>

የአዲስ አበባው ለቡ ቅርንጫፍ ሀያ አንደኛው ተዘራፊ ባንክ ሆኗል!!! (ግዮን ሚድያ)

የአዲስ አበባው ለቡ ቅርንጫፍ ሀያ አንደኛው ተዘራፊ ባንክ ሆኗል!!!
ግዮን ሚድያ
ባንኩ ከ1.7 እስከ 2 ሚሊዮን ገደማ መዘረፉ ተረጋገጧል!!
የኦሮሚያ ኮኦፕሬቲቭ ባንክ (Cooperative Bank Of Oromia) አዲስ አበባ ለቡ ቅርንጫፍ ባለፈው እሁድ ለሊት ተዘርፎ ማደሩ ታዉቋል። የባንኩ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በለጠ ዋቅቤካ እዉነት ተዘርፏል ወይ ተብለዉ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ትክክል ነዉ ባንካችን ተዘርፏል ጉዳዮን ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያካሄደ ነው ብለዋል። ዘራፊዎቹ እነማ ናቸዉ ተብሎ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ የጥበቃ ሰራተኞ ከሌሎች ጋር ተመሳጥረዉ ነዉ ያሉ ሲሆን ጥበቃዎቹ በኤጀንሲ የመጡ ናቸው ስለሆነም የጥበቃ ሰራተኛ ያቀረበልን ኤጀንሲውም ተጠያቂ ይሆናል ብለዋል።
 እንደ አቶ በለጠ ገለፃ የተዘረፈው ገንዘብ መጠን በውል አይታወቅም ያሉ ቢሆንም ከ1.7 እስከ 2 ሚሊዮን ብር ተዘርፏል የሚል ግምት ግን አለን ብለዋል። የገንዘብ ማስቀመጫ ካዝናዉ ተሰብሮ እንደተዘረፈም ታውቋል። ቅርንጫፉ ግን አሁን ላይ አገልግሎት እየሰጠ ነው፣ የአገልግሎት መቋረጥም አላጋጠመም ሲሉ ተናግረዋል።
Filed in: Amharic