>

በሰይጣን ግዛትም ሥላሤዎች አሉ - እንተዋወቃቸው፡፡ (ወልደ ማርያም ዘገዬ)

በሰይጣን ግዛትም ሥላሤዎች አሉ – እንተዋወቃቸው፡፡

ወልደ ማርያም ዘገዬ

በፈረንጅኛው Trinity ባማርኛው ሥላሤ አብን (the Father)፣ ወልድንና (the Son) መንፈስ ቅዱስን (the Holy Spirit) ይይዛል፡፡ በምሥጢረ ሥላሤ ትምህርት ሥላሤዎች አንድም ሦስትም ናቸው፡፡ አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ በሚል አገባብ ይታወቃሉ፡፡ ይህ እንግዲህ በሥነ መለኮት ወይም ቴዎሎጂ ሃይማኖታዊ የዕውቀት ዘርፍ የሚተነተን ነው፡፡

እስካሁን ባለው የሥነ መለኮት ትምህርት ፀላዔ-ሠናያት የሆነው ሣጥናኤል እምቅድመ ፍጥረተ አዳም ወሔዋን ዘመን ከእግዚአብሔር መንግሥት በጠባዩ መማረጥ ሳቢያ ከገነተ ሰማይ ወደ ደይነ ምድር መወርወሩንና መሰል ሰብኣዊና ረቂቅ ፍጡራንን ወደ ግዛቱ ከመጠቅለሉ ውጭ እንደ እግዚአብሔር መንግሥት “ሥላሤ” የሚባል ሥነ ተፈጥሮ የለውም፡፡ ሰይጣን በልማድ እንደምናውቀው የክፋት ምንጭና የብልግናዎች ሁሉ ቁንጮ መሆኑን ነው፡፡ ሣጥናኤል፣ ጋንኤል (ሲበዛ አጋንንንት)፣ ዲያብሎስ፣ ሉሲፈር ወዘተ. በሚባሉ የክትና የሠርክ ስሞች የሚታወቀው ሰይጣን የሞት፣ የስደት፣ የጠብ፣ የግጭት፣ የስቃይ፣ የመከራ፣ የርሀብ፣ የበሽታ፣ የዕልቂት፣ የድርቅ… ተምሣሌትና ዋና መንስዔ እንደሆነ የሁላችን ግንዛቤ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የሰይጣንን ኃይል ለተለያዬ ዓላማ ይጠቀማሉ፡፡ ገንዘብና ሥልጣን ለማግኘት ሲባል ከትንሽ ገንዘባዊ መስዋዕትነት እስከሰው ነፍስ ጭዳነት ለሰይንና አጋፋሪዎቹ በማቅረብ ብዙ የሀብትና የሹት ደረጃዎችን የሚወጡ እንዳ እንገነዘባለን፡፡ የሁሉም መጨረሻ ግን አያምርም፡፡ በሰይጣን ከሚያልፍልህ በእግዚአብሔር ደጅ በድህነት ኖረህ ብትሞት ይሻልሃል፡፡ የሰው ወርቅ አያደምቅም ወንድማለም፡፡ …. ሰይጣን ብድርን ሲያስከፍል በነፍስ እንጂ በቁስ አይደለም፡፡

ከዚህ ተፈጥሮው በመነሣትም በግብርም በአስተሳሰብም እርሱን የሚመስሉ ፍጡራን ከሰዎችም ሆነ ከሌሎች እንስሳት ሲገጥመን “ሰይጣን” እንላቸዋለን፡፡ ዓለማችን እጅግ ብዙ የሰይጣን ምሣሌዎችንና ቀጥተኛ ወኪሎችን አስተናግዳለች፡፡ እነዚህ ሰይጣናት (devil-incarnates) የንጹሓን ዜጎችን የዕለት ከዕለት ሰላም ከማወክ አልፈው ለበርካታ ጦርነቶችና ግጭቶች መንስኤ በመሆን በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የዓለማችን ዜጎች ዕልቂት ዋነኛ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ከነዚህ ሰይጣናዊ ሰዎች ሂትለርን ከጀርመን፣ ሙሶሊኒን ከጣሊያን፣ መለስን ከኢትዮጵያ እዚህ ላይ በዋቢነት ብንጠቅስ ሲያንሳቸው ነው፡፡ እነዚህ ከሞታን ሠፈር የምናስታውሳቸው የአጋንንት ወኪሎች ናቸው፡፡ የዓለማችን ቅርጽ እንዲህ ማስጠሎ የሆነው የነዚህ “ሰዎች” አሉታዊ ሚና ጎልቶ በመውጣቱ ነው፡፡ ጊዜያቸውም ስለሆነ፡፡
በአሁኑ ወቅት በሕይወት እየኖሩ ሰይጣንን በሚያስከነዳ ክፋትና ተንኮል ሀገርንና ሕዝብን እንደደሮ እየገነጣጠሉ የሚገኙ የሰይጣን ልጆች ደግሞ በየሀገሩ አሉ፡፡ እንደኢትዮጵ ግን በሌሎች አይበዙም፡፡ ኢትዮጵያ መንግሥትም ባለቤትም ስለሌላት በተለይ በአሁኑ ወቅት እንዚህ የአጋንንት ወኪሎች እንደልባቸው እየፈነጩ ይታያሉ፡፡ የዘመንን ፍልስፍናዊ ቅኝት በሚገባ መጠቀም ማለት እንደነሱ ነው፡፡ ከነዚህ መካከል ዋና ዋናዎቹና ይህን ካምፕ በፊታውራሪነት የሚመሩት የሚከተሉት “ኢትዮጵያውያን” ናቸው፡፡
• ሕዝቅኤል ጋቢሣ
• በቀለ ገርባ
• ጃዋር ሞሀመድ

እነዚህ ናቸው በሀገራችን “የሰይጣን ሥላሤዎች ናቸው” ያልኳቸው፡፡ አንድም ሦስትም እየሆኑ ሀገርንና ሕዝብን ለማጨራረስ ቀን ከሌት ያለ አንዳች መታከት የሚባዝኑት የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላቶችን ማወቅ ተገቢና ወቅታዊም ነው፡፡ እነሱም ይህን ያውቃሉ፡፡
ሕዝቅኤል ጋቢሣ ሌላው ሁሉ ቀርቶ የአብራኩ ክፋይ የሆነች ልጁ ከዩኒቨርስቲ ስትመረቅ በኢትዮጵያ ባንዲራ ስትደምቅበት የሰይጣን ሽንት የሆነው እርጉም አባቷ ግን የሚሠራው ሁሉ የልጁን ሀገር ድራሽ ማጥፋት ሆነ፡፡ እበት ትል ይወልዳ ማለት ይሄኔ ነው፡፡ የዚህን የሰንበት ጽንስ ዕኩይ ተግባር እኔ ልቅርና አባቱ ሰይጣን ራሱ ዘርዝሮ አይጨርሰውም፡፡ የሚናገረውና የሚጽፈው ሁሉ እንዳንዳች ነገር የሚቆንስና የሚገለማ ነው፡፡ በምን ቀን ይህን መሰሉ የአጋንንት መንፈስ እንደተጣባው አይታወቅም፡፡ ዘመድ አዝማድ ቢኖረው የሰውዬው ደዌ ብዙዎችን ሳይበክልና የጋራ መኖሪያችንን ሳያወድም ክፍል ተቆጥሮለት ወደ ታወቀ ጠበል ወስዶ ማስጠበል ነበር፡፡

በቀለ ገርባ የሚሉት በሽተኛ ደግሞ አለ፡፡ ከሰው ልጅ ተፈጥሮ በማፈንገጥ “ኦሮሞ ወንድ ከኦሮሞ ሴት ውጭ ከተኛ ዘሩን እንዳጠፋ ይቁጠረው” ብሎ ሲናገር ቅንጣት የማያፍር ጥቁር ሰይጣን ነው፡፡ “በኦሮምኛ ካላናገሯችሁ ምንም ዕቃ አትሽጡላቸው፣ ‹ነጋቲ ቡላ› በሏቸው” የሚልና ግም ነጭ ጭቃ አናቱ ላይ ተሸክሞ የሚዞር በሰው አምሳል የተፈጠረ የለዬለት ጋኔን ነው፡፡ ለስ የቋንቋና ሥነ ጽሑፍ መምህር ነው፡፡ ግን የቋንቋና ማኅበረሰብን ዕድገትና ዘፈቀዳዊ ግንኙነት አያውቅም፡፡ ቋንቋ ባሕርያዊ እንዳልሆነም የማይረዳ ገሪባ ነው፡፡

ጃዋር እንኳን ከሰይጣንም በላይ ነው፤ ሰይጣን ቢሞት የሚተካው አልጋ ወራሹ ጃዋር መሆን አለበት – ሰይጣን የሚሞት ከሆነ፡፡ እንደሚታማውና መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ይህ ጋንኤል ኢትዮጵያን ለመበታተን እንደ ግብጽ ባሉ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች የተመለመለና በብዙ ሚሊዮን ዶላር ተገዝቶ ሥራውን በአግባቡ እየተወጣ ያለ ጎልማሣ ነው፡፡ ይህ ሰው እስካለ ድረስ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ገና ብዙ ፍዳ ያገኛቸዋል፡፡ (ይህ አባይ የሚሉት ወንዝ ምነው ጋና ወይ ካሜሩን ውስጥ በሆነ! ጠቅሞ ላይጠቅመን አሣራችንን አበላን አይደል?) የተከፈተለት ሚዲያ ከፌዴራል መንግሥት በግልጽም በድብቅም ድጋፍ ከማግኘቱም በተጨማሪ የላኩት ኃይሎች ስለገንዘብ ምንም እንዳያስብና እንዳይጨነቅ ዋስትና ገብተውለታል፡፡ ለዚህም ይመስላል እንደኢሳት ያሉ ጣቢያዎች ነጋ ጠባ የገንዘብ ዕርዳታ በመለመን ሥራ ሲጠመዱ የጃዋር ኦኤምኤን ግን እንኳንስ ገንዘብ ሊለምን ለሠራተኞቹ የሚከፍለው ደሞዝ ራሱ ከማንም ጋር የማይወዳደርና ሥራ አስኪያጁ ጃዋርም ጥይት በማይበሳው እጅግ ውድ መኪና የሚንፈላሰስ፣ ወፍ ከሰማይ በሚያወርዱ ሥልጡን ኮማንዶዎች ከሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር በበለጠ የሚጠበቅና ተሰሚነቱና ተፅዕኖውም ከማንም በላይ የሆነው፡፡ ይህን ሁሉም ያውቃል፡፡ ክርስቲያን ታደለ የሚባል የአብን ምክትል ሊ/መንበር(?) ወዶና ፈቅዶ ያልተወለደበት አማራነት ወንጀል ሆኖበት በጎሣዊ ማንነቱ ሰበብ ተይዞ ሲታሰርና ሲሰቃይ ጃዋር ግን ሲዳማን ከደቡብ ለመገንጠል በግልጽ ዐዋጅ ዐውጆ ለብዙ ሕዝብ ዕልቂትና ለንብረት ውድመት ዋነኛ ተጠያቂ መሆን ሲገባ ማንም ዝምቡን እሽ አላለውም – የሚገርም የነገሮች ሂደት፤ በታሪክ የሚያስጠይቅ ልዩ ኦህዲዳዊ የአስተዳደር ዘይቤ፤ በታሪክ ማኅጸን የተረገዘው ህግ ሲወለድ እስከሞት ሊያስቀጣ ለሚችል ከፍተኛ ወንጀል የሚዳርግ በዘረኝት ላይ የተመሠረተ ሸውራራ ኦነጋዊ መንግሥት የተተከለበት አስደናቂ ዘመን፡፡ ይህ የሚያሳየው የፌዴራል መንግሥት ተብዬው የኦህዲድ ባለሥልጣናትም ጃዝ ብሎ ጃዋርን በላከው ኃይል ተፅዕኖ ሥር መውደቃቸውን ነው፡፡ እንጂ በአንድ ሀገር ውስጥ የተለያየ ሕገ መንግሥትና አስተዳደር ያለ በሚስመስል ሁኔታ አማራውን እያጠቁ ኦሮሞው አገር ምድሩን እንዲቆጣጠርና ጽንፈኞች ያሻቸውን እንዲያደርጉ ፈረሱም ሜዳውም ባልተለቀቀላቸው ነበር፡፡ ይህ አሣፋሪ ዘመን ማለፉ አይቀርም፡፡ ሲያልፍ ግን ብዙ ጠባሳ እንዳይል አእምሮን ከአሁኑ በቅጡ መጠቀም ይገባል፡፡ በዱባ ጥጋብ የሚፈነጥዝ ዘረኛና ሤረኛ ሁሉ ቆም ብሎ የማሰቢያ ጊዜው አሁን መሆኑን መረዳት አለበት፡፡ “እዩኝ፣ እዩኝ” “ደብቁኝ፣ ደብቁኝኝ”ን እንደሚስትል ከወዲሁ ካልተረዳን ዘሬ ትናንትን እንዳልሆነ ሁሉ ነገም ዛሬን አይንምናቢያንስ ለመጪው ትውልዳችንና ለልጆቻችን በማሰብ ከፈረሰኛ የስት ደንገላሳ ወጥተን በጥሞና እናስብ፡፡ እነደቻሣና ኩምሣ እየሰማችሁኝ ነው? ከነሐጎስና ገረ’ግዚሃር ካልተማራችሁ ከማን ልትማሩ ትፈልጋላችሁ? ዕደጉ እንጂ! እኛም “ወፌ ቆመች” እንበላችሁ፡፡ እንደቀጨጫችሁ አትቅሩብን፡፡

ስለ አጋንንታዊ ሥላሤዎች ይችን ታህል ካወራን ለዛሬ ይብቃን፡፡ እምነታችንን አጥብቀን እንራመድ፡፡ ለአጋንንት መድኃኒቱ የእምነት ጽናት ነውና በፈጣሪ ብቻ እንታመን፤ ለርሱም ችግራችንን እንንገረው፡፡ መሥራት ያለብንንም እንሥራ፡፡ ዝም ብለን ግን አንቀመጥ፡፡

Filed in: Amharic