። ነገር ግን የህወሓት ሰዎች ትግራይን እንደልዩ ወደብ ነበር የቆጠሯት። ትግራይን በተለየ ሁኔታ ገንብተው ሌላውን የኢትዮጵያ ክፍል በጣጠሱት፣ ከፋፈሉት፣ ፈንጂ ቀበሩበት። የማይነጋ መስሏቸው በቋት ውስጥ ተጸዳዱ።
•••
የመሪዎቹ ሌብነት ለተራው ትግሬ ተረፈው። ተራው ትግሬ ያልበላውን ትፋ ተባለ። በዓባይ ፀሐዬ ስኳር መቋም እሱ ተሰደበ። በጌታቸው አሰፋ ጭካኔ እሱ የቀን ጅብ የሚል ስያሜ በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር በኮሎኔል አቢይ አማካኝነት በይፋ ስም ወጥቶለት ሀገር ሁሉ ትግሬን ሰደበበት። ኦሮሞው ጠቅላይ ሚንስትር ትግሬ ጓደኞቹን በስም ጠቅሶ መስደብ ሲገባው መላው ትግሬን ሰድቦ ለሰዳቢ ሰጠው።
•••
በመላዋ ኢትዮጵያ እየዞረ ልዋጭ፣ ልዋጭ እያለ አፈር ግጦ ይበላ የነበረው ትግሬ በህወሓት ጦስ በየደረሰበት ሰላይ፣ የቀንጅብ፣ እየተባለ ተቀጥቅጦ ተባረረ። ያለፉትን 27 ዓመታት በኢትዮጵያ በተለየ ሁኔታ እየጨፈሩ ሀገር ምድሩን በአንድ እግሩ ያቆመው የትግሬ ወጣት፣ በፒያሳ፣ በቦሌ፣ በካዛንቺስ፣ በ22 እና በቺቺንያ ዓለማቸውን 24/7 ሲቀጩ የነበሩ ትግሬዎች ከለውጡ በኋላ አብዛኛው ተሰድዶ ወደ ትግራይ ተመመ። አዛውንቶቹ እነ አቦይ ስብሐትም ወደ መቀሌ ተሰደዱ። ሥልጣኑን አባቶርቤዎች ተቆጣጠሩት።
•••
አሁን ለሁሉም ማጠፊያው አጥሮባቸዋል። ትግሬዎቹ በሥልጣን ዘመናቸው ወንድም የሆነውን፣ ጎረቤት የሆነውን ዐማራን ጠላት አድርገው ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ዐማራን ጠላት እንዲያደርጉ በሰፊው ስለቀሰቀሱ ለጊዜው ዐማራ በተገኘበት እንደ እባብ ተቀጠቀጠ። ተዋረደ። ተዘረፈ። ተሰደደ። በገፍም ተገደለ፣ ታሰረ። ይሄ ሁሉ ሲሆን የህወሓት ደጋፊዎች ጮቤ ረግጠው ይዘፍኑ ነበር። ከበሮ እየመቱ እየዘለሉ ይጨፍሩ ነበር።
•••
አብዛኛው ትግሬ ነገ ክፉ ቀን ይመጣል ብሎ የሚያስብበት አእምሮ አልነበረውም። ሁሌ ፋሲካ ነበር። ሁሌ ጭፈራ ነበር። ተቃውሞ የትም ሲነሳ በለው። ሌባሁላ። የደርግ ርዝራዥ። አሸበርቲ ሁላ፣ የግብጽና የሻአቢያ ተላላኪ እያሉ ከግፈኛው ህወሓት ጋር ተደርበው ከመሳደብ በዘለለ የሚጎዳው ህዝብ ወገናችን ነው ብለው የማዘን ልብ ተነፍገው ነበር። በተለይ በውጭ ሀገር የነበሩ ትግሬዎች ኢትዮጵያ የግል ርስታቸው ትመስል ትግሬነታቸውንና አግአዚ ጦራቸውን በመተማመን ስደተኛውን ኢትዮጵያዊ ሁላ “ ቅይ ትገባታለህ ” ሲሉ ቅሽሽ አይላቸውም ነበረ። ዛሬ ያ ሁሉ ትዕቢት ተንፍሶ እንደ ጉድ እጥፍጥፍ ብለው ተኮራምተው ሳያቸው ያሳዝኑኛል። በተለይ አንድ ኬቢ አብ ይባል የነበረ ትግሬ ይዝትብኝ የነበረውን ዛቻ ሳስታውስ አሁን ሳቄ ሁላ ይመጣል። ተነፈሰ መሰለኝ። ብጽፍለት እንኳ አይመልስልኝም። የሆነው ይሄው ነው።
•••
ዘመን ተለዋዋጭ ነው። ሁሉም ትግሬ ጨካኝ አልነበረም። ለምሳሌ እኔ ወደ ጀርመን ስወጣ ለኤንባሲ የጻፈልኝ ትግሬ ጓደኛዬ ነው። ትግሬ ወንድሜ ነው። ዘመዴ የእኛ ሰዎች የሆነ ቀን ይበሉሃል እያለ የሚጨነቅልኝ በአባቱም በእናቱም ትግሬ የሆነ፣ እየተታከሶ አዲስ አበባ የገባ ታጋይ ነው። ክርስቲያን ታጋይ። አጎት ወንድም እህቶቹን በጦርነት ያጣ ተጋይ ነው። አሉ እንዲህ ዓይነት አርቆ አሳቢ ትግሬዎች። የማይነጋ መስሏቸው ቧ፣ አንተ ሙንአባትክ ነው እያሉ ያቅራሩ የነበሩ እንደነበሩ ሁሉ ደግሞም አሉ። አዛኞች። ይመጣ ያለው ነገር ያስፈራቸው የነበሩ አሉ።
•••
በኤንባሲ ሁሉ ትግሬ፣ በአየርም፣ በምድርም ነጋዴው ሁሉ ትግሬ፣ ከእድር ዳኛ እስከ ቀቤሌ ሊቀመንበር፣ ከታክሲ ተራ አስከባሪ እስከ የትኛውም ማኅበራት መሪዎች ድረስ ትግሬ ያልገባበት ማኅበር ፈራሽ ነበር። ትግሬ ልክ እንደ ቡዳ መድሃኒት ይቆጠር ነበር። ይሄ ሁሉ ሲሆን ኧረ ይሄ ነገር ግፍ ነው። ነገ በልጆቻችን ላይ ጣጣ ያመጣል ብሎ የሚጠይቅ ትግሬ እምብዛም ነበር። ትግሬ ከዓመት በፊት የታሰረ ወንጀለኛ ከእስርቤት የማስፈታት ሥልጣን ነበረው። ዳኛ፣ ዓቃቤ ሕግ፣ ፖሊስና ወታደር የማዘዝ ሙሉ ሥልጣን ነበረው። መንገድ የሚለቅለት ኢትዮጵያዊ፣ ሳይናገር የሚስቅለት ሚሊዮኖች ነበሩ። ግብር ያስቀንሳሉ። ከጉምሩክ ዕቃ ያስወጣሉ። ከቀበሌ እስከ ክልል ትግሬን የተጠጋ ተጠቃሚ ነበር። ያው ነበር ነው እንግዲህ እንዲህ ባይሰበር።
•••
በጎጃም ነጭ ጤፍ እንጃራ ውድ ነበር። በትግራይ ግን ርካሽ። አምርተው አይደለም። ሸምተው እንጂ። እንዴት ሸመቱት? ብሩ ከየት መጣ እሱን እነሱ ነበር የሚያውቁት። በኢትዮጵያ ሙሉ ቢራ ብርቅ ነበር በመቀሌ ግን እጅ መታጠቢያ ነበር። ኮንዲሚንየም ከዓደዋ በመጡ የትግሬ ሰዎች ሲወረር ኧረ ይሄ ነገር የሚል ልባም ትግሬ ጠፋ። አሳምነው ጽጌ በኮንዲሚኒየም ቤት ሲሰቃይ እነ አብርሃ ማንጁስ ዋና ያለው ቪላ ገንብተው ይቀማጠሉ ነበር።  የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የትግራይ ኤምባሲ እስኪመስሉ ድረስ በትግሬ ልጆች ሲወረር ኧረ ይሄ ነገር ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ያጣላናል። ፍትሃዊ አይደለም የሚል አንድም ትግሬ አልነበረም። በፈለጉት ቦታ ህንፃ እንደ ችግኝ ሲተክሉ ብሩ ከየት መጣ ብሎ የሚጠይቅ ብልህ ሰው አልነበረም።
•••
የቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ከትግሬ ተመርጠው ሲሾሙ። የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ከትግሬ ተመርጠው ሲሾሙ፣ ባንኩ፣ ቴሌው፣ ኮንትራቱ ሁሉ ለትግሬ ሲሰጥ ኧረ ይሄ ነገር እንዴት ነው ብሎ የሚጠይቀው እየተሰደበ፣ እየተዋረደ፣ እነሱው ናኙበት። ተሾሙ ተሸለሙበት። አሁን ያ ሁሉ እንዳልነበር ሆኗል። ትግሬን ያሰደበችዋ ህወሓት አሁን ምሽጓን መቀሌ ላይ ቆፍራ ትግሬን ወደ መቃብር አብራው ይዛው ለመውረድ እየሠራች ነው።
•••
አሁን ህወሓት የጠመቀችውን ጠላ የቀመሱ የኢትዮጵያ ሰዎች መጠጡ አናታቸው ላይ ወጥቶ በስካር ላይ ናቸው። ትግሬ በመስታወት ቤት ተቀምጦ ዐማራ ከቅማንት፣ ኦሮሞ ከዐማራ፣ አፋር ከሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል ከዐማራና ከኦሮሞ። ደቡብ እርስ በእርሱ ድንጋይ ሲወራወር ከዳር ተቀምጦ ሊያይ ነበር ፍላጎቱ። በኢትዮጵያ ሰላማዊው ክልል ትግራይ ክልል ብቻ ነው ብሎ እስከማወጅ ደረሰ። ነገር ግን ሌሎቹን ነገዶች ድንጋይ እንዲወራወሩ የጆከር ሥራ የሠራው ትግሬው ህወሓት የገነባው መሥታወት ቤት ላይ ሌሎች ብሔሮች የሚወራወሩት ድንጋይ የማረፊያ ጊዜው የደረሰ ይመስላል።
•••
በሱሉልታ፣ በሐና ማርያም፣ በሰበታ፣ በለገጣፎ፣ በቡራዩ፣ በአራት ኪሎ የዐማራ ህዝብ ሰፍሮበታል የተባለን ቦታ ሁሉ ስታፈርስ የከረመችው ህወሓት ልማድ አይለቅምና ከመሃል ሀገር በእሷ ጦስ ምክንያት ተሰድደው ወደ ትግራይ የገቡ የትግሬ ኢትዮጵያ ዜጎችን ቤት በግሬደርና ዶዘር ስትንደው ውላለች። የረሃብ ጊዜን የገዛ ታጋይ ልጆቿን አርዳ በመብላት የክፉ ቀን ያሳለፈችዋ ህወሓት ዛሬም እንደዚያው የክፉ ቀኑን ልጆቿን ደም እንባ እያስለቀሰች ለማለፍ እየሞከረች ነው። የተዘረፈውም ብር ሲያልቅ ምን ታድርግ?
•••
ስለ ዛሬው ሁኔታ የአረናው አቶ አምዶም ገብረ ሥላሴ እንዲህ ይላል። “ የህወሓት መንግሥት በሮማናት ከተማ እንደርታ ወረዳ(መቐለ ዙርያ) “ሕገወጥ ግንባታ” በሚል ምክንያት ከ10,000(ዓስር ሺ) በላይ ቤቶች እያፈረሱ ይገኛሉ።
•••
የማፍረስ ተግባሩ ዛሬ 09/11/11 ዓ/ም ከጥዋቱ 12:00 የጀመረ ሲሆን በ4 ዶዘሮች በመቶዎች የመቆጠሩ ልዩ ሃይሎች፣ መደበኛ ፖሊሶች ምሊሻዎች የታጀበ ነው። የማፍረሱ ተግባር ኑዋሪዎች ያለ ማስጠንቀቅያና ድንገት በመሆኑ ቤቶቹ ከነ እቃቸው ወድመዋል።
•••
የማፍረሱን ሂደት የተቃወሙ ባለቤቶችና ህዝብ በካቴና እየተቸነከሩ በመታሰር ላይ ይገኛሉ። ፎቶና ቪድዩ ለመቅረፅ የሞከሩ ሰዎችም እየታሰሩ ይገኛሉ።
•••
ሚድያታት #BBC #VOA #Dotchovele #DW_Tv #TgTv ወዘተ ሓበሬታ ወዝዑልና ይብሉኹም ኣለው ነበርቲ ሮማናት ዝኾኑ ግዳያት።እያለ ሲጮህ ውሏል።
•••
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በመቐለ መሰቦ ሮማናት (ጣብያ ማኅበረ ገነት) የሚባል ቦታ ላይ በህወሓት አማካኝነት እየደረሰ ያለው ግፍ እስከ አሁን የ463
አቧወራ ቤቶች ከነንብረቱ የወደመ ሲሆን የማፈረሱ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላልም ተብሏል። የሚገርመው ነገር ቤቶቹ እየፈረሱ ያሉት በክረምት በመሆኑ የትግሬ እናቶች እና ህፃናት ላልተፈለገ እንግልትና ችግር በክረምት ወቅት እየተቀበሉ ይገኛሉ።
•••
በእውነት ለእኔ እንደትግሬ ህዝብ አሳዛኝ ፍጥረት የለም። እንደ እሳት የተጠበሰ ህዝብ። ሽማግሌዎቹ በስሙ ገድለው። አፈናቅለው፣ አስረው፣ ዘርፈው እሱ እንዲጠላ አደረጉት። አሁን የትም ክልል ሄዶ በነጻነት ሠርቶ መብላት አይችልም። የት ሂደው ይሰደዱ? የት ይግቡ? በቀይ ባህር ወደ የመን ከሚሰደዱት አብዛኞቹ ትግሬዎች ናቸው። ዐማራም ኦሮሞም በስደቱ ቢኖርበትም አብዛኛው ተሰዳጁ ህዝብ ግን በብዛት ትግሬ ነው። መሪዎቹ ትግራይን ገነት አድርገው ለሌላው ኢትዮጵያዊ በቴሌቭዥን ፕሮፓጋንዳ ይሠራሉ። ተራው ዜጋ ትግሬው ግን መሬት ላይ መከራውን ይበላል።
•••
ከእንግዲህ በኋላ የሚመጣው ጊዜ ደግሞ ከአሁኑ የባሰ ይከፋል። የተማረ የሰው ኃይል በሙሉ የተከማቸው ትግራይ ላይ ነው። እንደበፊቱ በመላው ኢትዮጵያ ተሯሩጦ ለመሥራት ጊዜው አልፈቀደለትም። በመቀሌ፣ በአዲግራት ከተሞች ዘረፋ ተስፋፍቷል። የሥራ አጡ ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት ጨምሯል። በውኃ እጥረት ብዙ ትግሬ እያሰቃየ ነው። ረሃብና በሽታም እየተሰማ ነው። የስንዴ ዱቄት እጥረት በመግጠሙ የዳቦ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል። ጤፍ እንደልብ አይገባም። እናም ትግራይ ችግር አለ። ችግሩ ግፍ የወለደው ችግር ነው። የተጠራቀመ ችግር ነው። አደባባይ እንዳይወጣ ግን ዐማራ ይሰማል ተብሎ የታፈነ ችግር ነው።
•••
ታዲያ ይሄ ሁሉ ሆኖም ገና ስለ ትግሬ በህወሓት መቀጥቀጡን መናገር ስትጀምር ችግራችንን ለምን ዐማራ ይሰማዋል። ልቅሶዋችንንማ ዐማራ መስማት የለበትም። ሞት፣ መፈናቀልና መራብ መጠማታችንን ዐማራ መስማት የለበትም በማለት የጨነቀው ኑሮ እየገፋ የሚንበጫበጨው ትግሬ ይበዛል። ህወሓትም ይሄን አውቃ በደንብ ታሻቸዋለች። ርግጥ አድርጋ ትገዛቸዋለች። እኔ ከሌለሁ ዐማራ ይመጣና ይወጣችሁል። ቅርጥፍ አድርጎም ይበላችኋል ብላ እያስፈራራች ትረግጣቸዋለች።
•••
አንዳንድ ደፋር ትግሬዎች ጉዳዩን፣ ችግሩን በድፍረት ወደ አደባባይ ሲያመጡት እንኳ ራሱ ትግሬው እሪሪሪ ነው የሚለው። ለምን ችግራችንን በአማርኛ ትጽፉታላችሁ? ለምን የዐማራ መሳቂያ ታደርጉናላችሁ? በቃ እንቻለው። ዋጥ እናድርገው ይላሉ። ነገር ግን ነገርየው መፈንዳቱ አይቀርም። በተው ቻለው ሆዴ ዘፈን የሚሸወድ አይደለም።  ሌሎች ኢትዮጵያውያን የቀመሱትን ትግሬም ይቀምሳታል። ፅዋውንም ይጎነጫታል። በጠመቁት ጠላ ሌላውን አስክረው እነሱማ ሳይሰክሩ አይቀሯትም። በሌሎች ቤት የገባው ልቅሶ፣ እየዬ፣ እሪታ፣ ረሃብ፣ መፈናቀል፣ መታሰር፣ መገደል እነሱንም ይገጥማቸዋል። ያውም በዓደዋዎቹ የአቦይ ስብሐት ሥርወ መንግሥቱ ህወሓት በገዛ ልጆቹ ትግሬ መከራውን ይበላል።
•••
በትግራይ የሚገኙት፣ እነ #ኢሮብ፣ #ሰበእንደርታ፣ #ተንቤን፣ #ትግረ፣ #ኩናማ፣ #ሳሆ፣ #ዐማራ፣ #አገው ወዘተ የመሳሰሉትም በቅርቡ ልክ እንደ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ የመብት ጥያቄ ማንሳታቸው አይቀርም። መቀሌ በሰበ እንደርታ ልጆች ትተዳደር የሚለው ተቃውሞም በቅርቡ ይፈነዳል። እስከዚያው ግን ህወሓት ትግሬን ሱሪውን ዝቅ አድርጋ በሳማ መግረፏን ትቀጥላለች። ኢትዮጵያም ትግሬም አብረው ያለቅሳሉ። ተረኛው ኦሮሞ ነው። ኦሮሞም ትግሬው ባለቀሰበት መንገድ ነገ እሪሪ ብሎ ማልቀሱ አይቀርም። ኢትዮጵያ ግን ሁሉን አምባገነን አራግፋ በቅርቡ ትነግሳለች። ይኸው ነው።
•••
ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት። +4915215070996 ደግሞ የቴሌግራም፣ የቫይበር፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው።
@ZemedkunBekeleZ ደግሞ የቴሌግራም ቻናሌ ነው። በዚህም ይከታተሉ።
•••
ሻሎም !  ሰላም !
ሐምሌ 10/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic